ፈልግ

ባለፈው ወር በሊቢያ ዴርና ከተማ የደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ ምስል ባለፈው ወር በሊቢያ ዴርና ከተማ የደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ ምስል 

ከ‘ዳንኤል አውሎነፋስ' ውድመት በኋላ ወጣት ሊቢያውያን ከተማዋን እንደገና ለማቋቋም እየሰሩ ነው ተባለ

በሊቢያ ዴርና ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በወደብ ከተማዋ ላይ ከፍተኛ የሰው ህይወት እና ንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ዳንኤል አውሎ ንፋስን ተከትሎ ከተማቸውን መልሶ ለመገንባት እየሰሩ ነው።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በሊቢያ የዴርና ከተማ ጳጉሜ 5, 2015 ዓ.ም. ከተማዋን በመታው አውሎ ንፋስ ሳቢያ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደብዛቸው ጠፍቷል። ከተማዋ ከአንድ ወር በፊት በአውሎ ነፋሱ ከተመታች በኋላ በአደጋው የፈራርሱ ቤቶች አሁንም ድረስ ምንም ጥገና ሳይደረግላቸው እንደፈረሱ የሚታዩ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኪሳራ እና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገኛሉ።
በየትምህርት ቤት ጊቢዎች እና በሌሎች ቦታዎች ሰፍረው የሚገኙ ቢያንስ 30,000 የሚሆኑ ተፈናቃዮችን መድረስ አስቸጋሪ ስለሆነ አሁንም ድረስ ካለምንም ዕርዳታ ተቀምጠዋል።

ከተማቸውን ወደ ቀድሞ ሁኔታዋ ለመመለስ ተልዕኮ ላይ ያሉ ወጣቶች

በሊቢያዋ ከተማ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ የተቆጩ ጠንከራ የአከባቢው ወጣቶች ከተማቸውን ወደ ቀድሞ ስፍራዋ ለመመለስ እና በአደጋው ምክንያት የተቸገሩትን ወገኖች ለመርዳት ፈቃደኛ ሆነዋል።
እነዚህ ወጣቶች “የዴርና ዘመቻ ከወጣቶች ጥረት ጋር” በሚል መሪነት በጋራ በመስራት ከደረሰባቸው ሀዘን ለመጽናናት እና ከተማቸውን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ የበጎ ፈቃድ ተልእኮ እያደረጉ ይገኛሉ።
በዴርና እምብርት የሚገኘው የካፌ እና የፀጉር ቤት ባለቤት የሆነው አቡበከር ማንሱሪ በመጀመሪያ የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቱን ካገኙት መካከል አንዱ ነው። አቡበከር “ዛሬ ካፌው በ'ዴርና ዘመቻ ከወጣቶች ጥረት ጋር’ ጸድቷል ሲል ለአፍሪካ ኒውስ ተናግሯል። አክሎም "እውነታው ግን ፥ ምንም እንኳ ውስን አቅም ቢኖርም ይህ ትልቅ ጥረት ነው” ብሏል።
ከተማዋ እንደገና ወደ ህይወት ጎዳና መምጣቷን ለማመልከት ለወጣት ሰራተኞች የቡና ግብዣ አድርጎላቸዋል። ይህንንም በማስመልከት “እነዚህ ወጣቶች ለሚያደርጉት ተግባር ነፃ ቡናን ለእርዳታ ሥራቸው እና ለሞራል ማበረታቻ አቅርበናል” ሲሉ አቶ አቡበከር አክለዋል።

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ታሪክ

ከአደጋው የተረፉት ዋሌድ ሙሳ ኦትማን አደጋው በእርሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ ያደረሰውን ጥፋት በማስታወስ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ የደረሰውን አደጋ ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
“በመጀመሪያ ጣሪያው ወደቀ፥ ከዛም የቤቱ እቃዎች በሙሉ፣ ከወረቀቶቼ እና ከንብረቶቼ ጋር ጠፍተዋል። ጎረቤቶቼ፣ ጓደኞቼ እና ዘመዶቼ ሁሉም በአደጋው ሞተዋል። እግዚአብሔር ምህረቱን ይስጣቸው” ሲሉ አቶ ዋሌድ ኦስማን ተናግረዋል። አሁን ላይ አቶ ዋሌድ የዕለት ተዕለት ስራቸው ቤቱን ከፍርስራሽ እና ቆሻሻ የማጽዳት ስራ ላይ ያጠነጠነ ነው። ጎርፉ ንብረታቸውን ከማውደሙ በተጨማሪ የበርካታ ቤተሰቦቻቸውን ህይወት ቀጥፏል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥረቶች

ዩኔስኮ እና መላው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መዋቅር ትምህርትን ለማበረታታት እና ለማስተዋወቅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሊቢያ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ተስማምተዋል።
የዩኔስኮ የልዑካን ቡድን ማክሰኞ ዕለት ትሪፖሊ የገባ ሲሆን፥ የትምህርት፣ የባህል፣ የከፍተኛ ትምህርት እና የምርምር ሚኒስትሮችን በማነጋገር ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።
በትምህርታዊ እና ታሪካዊ መዋቅሮች ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም የልዑካን ቡድኑ በአደጋው በጣም የተጎዳውን ዴርናን ይጎበኛል ተብሎም ይጠበቃል።
የዩኔስኮ ልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የመልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ስራዎችን ለማቀድ እና በመነሻ ደረጃ ላይ የሚደረጉ የአደጋ ጊዜ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችሉ ትግበራዎችንም ለማሳደግ ይረዳልም ተብሏል።
 

12 October 2023, 14:56