ፈልግ

የደቡብ አፍሪካ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እየሄዱ የደቡብ አፍሪካ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እየሄዱ 

በዓለም አቀፉ የአፍሪካ ህፃናት ቀን ‘የዛሬ ወጣቶች የነገ መሪዎች ናቸው’ ተባለ

ዓለም አቀፉ የአፍሪካ ህጻናት ቀን በየዓመቱ ሰኔ 9 የሚከበር ሲሆን ፥ ይህም እ.አ.አ. በ1991 እንደተጀመረ እና አላማውም የአፍሪካን ልጆች ለመዘከር እና መብቶቻቸውን ለማስጥበቅ እንዲሁም በየዕለቱ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እንዲያስቡ እና እንዲሰሩ ለማበረታታትም ጭምር ነው።የዘንድሮው አከባበር ለዓለም ትልቅ ለውጥ መምጣቱን ያሳያል ተብሏል።

አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
የዘንድሮው የዓለም አቀፍ የአፍሪካ ህጻናት ቀን ሲከበር መሪ ቃሉን “የህፃናት መብቶች በዲጂታሉ ዓለም” በሚል ሲሆን ፥ ይህን በዲጂታል አብዮት የተፈጠረውን የዘመን ለውጥ ማየቱ በግልፅ ጠቃሚ ነው።
ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ቴክኖሎጂ እና ጊዜዎች ቢለዋወጡም አሁንም ድረስ በጣም ብዙ የአፍሪካ ህጻናት መሰረታዊ የሰብአዊ መብት እያገኙ አይደለም። ይህ የሰብዓዊ መብት እጦት ነው እ.አ.አ. ሰኔ 16 ቀን 1976 በሶዌቶ የሚገኙ ወጣት ደቡብ አፍሪካውያን ተማሪዎች በትምህርት ላይ የሚደርሰውን ኢፍትሃዊነት እና የአፓርታይድ አገዛዝ እኩልነት እንዲቃወሙ ያደረጋቸው እና መጨረሻም አድፍጠው በጠበቋቸው የፀጥታ አካላት ግድያ እና ጭፍጨፋ የተካሄደባቸው። በመሆኑም ይህ ቀን እነዚያን ተማሪዎች ለመዘከር ነበር የተመረጠው ፥ ነገር ግን መከበር ከጀመረ ሃምሳ ዓመታት ቢያስቆጥርም አሁንም ድረስ 244 ሚሊዮን የሚጠጉ ዕድሜያቸው ከ6 - 18 የሚሆኑ ሴት እና ወንድ ልጆች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከትምህርት ውጭ ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጉት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ይገኛሉ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በበኩላቸው መስከረም 2012 ዓ.ም. በጀመሩት እና በዓለም አቀፉ የትምህርት ስምምነት ላይ የተመረኮዘውን የአፍሪካ የትምህርት ስምምነት (African Compact on Education) ድጋፍ እና ማበረታቻቸውን በመግለጽ ይህን ወሳኝ ጉዳይ ደጋግመው አንስተዋል።
ይህ ደግሞ ህፃናትን እና ወጣቶችን አርኪ ህይወት እንዲገነቡ በማበረታታት ላይ ብቻ ማተኮር ሳይሆን ትምህርት ወሳኝ እንደሆነ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ስላለው ነው። በተጨማሪም ወንድማማችነትን በማስተማር መለያየትን እና ግጭቶችን እንዲያሸንፉ እና አገሮቻቸውን በእንግዳ ተቀባይነት ፣ በፍትህ እና በሠላም ጎዳና እንዲመሩ ያስተምራቸዋል።

ልጆች ላይ ያለን የጋራ ሀላፊነት

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እ.አ.አ. በ1991 ዓለም አቀፉን ቀን ሲያቋቁም “ሕፃናትን የሚጎዱ ጎጂ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ፡ የጋራ ኃላፊነታችንን እንወጣ” ብሎ በገባው ቃል መሠረት አድርጎታል።
የአፍሪካ ህጻናት ቀን ግንዛቤ ማስጨበጡን ቢቀጥልም ፥ ልጆችን ለውትድርና መመልመል ፣ የሴቶች ግርዛት ፣ የምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ ፣ የትምህርት እጦት መስፋፋት እና የመሳሰሉት ችግሮች አሁንም ቀጥለዋል። እ.አ.አ. በ2050 ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ የዓለም ህጻናት መካከል ከሶስቱ አንዱ ማለት ይቻላል አፍሪካዊ ይሆናል ተብሎም ተነግሯል ፥ ይህም ከተሰራበት ለአፍሪካ ትልቅ ዕድልን ይዞ ይመጣል ፥ የበዓሉ አከበበርም ላይ ብርሃንን ይፈነጥቃል።

የዘመናት ለውጥ

በመሆኑም በዚህ ዓመት ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ዓለምን በወጣቶች ብዛት የሚመሩበት ዓመት ሊሆን ስለሚችል ይህ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ህጻናት ቀን እስካሁን ከተከበሩት ሁሉ የላቀ ነው ሊባል ይችላል።
የዚህ ለውጥ አስፈላጊነት ላይ ለሚቀርበው ጥያቄ ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ምላሹ የሚመረኮዘው መሪዎቹ ይህን ትልቅ እድልን በእጃቸው ለማስገባት ወይም የተገኘውን አጋጣሚ እንዳይጠቀሙ የሚያደርገው በሚወስዱት እርምጃ ወይም እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተ ነው።
ኔልሰን ማንዴላ እንደተናገሩት “የዛሬ ወጣቶች የነገ መሪዎች ናቸው” ፥ ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ አጋሮቿ እነዚህ ቃላት ከመቼውም ጊዜ በላይ በተስፋ እና ፈታኝ ሁኔታዎች ያስተጋባሉ።
 

19 June 2023, 16:05