ፈልግ

2015.11.13 attentato terroristico Parigi, vittime, attentato, preghiera, fiori 2015.11.13 attentato terroristico Parigi, vittime, attentato, preghiera, fiori  (©Nebojsa - stock.adobe.com)

የሽብር ጥቃት ሰለባዎች ቀን ታስቦ ውሏል

በአሸባሪዎች ጥቃት የሞቱትን ሰዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪ መሠረት በዓለም ዙሪያ እሑድ ነሐሴ 15/2014 ዓ. ም. ታስቦ መዋሉ ታውቋል። በአሸባሪዎች ጥቃት አባቱን ያጣው አቶ ጆቫኒ ቤራርዲ፣ በታሪክ እና በትምህርት ቤት መጽሐፍት ውስጥ ስለ ሽብር ጥቃት የሚገልጽ ክፍል አለመኖሩን አስታውሷል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በቅርቡ በሶማሊያ ውስጥ የተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት፣ ዛሬም ቢሆን የጥቃቱ ሰላባዎች ቁጥር ፈጽሞ እንደማይገታ የሚገልጽ መሆኑ ታውቋል። የጥቃቱ ሰለባዎች ቁጥር እንደ ሀገር ሊለያይ ቢችልም የሰለባዎች ቤተሰብ እና ጓደኞች ሕመም በሁሉም ሰዎች ዘንድ ተመሳሳይ እንደሆነ ተነግሯል።  ይህን መሠረት በማድረግ ነሐሴ 15 ቀን እንዲከበር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጀው ዓለም አቀፍ የሽብር ጥቃት ሰለባዎች መታሰቢያ እና የምስጋና ቀን እሑድ ነሐሴ 15/2014 ዓ. ም. ለአምስተኛው ጊዜ ታስቦ መዋሉ ታውቋል።

ያልዳኑ ቁስሎች አሉ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሽብር ጥቃት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችን በሚያስታውስበት በዚህ ወቅት ዓለም ከኮቪድ ድንገተኛ አደጋ ለመውጣት ሲታገ፣ የሽብር ጥቃት የሚደርስባቸው ሰዎች አስተማማኝ የሕይወት ዋስትናን ሳያገኙ ቀርተው በጭንቀት ውስጥ እንደሚኖሩ፣ እንደ ትጥቅ ትግሎች፣ የኃይል ጥቃቶች እና የአሸባሪዎች ድርጊቶች በመላው ዓለም እየተፈጸሙ መሆናቸው ታውቋል። በአሸባሪዎች ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ታሪክ በርካታ የሕይወት ታሪኮችን የያዘ፣ የማይፈውስ ቁስል ያለው እና ከጣሊያኑ የቀይ ወይም የኒዮ ፋሺስት ሽብርተኝነት አንስቶ እስከ ዛሬው የጂሃዲስት ወይም ሌላ ዓይነት ሽብር ድረስ የዘለቀ መሆኑ ታውቋል።

ለጥቃት የተተው ናቸው

ዘንድሮው ታስቦ የዋለው የሽብር ጥቃት ሰለባዎች ቀን ዋና ጭብጡ “ትዝታዎች” የሚል ሲሆን፣ ይህ የተባሉበት ምክንያት የጋራ ሰብዓዊነትን እና አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ከሚገኙ እና ሊመለስ የማይችል የሕይወት ኪሳራ ካጋጠማቸው ሰዎች ጋር ያለውን አንደንት የምንገልጽበት አጋጣሚ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አብራርቷል። በጣሊያን የሽብር ሰለባዎች ኅብረት እና በኋላም የአውሮፓው ኅብረት ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጆቫኒ ቤራርዲ፣ አባታቸው አቶ ቤራርዲ የሕዝብ ደኅንነት ጉዳይ ሃላፊ ሆነው በመሥራት ላይ እያሉ እ. አ. አ መጋቢት 10/1978 በቱሪን መገደላቸውን አስታውሰዋል። ዕድሜአቸውን ሙሉ የሽብር ጥቃት ሰለባዎችን ሲያስታወሱ የኖሩት አቶ ጆቫኒ፣ በሰዎች ላይ የሚደርስ የሽብር ጥቃት መከላከል አይቻልም ማለት ሳይሆን ነገር ግን የጥቃቱ ሰለባዎች ለሚደርስባቸው አደጋ የተተዉ ናቸው" በማለት አስረድተዋል። 

ለሽብር ሰለባዎች የሚሰጠው ክብር በቅርጽም በመጠንም የተለየ ነው!

አቶ ጆቫኒ ቤራርዲ ለሽብር ሰለባ ተጠቂዎች የሚሰጠው ክብር መቼም ቢሆን እንደነበረ ሆኖ የቀጠለ እንዳልሆነ ገልጸው ይልቁንም በመጠንም በቅርጽም የተለለየ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም እንደ ማስረጃነት የሚቀርበው፣ በትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች በተዘጋጀ የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ሽብር ጥቃቶች የተጻፈ ታሪክ እንደሌለ አብራርተዋል። በጅምላ ጭፍጨፋው ላይ በጣም ብዙ የመንግስት ሚስጥሮች አሉ። እ. አ. አ በ 2004 ዓ. ም.  በማድሪድ ውስጥ በሽብርተኞች በኩል ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ የአውሮፓ ኅብረት መጋቢት 11 ቀን በኅብረቱ አገራቱ ውስጥ የጥቃቱ ቀን ታስቦ እንዲውል መወሰኑን ገልጸው፣ የአሸባሪነትን አስከፊነት ለሌሎች ለማሳወቅ የተደረጉ ጥረቶች ጥቂት ብቻ መሆናቸውን በመግለጽ፣ መስዋእትነትን የከፈሉ ሰዎች ገድል አዲሱ ትውልድ ተመልክቶ ትምህርት ሊያገኝባቸው ይገባል ብለዋል።

22 August 2022, 18:13