ፈልግ

ዓለም አቀፍ የውሃ ቀን - ካንዳሃር አፍጋኒስታን ዓለም አቀፍ የውሃ ቀን - ካንዳሃር አፍጋኒስታን  (ANSA)

የተባበሩት መንግስታት የውሃ ኮንፈረንስ ስለ ዓለም አቀፍ የውሃ ቀውስ ያለውን ግንዛቤ ያሳድጋል ተባለ

“በዓለም ዙሪያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ሳያገኙ በሚኖሩበት በዚህ ሰአት ፥ ስለ ዉሃ የሚሰበሰበው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፥ ዓለም አቀፍ ስምምነት የተደረገባቸውን ከውሃ ጋር የተገናኙ አላማና እና ግቦችን ለማሳካት ፥ እ.አ.አ. ከመጋቢት 22 እስከ 24 በኒውዮርክ ይሰበሰባል።

ዘላለም ኃይሉ - አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

የ2023 የውሃ ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒውዮርክ ተሰብስቧል። ይህ ዝግጅት በኔዘርላንድ እና በታጂኪስታን ሪፐብሊክ ቅንጅት የተዘጋጀ ሲሆን በውሃ አጠቃቀሙ ላይ ያሉትን ተግዳሮቶች ለማሻሻል ዓለም አቀፍ ተነሳሸነት እንዲኖር እና ትግበራውን ለማፋጠን ተብሎ የታለመ ጉባኤ ነው ተብሏል። ጉባኤው የተጀመረው ፥ የ2023 የአየር ንብረት ሳይንስን ዘገባ ለመገምገም የወሰነው የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ፓነል ከጀመረ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።

"አሁንኑ ይተግበር”

የአይ.ፒ.ሲ.ሲ. (IPCC) ሊቀመንበር የሆኑት ሆውሰንግ ሊ አበክረው እንደሚናገሩት ዘገባው ታላቅ ተግባር ለመተግበር አጣዳፊነቱን አጉልቶ ያሳያል እናም በአስቸኳይ ተግባራዊ ከተደረገ መጪው ጊዜ ለሁሉም ቀጣይነት ያለውና የተረጋጋ እንደሚሆን ይገልፃሉ። ውሃ ለዘላቂ ልማት ፥ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በሚከሰተው ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታልም ተብሏል።

ሆኖም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያሳየው 3.6 ቢሊዮን የሚሆነው የሰው ልጅ በአስተማማኝ ሁኔታ የንፅህና መጠበቂያ ሳይደረግላቸው የሚኖሩ ሲሆኑ ፥ ከሶስቱ ሰዎች አንዱ ማለትም 2.3 ቢሊዮን የሚሆነው “በቤት ውስጥ መሰረታዊ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎች የሏቸውም።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ስለውሃ አጠቃቀም የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንዴት የህይወት ደም ስለሆነው ውሃ የሚሰጠው ዉሳኔ ፥ ለዓለማችን መልካም የሆነ ውጤት የሚያመጣ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አጀንዳው በ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳ ሁለተኛ አጋማሽ እድገትን እና ቁርጠኝነትን ለማፋጠን እንደ መነሻ ሆኖ ያገለግላል። በተለይም ስድስተኛው ግቡ ፥ ለሁሉም የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ አቅርቦትን እና ዘላቂነት ያለው አስተዳደርን ማረጋገጥ ነው ተብሏል።

ሁሉን አቀፍ ንግግሮች

ከምልአተ ጉባኤው ጋር በትይዩነት ፥ ጉባኤው ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2022 በተካሄደው ፥ ውሃ ለጤና ፣ ውሃ ለዘላቂ ልማት ፣ ውሃ ለአየር ንብረት ፣ ውሃ ለመቋቋምያ እና ለአካባቢ ጤና ፣ ውሃ ለትብብር እና ውሃ ለአስር ዓመቱ እቅድ ትግበራ በሚለው የመሰናዶ ስብሰባ ፥ አባል ሀገራት በተስማሙባቸው አምስት ዋና ዋና ጭብጦች ላይ ፥ አምስት መስተጋብራዊ ውይይቶችን ያቀርባል ተብሎም ይጠበቃል።

በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ትኩረት የሚሰጠው ፣ ፍትሃዊ የሆነ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት ፣ በአከባቢ እና በግል ጽዳት እንዲሁም ፥ ውሃ ስላለው ኢኮኖሚያዊ እና ዘላቂ ከተማ ልማት ላይ ስለሚጫወተው ሚና ይሆናል።

በሚቀጥለው ቀን ፥ የዓለም ጤና ድርጅት እና የዩኒሴፍ በጋራ የሚያዘጋጁት መርሃ ግብር ላይ “የውሃ አቅርቦት፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅ” በሚለው ዙርያ ሲሆን ፥ ይህም መሠረታዊ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ከሌላቸው ከአስር ሰዎች ውስጥ ስምንቱ በገጠር እንዴት እንደሚኖሩ እና ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ መካከለኛ ደረጃ ባደጉ አገሮች እንደሚኖሩ አመልክቷል ።

ፓኪስታን ላይ ስለተሰራው ሥራ ምሳሌነት

በእንደዚህ ዓይነት አውድ ውስጥ የተከናወኑ ተጨባጭ ድርጊቶች አንዱ ምሳሌ በሰሜን ፓኪስታን ውስጥ ከሚገኘው ከጊልጊት-ባልቲስታን ክልል ፣ የውሃ መሠረተ ልማት አውታር ፕሮጀክት በአካባቢው መንግሥት እና በተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የግብርና ፈንድ መካከል ባለው ስምምነት በብዙ ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባ ነው።

ግንባታው 75 የመስኖ ሥራ እና የመሬት አቀማመጦችን ያካተተ ሲሆን "የአባቶቻችን ህልም" የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል። በአካባቢው ገበሬዎች በሚሰራው ለመንደሩ የምግብ ዋስትና ጉዳይ ላይ አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።  የፓኪስታን የኢፋድ (IFAD) የሀገር ውስጥ ፕሮግራም ኦፊሰር ፊዳ መሀመድ እንደተናገሩት ፥ ከቦታው አስቸጋሪነት ምክንያት ፥ ከፍተኛ ተራራማ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከአጠቃላይ ሥራው 2%ቱን ብቻ ለመሥራት ተገደናል ብለዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልዕክት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዓለም የውሃ ቀንን ምክንያት በማድረግ ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት ለሥራው ስኬታማ ውጤት ጸሎት እንደሚያደርጉ ገልፀው ፥ ዝግጅቱ   በውሃ እጥረት ምክንያት ለሚሰቃዩ ሰዎች ሲባል ፥ ድጋፍ ለመስጠት ተነሳሽነቱንም እንደሚያሳድግ እና በጣም ወሳኝ ጊዜም እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል ሊቀ ጳጳሱ።

23 March 2023, 16:28