ፈልግ

ዊፒ ጎልድበርግ ዊፒ ጎልድበርግ 

ዊፒ ጎልድበርግ ‘ር.ሊ.ጳ.ፍራንቺስኮስን ስላስተላለፉት መልዕክት ለማመስገን ዓመታትን ጠብቄአለሁ አለች

ተዋናይት እና አክቲቪስት ዊፒ ጎልድበርግ የተበላሸውን ዓለም ለመፈወስ ብሎም ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የተስፋ፣ የፍቅር እና የመደመር ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በምንጥርበት መንገድ መልካሙን ገድል የመዋጋት አስፈላጊነትን ትናገራለች።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

“ቫቲካን ንቦች አሏት?”
“ቫቲካን ንቦች ዬሏትም”
“ቫቲካን ንቦች ሊኖሯት ይገባል…”
ተዋናይት፣ አክቲቪስት እና ንብ አንቢ የሆነቿ ዊፒ ጎልድበርግ “በንብ አንቢነት ሥራ ተሰማርተህ ካለህ ንቦች በዓለም ዙሪያ እየሞቱ መሆናቸውን እንድታውቅ ትኩረት ይሰጥሃል” በማለት አፅንዖት ሰጥታ ትናገራለች።
“ምናልባት ለጳጳሱ አንዳንድ ንቦችን ልልክላቸው ይገባል” ስትልም ሐሳቧን ታቀርባለች።
ዊፒ ከላይ ያለቺውን ቃላት የተነፈሰችው ጥቅምት 1 2016 ዓ.ም. ሐሙስ ዕለት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ጋር ከተገናኝች በኋላ በማግስቱ በሊያ እና ማሪያና ቤልትራሚ የተዘጋጀውን የስዕል አውደ ርዕይ በጎበኝችበት ወቅት የንብ አንቢዎችን ፎቶ በትኩረት ካሰላሰለች በኋላ ነው።
“ለውጦች” በሚል ርዕስ የተሰየመው ኤግዚቢሽኑ የአየር ንብረት ለውጡ በእንስሳትና በሰዎች ላይ ያስከተለውን አስደናቂ ለውጥ እና በዚህም ድሆች እና አናሳዎች እንዴት እንደሚጎዱ ያሳያል።

ለ “አመሰግናለሁ” ወደ አሥራ አንድ ዓመት ገደማ

ዊፒ ጎልድበርግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለማግኘት ወደ አሥራ አንድ ዓመታት ያህል እንደጠበቀች ትናገራለች። በመጨረሻም ጥቅምት 1 2016 ዓ.ም. ዕለተ ሐሙስ ላይ ይህን ለማድረግ ቻለች ፥ ለረጅም ጊዜ በውስጧ ይዛው የነበሩትን ቃላት ተናግራለች። ቀላል ቃላት ፥ “አመሰግናለሁ” የሚል።
በቅድስት መንበር የጋዜጣዊ መግለጫ ጽ/ቤት የሚታዩት ፎቶዎች ሊያሳዩት የሞከሩት መልዕክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ “ለፍቅር እጦት እና ለፍላጎቱ ፣ ለመደመር እና ለመንከባከብ የመታገል አስፈላጊነትን” ለማሳየት አብዛኛውን የጵጵስና ጊዜያቸውን እንደሰው በደንብ ያስረዳል ብላለች።
ዊፒ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስን መልእክት እንደምትወዳት ደጋግማ በመግለጽ ፥ አንድ መሪ ለመልዕክቱ ድምፅ መስጠት እንዳለበት እንደምታምን ተናግራለች ፥ ብጹዕነታቸው ሁሉንም ሰው መውደድ እንዳለብን ነግረውናል ፥ አንድ መርሳት የሌለብን ነገር ‘ይቅር ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ የሚወሰን እንደሆነ እንጂ በኛ እንዳልሆነ ነው’ የተቀረው ነገር “በእውነቱ ከሆነ የአንተ ጉዳይ አይደለም” ብላለች።

የለውጥ ጊዜያት

‘እውነት ነው’ ትላለች ዊፒ ፥ ወጣት እያለች ር. ሊ. ጳጳሳት ዮሃንስ 23ኛ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም አንዳንድ አስፈላጊ ለውጦች እንዲደረጉ ግፊት አድርገው እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው ነው' ካለች በኋላ በጣም ታዋቂ ከሆኑት እ.አ.አ. በ 1992 ከተሰሩት የሆሊውድ ፊልሞች ውስጥ “ሲስተር አክት” እና “ጎስት” የሚሉት ላይ መሪ ተዋናይ ሆና የሰራችዋ ዊፒ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የአካታችነት መልእክት አድናቆቷን እንድትገልፅ አጓጉቷት እንደነበር ትገልፃለች።
“ለሰዎች ‘አምላክ እንደማይወዳቸው መንገርን አቁም’ ‘ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይመጡ መንገርህን አቁም’ የሚሉትን መልዕክቶች ለመናገር እርሳቸው የመጀመሪያው ሰው ናቸው” ስትል ፥ “አንዳንድ ሰዎች ትዳራቸውን ያፈርሳሉ ፣ ሌሎች ደግሞ ግብረ ሰዶማውያን ይሆናሉ ፥ አንተ በዚህ ላትስማማ ትችል ይሆናል ፥ ነገር ግን አምላክ ምንም ዓይነት ስህተት እንደማይሠራ ሁላችንም እናውቃለን” ብላለች።
በዊፒ አስተያየት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስስ “ሁሉም ሰው መልእክተኛ ሊሆን አይችልም ፥ ሁሉም ሰው ውጊያውን ለመዋጋት የቆረጠ አይደለም” በማለት ዓለምን ለመፈወስ የሚችል ትክክለኛ መልእክት እንዳላቸው ታምናለች። ሆኖም “ሁላችንም ስለ ጉዳዩ መነጋገር እንችላለን፥ ያ አንዳንድ ጊዜ ኢፍትሃዊነትን ለመዋጋት በጣም ጥሩው መሣሪያ ሊሆን ይችላል” በማለት አክላ ተናግራለች።

በግልጽ መነጋገር ስላሉብን ችግሮች

በቅድስት መንበር የመግለጫ ክፍል ውስጥ ስለሚታዩት ፎቶግራፎች ስትናገር የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ መልእክት በፎቶዎቹ ከተገለጸው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን በመግለፅ “ይህ ለሁሉም ሰው የተላለፈ መልዕክት ነው” ስትል ተናግራለች። “ሥዕሎቹ ችግር እንዳለብን ይነግሩናል ፥ እያንዳንዱ ችግር በግለሰብ ቦታ የሚደረጉ እና ግለሰባዊ ቢሆኑም ፥ ሁሉንም አንድ ላይ ስናዋህድ ዓለም አቀፋዊ ችግር ይሆናሉ ፥ እንዲሁ ስናያቸው ቁርጥራጭ እና የተነጣጠሉ ቢመስሉም ነገር ግን በእርግጥ የግዙፍ እና ትልቅ ምስል አካል ናቸው” ብላለች።
ከእንዲህ ዓይነቱ ኢፍትሃዊነትን መታገያ ማሳያ አንዱ የሆነው የሰውነት አካልን በመሸጥ በሚጠረጠሩ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው እንደተወሰዱ በተገመተው ሕፃናት በጠፉ ማግስት ማሪያ በብራዚል ውስጥ በፎቶ ግራፍ ያሳየችው አውደ ርዕይ አንዱ ነው።
“እሷ በ50 የተለያዩ ደረጃዎች እየተዋጋች ነው ፥ እኛም በሚቻለው መንገድ ሁሉ ከእሷ ጋር መዋጋት አለብን” ትላለች ዊፒ፣ “ይህን እያየን ነው፣ እያየንህም ነው፣ እናም ያየነውን ለሁሉም እንናገራለን” ብላለች።እንደ ዊፒ አመለካከት ለዚያም ነው “ፎቶዎችን ማንሳት፣ መላክ፣ በሁሉም ቦታ መላክ፣ ማስቀመጥ፣ በሁሉም ቦታ ማሳየት፣ በከተማችን ውስጥ ማሳየት ያለብን ፥ ምናልባት ሰዎች ምን እየተከሰተ እንዳለ አያውቁም ፥ ስለዚህም ደጋግመን መናገር አለብን” በማለት በአጽንኦት ትናገራለች።

መልእክተኞች በተለያየ መልክ ይመጣሉ

በታዋቂው “ሲስተርስ አክት” ፊልም ላይ እንደ መሪ ተዋናት በመተወኗ የመነኮሳትን ሚና በተመለከተ ከሲስተር ኒና ለቀረበላት ጥያቄ ዊፒ ስትመልስ “እሷም መልእክተኛ ነች” ትላለች ፤ ከ ‘ሲስተርስ አክት’ ፊልም በኋላ የጥሪ አገልግሎት እንዴት እንደጨመረ እና ያላትን ተፅዕኖ እንድትገነዘብ እንዴት እንደረዳት ተናግራለች። “አሁንም ድረስ በፊልሙ ውስጥ ያሉትን መዝሙሮች የሚዘምሩ መነኮሳትን በዓለም ዙሪያ ስዞር አግኝቻለሁ” ስትል የፊልሙን ተጽዕኖ ትናገራለች።
በዊፒ ህይወት ውስጥ ካሉት እህቶች አንዷ የሆኑት አስተማሪ እና የቅርብ ጓደኛዋ የነበሩት ሲስተር ዣን ፊልደር ሲሆኑ ፥ እሳቸውም እንደ ተዋናይዋ ገለጻ ሰዎች በዕለት ተዕለት ህይወታቸው የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች የሚያውቁ እና በእነሱም ተስፋ የማይቆርጡ ሰው ነበሩ።
“በ ‘ሲስተርርስ አክት’ ፊልም ውስጥ ሳየው የነበረው ነገር ያንን ነው” ካለች በኋላ “ለአገልግሎት ጥሪ የተጠራሁ መስሎኝ ነበር ፥ ነገር ግን አሁንም ጥሪው በእኔ ውስጥ እንዳለ እና የሆነ ቦታ እንደሚገኝ ይሰማኛል” ብላለች።

አንተ እና አንተ ብቻ

በመጨረሻም፥ እያንዳንዳችን እንዴት የተለየን እንደሆን እና ነገሮችን በተለየ መንገድ የመረዳት መብት እንዳለን በማሰላሰል ፥ ዊፒ ጥላቻን ከሚያቀጣጥሉት ከማግለል፣ ካለመቀበል እና ከማራቅ ይልቅ አካታችነት የፈውስ መንገድ እንደሆነ እንደሚሰማት ተናግራለች።
“‘አንተ አይደለህም’ ‘አንተ አልተመረጥክም’ ማለት በዓለም ላይ ጥላቻን የሚያቀጣጥል ሲሆን ፥ ትክክለኛው መልስ የሚሆነው ግን ‘አዎ እነርሱ ናቸው፣ እሱ ነው ፣ አዎ አንተ ተመርጠሃል’ የሚሉት ቃላት ፈዋሽ ናቸው” በማለት ደምድማለች።
 

14 October 2023, 12:36