ፈልግ

በሊባኖስ ምስራቃዊ ክፍል ውስጥ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ የምትገኝ አንዲት ወጣት ሶሪያዊት በሊባኖስ ምስራቃዊ ክፍል ውስጥ በስደተኞች ካምፕ ውስጥ የምትገኝ አንዲት ወጣት ሶሪያዊት  (AFP or licensors)

ሊባኖስ፡ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮችን የመግዛት አቅም ዬላቸውም ተባለ

የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ፈንድ ድርጅት (UNICEF) ሰሞኑን ባወጣው አዲስ ሪፖርት ሊባኖስ ውስጥ ካሉ አጠቃላይ ህጻናት ወደ አንድ ሶስተኛው የሚጠጉት ለረሃብ የተጋለጡ ወይም የዕለት ጉርስ የማያገኙ መሆናቸውን ያሳያል።

   አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ (ዩኒሴፍ አዲስ) የተለቀቀው ይህ ሪፖርት እንደሚያሳየው በሃገሪቱ ላይ እየተከሰተ ያለው የገንዘብ ቀውስ ወደፊት በህፃናት ልጆቿ ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ያመላክታል።
ቢያንስ አንድ ልጅ ያሏቸው 2,090 ቤተሰቦች ላይ በተሠራው የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት መሰረት አንድ ሦስተኛ የሚጠጉ የሊባኖስ ልጆች በቂ ምግብ እንደሌላቸው ይጠቀሳል።

አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለመግዛት መታገል

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ከ10 የሊባኖስ ቤተሰቦች ውስጥ ወደ 9 የሚጠጉ (86 በመቶው) አስፈላጊ እቃዎችን መግዛት አይችሉም ፥ ይህም ከዓመት በፊት ከነበረው 76 በመቶ ከፍ ማለቱን ያሳያል።
አንድ ሶስተኛ የሚጠጉ (30 በመቶ) ቤተሰቦች ቢያንስ ከልጆቻቸው ዉስጥ አንዱ ተርቦ እንደሚተኛ ሲናገሩ ፥ ግማሾቹ ሴቶች እና ልጃገረዶች (51 በመቶ) የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች በቂ አቅርቦት እንደሌላቸው ይናገራሉ። ሶስት አራተኛ (75 በመቶው) ለልጆቻቸው ጤና አጠባበቅ የሚውል ወጪን እንደቀነሱ ሲናገሩ አስራ አምስት በመቶው ደግሞ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ሙሉ በሙሉ አቁመዋል።
ከዚህም በላይ ከ10 ቤተሰቦች ውስጥ ከ1 በላይ የሚሆኑት ልጆቻቸውን ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ወደ ሥራ እንደሚልኩ ሪፖርት አድርገዋል። ይህ አሃዝ ባለፈው ዓመት ከነበረው 21 በመቶ በሶሪያ ስደተኞች መካከል ከሩብ በላይ በ28 በመቶ ከፍ ብሏል።

የአእምሮ ጤና ቀውስ

66 በመቶ የሚሆኑት አሳዳጊዎች ስለ ልጆቻቸው እንደተናገሩት ልጆቻቸው በሁኔታዎች ተሸብሯል ፣ አሊያም ተጨንቀዋል ወይም ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳሉ ነው የተናገሩት። እንዲሁም ግማሽ ያህሉ (47 በመቶ) የሚሆኑት ልጆቻቸው በጣም እንደሚያዝኑ ወይም በየሳምንቱ እንደሚጨነቁ ይናገራሉ። 62 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የልጆቻቸው ደህንነት ከባለፈው ዓመት አሁን በጣም ቀንሷል ይላሉ።
በቤተሰብ መካከል የነበረው ጥሩ ግንኙነትም እየቀነሰ መምጣቱ ነው የተነገረው። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሳዳጊዎች (53 በመቶው) አሁን ያለው ችግር ልጆቻቸውን ትዕግስት አልባ እንዳደረጋቸው እና ይህም ከልጆቹ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አስቸጋሪ እንዳደረገው ይናገራሉ።

ምክሮች

የዩኒሴፍ ዘገባ አሁን ያለው ሁኔታ በህፃናት ህይወት ላይ አስደናቂ ፣ የማይቀለበስ እና የረዥም ጊዜ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን በመጥቀስ ፥ የሊባኖስ መንግስት ፈጣን እና ቁርጥ ያለ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል።
በአሁኑ ጊዜ 700,000 ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸውን አጽንኦት የሰጠው ሪፖርቱ “የመንግስት እርምጃ ትምህርት ላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት” ብሏል።
የሊባኖስ መንግስት በቅርቡ የጀመረውን የብሄራዊ ማህበራዊ ጥበቃ ስትራቴጂን ሪፖርቱ እያበረታታ ፥ ብሄራዊ የህፃናት ድጋፍ እንዲደረግ እና መንግስት በሀገር ውስጥ እየጨመረ ከመጣው የታክስ ገቢዎች ላይ ለማህበራዊ ፕሮግራሞች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ጠንካራ ቁርጠኝነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርቧል።

ሊባኖስ፡ የወንድማማችነት ምልክት

የቅድስት መንበር ለሊባኖስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ደጋግማ ገልጻለች ፥ ሊባኖስ በመካከለኛው ምሥራቅ ካሉት ሃገራት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የክርስትና እምነት ተከታዮች ያላት ሀገር ስትሆን ፥ ብዙ ጊዜ የተለያዩ እምነት ያላቸው ሰዎች በፍቅር አብረው የሚኖሩባት ከተማ በመባል ሞዴል ተደርጋ የምትወሰድም ሃገር ናት።
ከካቶሊክ ሊቃነ ጳጳሳት መሃል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ አገሪቷን የጎበኙ ሲሆን ፥ ምንም እንኳን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እ.አ.አ. በ 2021 በጤና ችግሮች ምክንያት ወደ ሊባኖስ ሊያደርጉት የነበረውን ሃዋሪያዊ ጉዞ እንዳያደርጉ ቢከለከሉም ፥ የሊባኖሱን ፕሬዚደንት በሮም ተቀብለው የቤተክርስቲያኒቷ ከፍተኛ መገለጫ የሆነውን የጸሎት ጉባኤ አዘጋጅተው አስተናግደዋቸዋል።
እ.አ.አ. በ1989 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጆን ፖል ዳግማዊ ሊባኖስን “ከሀገር በላይ ናት ፥ የነጻነት ተምሳሌት እንዲሁም ለምስራቃዊያን እና ለምዕራባውያን የብዝሃነት ምሳሌ ናት” በማለት በታዋቂነት አውጀዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስም ይህንኑ ሀሳባቸውን በማስተጋባት ፥ አሁን እየደረሰ ባለው ቀውስ ሊባኖስ ማንነቷን እንዳታጣ እንዲሁም ለመላው ዓለም በወንድማማችነት የመኖር ተምሳሌትነቷን እንዳያሳጣት ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
 

22 June 2023, 14:23