ፈልግ

'የሴቶች እንባ' የተሰኘ አውደ ርዕይ 'የሴቶች እንባ' የተሰኘ አውደ ርዕይ 

የተሻለ ማህበረሰብ ለመገንባት ሴቶች ያላቸውን ድርሻ የሚያሳይ የሥዕል አውደ ርዕይ ቀረበ

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 6,000 ያህል ሴቶች የበለጠ የተቀናጀ አካባቢን ለመፍጠር በሚሰራው ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ በሩዋንዳ ኪጋሊ ሲሰባሰቡ ፥ ሊያ ቤልትራሚ የተባሉ ሁለገብ አርቲስት በቅድስት መንበር የግንኙነት ቢሮ የሚደገፉ ስራዎቻቸውን አቅርበው የግንኙነት እና የተግባቦትን አስፈላጊነት አጉልተው አሳይተዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ይህ የዘንድሮው ዓመት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከ6,000 በላይ ሴቶችን በኪጋሊ ሩዋንዳ ከኃምሌ 10 – 13 2015 ዓ.ም. አንድ ላይ አሰባስቧል።

ውይይቶች እና ሃሳብን ማጋራት

ጉባኤው የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማስተዋወቅ በየሶስት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን በአፍሪካ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ትልቅ ዘርፈ ብዙ ስብሰባዎች ውስጥ አንዱ ነው።
ስብሰባው በሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች ፣ በመንግስታት ፣ በግለሰቦች ፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ፣ የወጣት ቡድኖች እና አድሎአዊ ሥርዓት ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች የተደራጁ ውይይቶች የተደረጉበት እና ምርጥ ተሞክሮዎችን የተካፈሉበትም ነው ተብሏል።
ፕሮግራሙ ከጤና ጉድዮች እስከ ምጣኔ ሃብት ፣ ከትምህርት እስከ ጥበብ ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች በአካል እና በኦንላይን ውይይቶችን አቅርቧል።
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሩዋንዳ ፣ የሴኔጋል ፣ የኢትዮጵያ ፣ የጊኒ ፕሬዝዳንቶች እና የኔልሰን ማንዴላ ሶስተኛ ሚስት የሆኑት ግራካ ማሼል ተገኝተዋል።

“የእርስ በእርስ ግንኙነት ማድረግ ቁልፍ ጉዳይ ነው”

የፊልም አዘጋጅ እና የስነ ጥበብ ዳይሬክተር የሆኑት ሊያ ቤልትራሚ የዓለም የካቶሊክ የሴቶች ድርጅቶች ማህበር (WUCWO) ተነሳሽነት የተመሰረተው የዓለም የሴቶች ኦብዘርቫቶሪን በመወከል ተሳትፈዋል።ወ/ሮ ሊያ ’የሴቶች ለቅሶ’(Women’s Cry) የተባለው አውደ ርዕይ አዘጋጅ እንዲሁም ‘የማይታዩት’ (In-Visibles) የተባለው ዘጋቢ ፊልምም ደራሲ ሲሆኑ እነዚህ ሁለቱ ፕሮጄክቶች በቫቲካን የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ዲካስተሪ (የቫቲካን ዜና እናት ድርጅት) ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው።
ዓለም አቀፍ ፋውንዴሽኖች እና የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች መገኘታቸውን እንዲሁም በሩዋንዳ በሴቶች የተከናወኑ ጅማሮዎች መኖራቸውን ያስረዱት ወይዘሮ ቤልትራሚ “የእርስ በእርስ ግንኙነት ዋናው ነገር ነው” ብለዋል።
“በሴቶች አማካኝነት ከጦርነት ጠባሳ ማገገምን ጨምሮ የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን እንሰራለን”

የሴቶች ለቅሶ

ወይዘሮ ቤልትራሚ ትኩረታቸውን የእሳቸው ዝግጅት በሆነው በ ‘ሴቶች ለቅሶ’ ተብሎ የተሰየመ ኤግዚቢሽን ላይ ያተኮሩ ሲሆን ይህም አውደ ርዕይ ‘የሰውን ልብ በሥነ ጥበብ’ ለመንካት ዓላማው ያደረገ “ስሜት ለውጥን ለመፍጠር” የተሰኘ ትልቁ ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው።
በአውደ ርዕዩ ላይ የቀረቡት 26ቱ ፎቶዎች የጉልበት ሥራን እና እናትነት እስከ የአካባቢ ጉዳዮች ድረስ ያሉትን ጭብጦች የሚያሳዩ ሲሆን ፥ ሁሉም ስዕሎች የር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ ጥብቅ ደብዳቤ ከሆነው ፍራቴሊ ቱቲ ጥቅስ ጋር ተያይዘዋል።
“ሁሉም ነገር በኦንላይን ሆኖ በነበረው ከዓመታት በኋላ ፥ ከሁሉም የዓለም ማዕዘናት የተውጣጡ ብዙ ሴቶች ጋር በአካል መገናኘት በጣም አስደሳች ነገር ነው” ሲሉ ወይዘሮ ቤልትራሚ የተናገሩ ሲሆን “ለሁሉም የሚስማማ አስተሳሰብ የለም ፥ ይልቁንም ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ አለ” በማለትም አክለዋል።
በተጨማሪም ‘የሴቶች ለቅሶ’ በWD2023 የተባለው የኪነጥበብ እና የፊልም ፌስቲቫል ላይ ከ140 ስራዎች ጋር ተወዳድሮ የፍጻሜ እጩ ሆኖ እንዲመረጥ ያስቻለው በአውደ ርዕዩ በኩል ‘የላቀ እይታ’ ያለው የካቶሊኩ ዓለም አስተሳሰብ የመካተቱን አስፈላጊነት ገልጸዋል።

‘የማይታዩት’ (In-Visibles)

አርቲስቷ ቀደም ሲል በስቶክሆልም ፊልም ፌስቲቫል እና በሞንቴ ካርሎ የበጎ አድራጎት ፊልም ፌስቲቫል የተሸለመውን እና በሌሎች ስድስት ፌስቲቫሎች ላይ እንዲታይ የተመረጠው ኢን-ቪስብልስ ስለ ተሰኘው የፊልም ፕሮጄክታቸው አንስተዋል ።
“ይህ ማለት እነዚህ የማይታዩ ሴቶች ከአሁን በኋላ የማይታዩ አይደሉም ማለት ነው” ሲሉ ወ/ሮ ቤልትራሚ አክለውም የሴቶች ሁኔታ አሁንም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ በሚገኝበት ለሌሎች እውነታዎች ማበረታቻ የሚሆኑ ተሞክሮዎችን በመሸከም አፍሪካ በእንደዚህ አይነት አስደናቂ መስቀለኛ መንገድ ሴቶችን ማስተናገድ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስን ጥሪ በማስታወስ ይህች አፍሪካ ልትረሳ አይገባም ብለዋል።
ወይዘሮ ቤልትራሚ እንዳሉት የቀረበው ጥሪ ጥሩ ተቀባይነት አግኝቷል። “ከዚህ ቀደም በኮንጎ እና በደቡብ ሱዳን ሊቃነ ጳጳሳቱን ለማግኘት የሄዱ ሴቶችን እዚህ አግኝቻለሁ። ብጹዕነታቸው 'ድምፃቸው ለሁሉም ብርሃን ነውና' ብዙ ካቶሊኮች ያልሆኑም ጭምር የእሳቸውን ድምጽ ለመስማት እንደሄዱ ነግረውኛል” ብለዋል።
 

21 July 2023, 14:58