ፈልግ

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በድርቅ የተጎዱ የቱርካና ማህበረሰብ አባላት ኬንያ ከሶማሊያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በድርቅ የተጎዱ የቱርካና ማህበረሰብ አባላት  (AFP or licensors)

ሽብርተኝነት የኬንያ-ሶማሊያ ድንበር መከፈትን አዘገየ ተባለ

ኬንያ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ላይ ጥፋተኛ ብላ በሰነዘረችው የጥቃት ማዕበል ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ድንበሯን እንደገና የመክፈቱን ጉዳይ እንደምታዘገይ ገልፃለች።

   አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ኬንያ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው ታጣቂዎች ላይ ጥፋተኛ ብላ በሰነዘረችው የጥቃት ማዕበል ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ድንበሯን እንደገና ለመክፈት አልፈቀደችም።
በግንቦት ወር ሁለቱ መንግስታት የድንበሩን የተወሰኑ ክፍሎች በ90 ቀናት ውስጥ ለመክፈት ዝግጅት አድርገው ነበር።
ኬንያ ከአልቃይዳ ጋር የተያያዘውን የአልሸባብ አክራሪ ቡድን ለመዋጋት ጦሯን ወደ ደቡብ ሶማሊያ ካሰማራችበት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ማቋረጫዎች ተዘግተዋል።

ጽንፈኛ ዓመፅ

ይሁን እንጂ ከግንቦት ወር ጀምሮ ብጥብጡ የበረታ ሲሆን በቅርቡ ከ12 በላይ ሰዎች በጋራ ድንበሮቻቸው አከባቢ ተገድለዋል።
ይህ ማለት በማንዴራ ፣ ላሙ እና ጋሪሳ የድንበር ማቋረጫ ጣቢያዎች ዝግ ሆነው ይቆያሉ ማለት ነው።
የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኪቱሬ ክንዲኪ እንዳሉት “የኬንያ-ሶማሊያ የድንበር አከባቢዎችን ለመክፈት የታቀዱት ዕቅዶች የሽብር ጥቃቶች እና ድንበር ዘለል ወንጀሎችን መንግስት በፍፁምነት ወደ ዘላቂ መፍትሄ እስከሚያመጣው ድረስ ክፍት ከማድረግ ያዘገያል” ብለዋል።
ተንታኞች እንደሚሉት የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ኬንያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮ እንድታወጣ ጫና ለማድረግ እንደሆነ ይናገራሉ።

የተስፋፋ ስቃይ

በኬንያ ምድር ላይ ከተፈጸሙት አስከፊ ጥቃቶች መካከል በ2007 ዓ.ም. በኬንያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተካሄደው ጭፍጨፋ 148 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ሶማሊያ ከአርባ ዓመታት በኋላ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ገጥሟታል።
በዚህ ምክንያት ቢያንስ 6.5 ሚሊዮን ሰዎች ወይም 40% የሚጠጋው ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
 

07 July 2023, 15:37