ፈልግ

በኦዴሳ ክልል የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ካደረሰ በኋላ በኦዴሳ ክልል የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ካደረሰ በኋላ 

የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ተፋፍሞ ባለበት ሠዓት አንድ የንግድ መርከብ ወደ ጥቁርባህር ማቅናቱ ተነገረ

ዩክሬን ወታደሮቿ በዶኔትስክ ግዛት የሩስያ ወታደሮች የሰፈሩበትን አከባቢ መልሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ ጦሯ በኡሮዝሃይን ዳርቻ ላይ መስፈሩን ተናግራለች። ይህ መግለጫ የወጣው ሩሲያ በጥቁር ባህር ላይ የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ ኢላማ ባደረገችበት እና የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ጥቃት እያደረሰች ባለበት በዚህ ወቅት አንዲት የንግድ መርከብ የዩክሬን ግዛት ከሆነችው የኦዴሳ ወደብ ለቃ መውጣቷ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የዩክሬን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ሃና ማሊያር የዩክሬን ወታደሮች በዶኔትስክ ክልል የሚገኘውን የኡሮዛይንን መንደር ፡ እንደ እርሳቸው አገላለፅ ‘‘ነጻ ማውጣታቸውን’’ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስታውቀዋል። ነገር ግን የሩስያ ወራሪ ሃይሎችን ለመከላከል የሚደረገው የመልሶ ማጥቃት አካል ሆኖ የማጥቃት ዘመቻው መቀጠሉን አክለው ተናግረዋል።
ቀደም ሲል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በደቡብ ምስራቅ የዛፖሪዝሂያንን ክልል በጎበኙበት ወቅት በሩሲያ ጦር ላይ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻው ላይ የሚሳተፉ ወታደሮችን አግኝተው አበረታተዋቸዋል።
ሆኖም የሩሲያ ጥቃቶች ተጠናክረው በመቀጠላቸው ምክንያት ኪየቭን ከባድ ጦርነት ገጥሟታል። የዩክሬን ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በዩክሬን ምዕራባዊ በሊቪቭ እና በሰሜን ምእራብ ቮልይን ክልል ላይ በደረሰ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶችም መቁሰላቸውን ገልፀዋል።
የሊቪቭ ከንቲባ የሆኑት አንድሪይ ሳፎቪይ እንደተናገሩት “ብዙ ሚሳኤሎች ተመትተው ወድቀዋል” ብለዋል ፥ ነገር ግን በከተማቸው ውስጥ ጥቃት የደረሰባቸው ቦታውች እንዳሉም አምነዋል። ቢያንስ አንድ ጥቃት ደርሶበት በእሳት እየጋየ የነበር የመኖሪያ ሕንፃን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ መሰጠቱንም አክለው ተናግረዋል።
ጦርነቱ የተፈጸመው የሩሲያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እና የእስያ፣ የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ አጋር ሀገራት ስለፀጥታው ጉዳይ ከሞስኮ ከተማ ውጭ ከመሰብሰባቸው ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ ነው።
እሮብ ዕለት የዩክሬን አየር ሃይል እንዳስታወቀው በርካታ የሩስያ ጦር ድሮኖች በዳኑቤ ወንዝ አቅጣጫ አድርገው ወደ የምእራብ ኔቶ ወታደራዊ ህብረት አባል ከሆነችው ሮማኒያ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ ኢዝሜል ወንዝ ዳርቻ ማቅናታቸውን ተናግረዋል።

በመጠለያ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች

የደቡባዊ ኦዴሳ ክልል ገዥ የሆኑት ኦሌህ ኪፐር የኢዝሜል አውራጃ ነዋሪዎች ከድሮን ጥቃቶቹ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አስጠንቅቀዋል ፥ ነገር ግን ከአንድ ሰዓት በኋላ የአየር ጥቃቱን ማስጠንቀቂያ ሰርዘዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ሩስያ ወደቦች ላይ ቀጣይነት ያለው ጥቃት እያደረሰች ባለበት እና በጥቁር ባህር ላይ የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ ዒላማ ማድረግ ትችላለች ተብሎ ስጋቱ ባየለበት በአሁኑ ወቅት አንድ የንግድ መርከብ ረቡዕ ዕለት ከዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ለቃ መውጣቷ ተነግሯል።
ኪየቭ ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ባለፈው ወር በመፍረሱ ምክንያት በጥቁር ባህር ላይ "የሰብአዊነት ኮሪደር" የሚባል መተላለፊያ መጠቀም እንደምትጀምር ማስታወቋ ይታወቃል።
 

17 August 2023, 11:50