ፈልግ

ከጀልባ አደጋው የተረፉት ሰዎች በማላካሳ ካምፕ ውስጥ ከዘመዶቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር ሲገናኙ ከጀልባ አደጋው የተረፉት ሰዎች በማላካሳ ካምፕ ውስጥ ከዘመዶቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር ሲገናኙ 

በጀልባ መስጠም ምክንያት በጥርጣሬ የተያዙ የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ጥፋተኛ አይደለንም አሉ

ባለፈው ሳምንት በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ በመስጠሟ ምክንያት በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ዘጥኝ ተጠርጣሪዎች በግሪክ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ ክደው ተከራክረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ለተጎጂዎች የተሰማቸውን ሃዘን ደጋግመው በመግለጽ ፥ ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን ለመጠበቅ ፖለቲካዊ እርምጃ እንዲወሰድም ጠይቀዋል።

   አዘጋጅ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በፈጣን የፍርድ ቤት ውሎ ዘጠኙ ሰዎች በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ ክደዋል። ሁሉም ተጠርጣሪዎች ግብፃውያን ሲሆኑ ፥ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉትም ከአደጋው በህይወት የተረፉ ሰዎች ባደረሱት ጥቆማ እነዚህ ሰዎች መርከቧን ሲመሩ ፣ በጀልባው ላይ ትዕዛዝ ሲሰጡ እና ከግሪክ የባህር ዳርቻ ጥበቃ ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ እንደነበር ከገለጹ በኋላ ነው።
በአደጋው ሰባ ስምንት ሰዎች እንደሞቱ ቢታሰብም ከዚህም በተጨማሪ እስካሁን ያልተገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰጥመው ሞተዋል ተብሎ ተሰግቷል።
ቀደም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከ 750 ተሳፋሪዎች 500 የሚደርሱ ሰዎች መጥፋታቸውን ገልጿል ፥ ከ750ዎቹ መንገደኞች አብዛኛዎቹ ከግብፅ፣ሶሪያ እና ፓኪስታን የመጡ እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል።
ተጨማሪ መረጃ እየተገኘ በመጣ ቁጥር 'የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች በጀልባው ላይ የሚገኙትን የነፍስ አድን መርከቦችን ወደ ተሻለ ቦታ ለማድረስ እንዲረዳቸው የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ቀደም ብለው ጣልቃ መግባት ነበረባቸው ወይ' የሚለው ተጨማሪ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው።
አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚሉት የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች እና ፍሮንቴክስ ፈጣን እርምጃ መውሰድ ነበረባቸው ይላሉ።
በጉዳዩ ላይ ያተኮረ የቢቢሲ ዘገባ በአካባቢው የሚገኙ ሌሎች መርከቦችን እንቅስቃሴ ሲተነተን መርከቧ ከመስመጧ በፊት ቢያንስ ለሰባት ሰዓታት ያህል አልተንቀሳቀሰችም ብሏል።
ሆኖም የግሪክ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በእነዚህ ሰዓታት ውስጥ ጀልባዋ ወደ ጣሊያን በመጓዝ ላይ እንደነበረች እና ዕርዳታ እንደማትፈልግ ነግረዉናል ብለው ማስተባበላቸውን ቀጥለዋል።

የሩሲያ የነፍስ አድን ሠራተኞች

ከዚህ ክስተት በተለየ አጋጣሚ በሞስኮ የሚገኘው የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሩሲያ የጦር እና የጭነት መርከብ እሁድ አመሻሽ ላይ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ለአደጋ በተጋለጠች ጀልባ ላይ የነበሩ 68 ሰዎችን ማዳኑን ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ በበኩሉ እስካሁን 72,778 ስደተኞች ከደቡብ ወደ አውሮፓ የገቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል 71,136 ስደተኞች በባህር ወደ ጣሊያን ፣ ግሪክ ፣ ስፔን ፣ ማልታ እና ቆጵሮስ መግባታቸውን አስታውቋል።
ኤጀንሲው ከዚህ ዓመት (2023) መጀመሪያ ጀምሮ በክልሉ ቢያንስ 1,037 ሰዎች ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ሲል የበለጠ አስከፊውን የስታስቲክስ ዘገባውን አቅርቧል።
 

20 June 2023, 15:42