ፈልግ

ስደተኞች ኤስፋክስ (Sfax) በተባለው ስፍራ ስደተኞች ኤስፋክስ (Sfax) በተባለው ስፍራ   (ANSA)

የሊቢያ ድንበር ጠባቂዎች በረሃ ውስጥ የተጣሉ ስደተኞችን አዳኑ

በቱኒዚያ ባለስልጣናት ያለ ውሃ ፣ ምግብ እና መጠለያ በበረሃ የተጣሉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ስደተኞች ጉዳይ ብዙዎችን የዓለም ማህበረሰብን አስደንግጧል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሰሞኑን ዓለም የሊቢያ ፖሊሶች በቱኒዝያ ባለስልጣናት በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በረሃ ውስጥ ያለ ውሃ፣ ምግብና መጠለያ የተጣሉትን በደርዘን የሚቆጠሩ ስደተኞችን ሲታደጉ የሚያሳይ ምስል አይቷል። ቪዲዮው ቢያንስ 80 እጅግ በጣም የተጎዱ ወጣት ወንዶች እና ጥቂት ሴቶች ቡድኖችን አሳይቷል። ምስሉ እንደሚያሳየው ሁሉም በውሃ ጥም የተዳከሙት ስደተኞቹ አሸዋ ላይ ተቀምጠው ከ 40 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ ከሆነው የሙቀት መጠን ለመጠለል ሲሞክሩ ይታያል ።
የስደተኞቹ ችግር የተከሰተው ሰኔ 26 2015 ዓ.ም. በቱኒዚያ በተከሰተ ግጭት የአንድ ቱኒዚያዊ ህይወትን ከቀጠፈ በኋላ እና በመቶ የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ‘ስፋክስ’ (Sfax) ተብሎ ከሚታወቀውና ስደተኞች ወደ አውሮፓ ህብረት በህገ ወጥ መንገድ ከሚሰደዱበት ቦታ ከተባረሩ በኋላ ነው።
እንደ አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ገለጻ ከሆነ እነዚህ ስደተኞች በቱኒዚያ ፖሊሶች እየተመሩ ወደዚህ በምስራቅ ሊቢያ እና በምዕራብ አልጄሪያ አቅራቢያ በሚገኝ በረሃማ አካባቢ ነበር የተጣሉት።
ስደተኞቹ እዚህ ስፍራ ላይ ከተገኙ በኋላ የሊቢያ ድንበር ጠባቂዎች ውሃ ሰጥተዋቸው ወደ መጠለያ ቦታ ወሰደዋቸዋል።

የአውሮፓ ህብረት ቱኒዚያ ስደትን ለመግታት ስምምነት ላይ ደርሳለች ብሏል

የሚገርመው ነገር ድርጊቱ የተከሰተው የአውሮፓ ህብረት ከቱኒዚያ ጋር የንግድ ግንኙነቱን ለማሳደግ እና ከሀገሪቱ የሚነሱትን ስደተኞች ለመግታት ስምምነት ላይ ደርሳ ከጨረሰች በኋላ መሆኑ ነው።
በስምምነቱ መሰረት ብራሰልስ ለቱኒዝ ጠንካራ የድንበር ቁጥጥር ለማድረግ የሚያግዝ ገንዘብ ትሰጣለች።
በዚህም መሰረት የአውሮጳ ኅብረት ለቱኒዚያ የድንበር አስተዳደርን ለማሻሻል ፣ የቁጥጥር እና የማዳን ሥራ እንዲሁም ሌሎች የስደትን ጉዳዮችን ለመቅረፍ 100 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ያደርጋል።
 

25 July 2023, 07:36