ፈልግ

አንድ ነዋሪ በኢን አል-ሄልዌህ በተከሰተ ግጭት ምክንያት የተዘጉ ሱቆችን አልፎ ሲሄድ አንድ ነዋሪ በኢን አል-ሄልዌህ በተከሰተ ግጭት ምክንያት የተዘጉ ሱቆችን አልፎ ሲሄድ  (AFP or licensors)

በሊባኖስ ኢን ኤል ሂልዌህ በሚባለው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በተፈጠረ ግጭት የሟቾች ቁጥር ጨምሯል።

በኢን ኤል-ሂልዌህ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በፍልስጤም አንጃዎች መካከል የተከሰተው ግጭት እየተባባሰ ሲሄድ ፥ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ የተደረገው ሙከራ ግን አልተሳካም። ብጥብጡ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ፥ ትምህርት ቤቶችም በግዳጅ ተዘግተዋል ፤ ግጭቱ እንዲቆምም የአስተዳደር ኮሚቴው አሳስቧል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ባለፉት ሶስት ቀናት በሊባኖስ ኢን ኤል ሂልዌህ ካምፕ በተፈጠረው ግጭት የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ቢያንስ ሁለት ህጻናት ቆስለዋል።
ወደ 80,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ስደተኞችን ፣ ሶሪያውያንን ፣ ሊባኖሳውያን እና ፍልሰተኞችን በያዘው በዚህ ካምፕ የተከሰተው ግጭት ተባብሶ ከፍተኛ ውድመት ያደረሰ ሲሆን ፥ ይህም ህጻናትን ለአካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ቀጥተኛ ተጋላጭ እንዳደረገ ሴቭ ዘ ችልድረን የተባለው ህፃናት አድን ድርጅት ዘግቧል።
ግጭቱ የዕለት ተዕለት ኑሮውን በማስተጓጎሉ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አስገድዷቸዋል ፥ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የአንዳንድ ነዋሪዎች ህንጻዎች በበራሪ ጥይቶች በመመታታቸው እና ለህይወታቸው በመስጋታቸው ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል።
የህፃናት አድን ድርጅቱ ለተጎዱ ቤተሰቦች እርዳታ ያደረገ ሲሆን ፥ የመጠለያ ቁሳቁሶችን ፣ ነዳጅ እና ብርድ ልብሶችን በማከፋፈል ከብርድ እንዲታደጉ እየሰራ ይገኛል።
በተጨማሪም የንፅህና ቁሳቁሶችን እና የምግብ ማብሰያ የመሳሰሉ አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ የአካባቢ ባለስልጣናትን የንፅህና አጠባበቅ ፕሮጀክቶችን በመተግበር እየደገፈ ይገኛል።

ሁከትን ለማስቆም የተደረጉ ሙከራዎች

የፍልስጤም ወታደራዊ ጄኔራል እና ሶስት አጃቢዎች መገደላቸውን ተከትሎ የተጀመረው ግጭት ፥ በፍልስጤማዊያን አንጃዎች መሃል ማለትም በፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ፋታህ ፓርቲ አባላት እና እስላማዊ ቡድኖች መካከል የተደረገ ግጭት ነው።
አንድ የሊባኖስ ህግ አውጪ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጉን ያስታወቀ ቢሆንም ፥ የማይቋረጠው የተኩስ ልውውጡ የተኩስ ስምምነቱ አፍርሷል። ካምፑን የሚመራው የታዋቂ ኮሚቴ አባል የሆኑት አድናን ሪፋይ እንዳሉት “የሊባኖስ ፓርቲዎች እና የተወሰኑ የፍልስጤም አንጃዎች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ቢጥሩም ፥ በካምፑ ውስጥ የሚካሄደው ተኩስ እና ፍንዳታዎች ያለማቋረጥ ቀጥሏል” ብለዋል።
የሊባኖሱ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ናጂብ ሚካቲ እና ፕሬዝዳንት አባስ ሁከቱን ያወገዙ ሲሆን ፥ ባለስልጣናት በካምፑ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት በንቃት መፍትሄዎችን እንዲያፈላልጉም አሳስበዋል።
ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ባለሥልጣናቱ “በካምፑ ውስጥ ለተከሰተው ግጭት የተለየ ፣ ውጤታማ ፣ ዘላቂ እና የተረጋጋ መፍትሄዎችን ለማግኘት ልዩ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል።
የፕረዚዳንት ፋታህ መግለጫ የጸጥታ ባለሥልጣኑን ግድያ በማውገዝ ፥ የካምፖቻችንን ደህንነት እና መረጋጋት ላይ ያነጣጠረ የደም ማፋሰሻ ዘዴ አካል አድርጎታል። በማከልም “ወንጀለኞች በህግ እንደሚጠየቁ” ቃል ገብቷል።
ለተፈጠረው ግጭት ምላሽ ተቀናቃኙ የሐማስ አንጃ ሰኞ ዕለት ጦርነቱን በማውገዝ የራሱን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፥ ‘የሕዝባችንን ደም ለመታደግ እና ሕዝባዊ ሠላምን ለማስጠበቅ’ ውይይት እንዲደረግም አሳስቧል።
ሃማስ በማስከተልም ለግጭቱ ሃላፊነት የሚወስድ እና የግጭቱ መንስኤ የሚያጣራ አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ጠይቋል።
 

02 August 2023, 16:28