ፈልግ

በሜክሲኮ የስደተኞች ማዕከል በደረሰ የእሳት አደጋ ከደርዘን በላይ ሰዎች ሞተዋል በሜክሲኮ የስደተኞች ማዕከል በደረሰ የእሳት አደጋ ከደርዘን በላይ ሰዎች ሞተዋል  (AFP or licensors)

በሜክሲኮ የስደተኞች ማዕከል በደረሰ የእሳት አደጋ ከደርዘን በላይ ሰዎች ሞተዋል

በአሜሪካ ድንበር ላይ በምትገኘው ጁዋሬዝ በምትባለው የሜክሲኮ ከተማ የስደተኞች ማቆያ ጣቢያ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 39 ሰዎች ሲሞቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል። በሜክሲኮ ኩዳድ ጁዋሬዝ በሚገኘው የሜክሲኮ የስደተኞች ማቆያ ካምፕ የማደሪያ ክፍል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ ፥ የሰላሳ ዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፥ ሃያ ዘጠኝ ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ አዲስ አበባ

የሜክሲኮ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ቃል አቃባይ እንደገለጹት ፥ እሳቱ መጀመሪያ ላይ የተነሳው በማዕከሉ ማደሪያ ክፍል ውስጥ ሲሆን ፥ ከዚያም በፍጥነት በተቀረው የሕንፃው ክፍሎች ውስጥ እንደተዛመተ የተነገረው የእሳት አደጋ ላይ ቀጣይ ምርመራዎች ተጀምሯል ብለዋል ። እሳቱ ከመነሳቱ በፊት አንድ አንድ የወጡ ዘገባዎችም እንዳሉ ተመላክቷል።  

የተጎጂዎቹ አስከሬኖች በአንሶላ ተሸፍነው ከማዕከሉ ውጭ በመደዳ የተቀመጡ ሲሆን ፥ የቆሰሉትን እና አንዳንዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉትን ደግሞ ወደ አካባቢው በሚገኙ ሆስፒታሎች ተወስደዋል ። የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንደገለጹት ማዕከሉ አደጋው ከመከሰቱ ከሰዓታት በፊት በብዛት ከቬንዙዌላ የመጡ 68 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተናግረዋል።

የሪዮ ግራንዴ ወንዝ የሜክሲኮ ድንበር በሆነችው በኩይዳድ ጁሬዝ ከተማ እና በአሜሪካዋ ግዛት በሆነችው በቴክሳስ ኤል ፓሶ መካከል በሃይል የሚፈስ ወንዝ ነው። የጁዋሬዝ የስደተኞች ማዕከላት ፥ ከመካከለኛው እና ደቡብ አሜሪካ ከመጡ ፥ ከድህነት አረንቋ ለመውጣት እና ህልማቸውን ለማሳካት ብለው ወደ አሜሪካ ለመግባት በጓጉ ስደተኞች ተጨናንቋል።  

ሆኖም እነዚህ ስደተኞች ፥ ኮዮቴስ በመባል የሚታወቁት ፥ አደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎች ጋር ግንኙነት ካሏቸው የስደተኛ አዘዋዋሪዎች በሚያዘወትሩት አደገኛ የመተላላፊያ መንገድ ማቋረጥም ይጠበቅባቸዋል።  ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እ.አ.አ. ከ2014 ጀምሮ ከ7,000 የሚበልጡ ሰዎች በዚህ ጉዞ አደጋ ላይ ወድቀው ህይወታቸውን አጥተዋል ብሏል።

በቅርቡ በስደተኞች ተጽፎ ለንባብ የቀረበው ጽሁፍ እንደሚያስረዳው ፥ የሜክሲኮ ባለስልጣናት ስደተኞችን ስይዙ ኢ-ሰብአዊ የሆነ አካሄድን እንደሚጠቀሙ እና ፖሊሶቹም በበኩላቸው ስደተኞቹን በቁጥጥር ሥር ካደረጉ በኋላ መንገድ ላይ ስለ ስደተኞቹ የስደት ሁኔታ ያለ አግባብ እንደሚጠይቋቸው ይፋ አድርጓል።  

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ፥ የባይደን አስተዳደር በየካቲት ወር ያወጣው ህግ ከሆነ ፥ ማንኛውም የአሜሪካን ምድር የረገጠ ወይም የደረሰን ስደተኛ የጥገኝነት ጥያቄን የሚከለክሉ አዳዲስ ህጎችን አውጥቷል። ነገር ግን ይህ የወጣው ህግ ከ200,000 በላይ የሚሆኑት በየዓመቱ ድንበር ለማቋረጥ የሚሞክሩ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞች ፍሰትን እየገታ አይደለም ተብሏል።

29 March 2023, 14:25