ፈልግ

የተባበሩት መንግስታት ህንፃ የተባበሩት መንግስታት ህንፃ  (AFP or licensors)

የተ. መ. ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በዘላቂ ልማት እና በዓለም አቀፍ ትብብር ላይ እንደሚወያይ ተገለጸ

የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪን ጨምሮ የዓለም መሪዎች የጋራ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ለማሳሰብ እና በጣም አንገብጋቢ በሆኑ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መፍትሄዎችን ለመፈለግ ወደ ኒውዮርክ ያቀናሉ።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በኒውዮርክ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከ140 በላይ የሀገር መሪዎች እና መንግስታት እንደሚሳተፉ ተነግሯልነው። ስብሰባው “የ2030 አጀንዳን ለማሳካት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ እና 17ቱን የዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) ወደ ትክክለኛው መስመር የመመለስ አስፈላጊነት” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተዘጋጅቷል።

መተማመን እና ዓለም አቀፍ ትብብር

ዋናው ትኩረት የሚሆነው ከማክሰኞ መስከረም 8 -15 ዓ.ም. ድረስ የሚካሄደውን የከፍተኛ ደረጃ ‘አጠቃላይ ውይይት’ን ይመለከታል። በዚህም ሳቢያ “መተማመንን እንደገና መገንባት እና ዓለማቀፋዊ አንድነትን ማደስ ፥ በ2030 አጀንዳው ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ማፋጠን እና ዘላቂ ልማት ግቦቹ ለሁሉም ሰላም፣ ብልጽግና፣ እድገት እና ዘላቂነት” በሚል አርዕስት ሥር በሚደረግ ውይይት የዓለም መሪዎች ለቀጣዩ ዓመት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ለመገምገም እና መፍትሄዎችን ለመፈተሽ እድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በኒውዮርኩ ስብሰባ ላይ ከሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ አባላት መካከል ብቸኛው መሪ ይሆናሉ። ምክንያቱም የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ላለመሳተፍ ስለወሰኑ ነው።

በዩክሬን ሰላም እና ደህንነትን ማምጣት

የባለፈው ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ በርቀት የተሳተፉት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ዘንድሮ በተባበሩት መንግስታት ዋና መሥሪያ ቤት ረቡዕ ዕለት በፀጥታው ምክር ቤት በሚካሄደው የዩክሬን ልዩ ክርክር ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል። በዝግጅቱም ዜለንስኪ እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአንድ የስብሰባ አዳራሽ ተገኝተው “የተባበሩት መንግስታት ቻርተር ዓላማዎች እና መርሆዎች በውጤታማ እና ሁሉን አቀፍ ወገንተኝነት በማስከበር የዩክሬንን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ” በሚለው ጭብጥ ላይ ለመወያየት እድሉን ያገኛሉ ተብሏል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት በኒውዮርክ የሚደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በዋይት ሀውስ ሊነጋገሩ ቀጠሮ ተይዟል።

"ለትናንሽ ሀገራት እድል"

ባለፈው ሳምንት ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ‘ዲሞክራሲን ለመገደብ ሥልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎችን መዋጋት በጣም አስፈላጊ ነው’ ሲሉ የተናገሩት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ‘ትንንሽ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች ለጉባኤው እንዲያቀርቡ እና እድል እንዲሰጣቸው በጠቅላላ ጉባኤውላይ እንዴት መወከል እንዳለባቸው በገለጹበት ወቅት ነበር።
 

19 September 2023, 14:16