ፈልግ

የሞስኮ እና የኪዬቭ ባለስልጣናት በኢስታምቡል ከተማ ለድርድር ተቀምጠዋል የሞስኮ እና የኪዬቭ ባለስልጣናት በኢስታምቡል ከተማ ለድርድር ተቀምጠዋል   (AFP or licensors)

የሞስኮ እና የኪዬቭ ባለስልጣናት በኢስታንቡል ከተማ ለድርድር ተቀምጠዋል

በቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል በሞስኮ እና በኪዬቭ መካከል መጋቢት 21/2014 ዓ. ም. በሚደረግ ንግግር ታላቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑ ተነግሯል። የዩክሬኑ ፕሬዚደንት አቶ ዘሌንስኪ የገለልተኝነት አቋምን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸው ሲናገሩ የክሬምሊን አስተዳደር በበኩሉ የኑክሌር ጦር መሣሪያን ለመጠቀም ያለውን ፍላጎት ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት በጦር እስረኞች ላይ የሚደርሱትን ሰቆቃ እንዲያብራሩ ጠይቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የሁለቱ አገራት ተወካዮች በቱርክ ዋና መዲና ኢስታንቡል መጋቢት 21/2014 ዓ. ም. ድርድር በየሚያድረጉት ወቅት፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዮሴፍ ባይደን የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን “አምባገነን” እንደሆኑ እና “ዩክሬን መቼም ቢሆን አትሸነፍም ሆንም” ሲሉ በድጋሚ መናገራቸውን የዓለሙ ማኅበረሰብ ማድመጡ ታውቋል። በሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል ሲደረግ የቆየው ድርድር ለሁለት ሳምንታት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ዛሬ መጀመረ ሲነገር፣ በሌላ በኩል ሩሲያ በወረሯቸው የዩክሬን ከተሞች የሰዎች ሞት እና ስቃይ መቀጠሉ ታውቋል። ሩሲያ የኒውክሌር ጦር መሣሪያን የመጠቀም ሃሳብ እንደሌላት ወይም የኔቶ አባል ሀገራትን ለማጥቃት ዕቅድ እንደሌላት አስታውቃለች። የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ዜለንስኪ በበኩላቸው የዩክሬን የግዛት አንድነት እስከተጠበቀ ድረስ የገለልተኝነትን አቋም ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ጥያቄ

የብሪታንያ ጋዜጣ ፋይናንሺያል ታይምስ እንደዘገበው፣ ሩሲያ ከአሁን በኋላ ዩክሬን የራሷን መብት የመወሰን መብቷን እንደምታከብርላት እና ወደ አውሮፓ ኅብረት እንድትቀላቀል ለመፍቀድ ዝግጁ መሆኗን ገልጻ፣ ነገር ግን ወታደራዊ ኅብረትን የማትፈቅድ መሆኗን አስታውቃለች። በኦፊሴላዊው የሩሲያ የዜና ወኪል “TASS” ዘገባ መሠረት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበይነመረብ ላይ የተሰራጩ አንዳንድ የቪዲዮ ምስሎችን ዋቢ በማድረግ ባቀረበው ጥያቄ፣ የኪየቭ እና የሞስኮ ባለስልጣናት በዩክሬን ውስጥ በጦርነት እስረኞች ላይ የሚደርሱትን የማሰቃየት ሂደት እንዲገልጹ መጠየቁን አስታውቋል። 

ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተሰደዋል

በዩክሬን ውስጥ ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ሲነገር፣ በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ ዕርዳታ መስጫ መስመሮች እንደተስተጓጎሉ እና ለዚህም ምክንያቱም "ምቹ ሁኔታዎች አለመመቻቸታቸው ነው" በማለት የዩክሬን ባለስልጣናት ገልጸዋል። ጦርነቱ ከተጀመረ ከሰላሳ ሶስት ቀናት በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው ዘገባ እስካሁን 3.8 ሚሊዮን ዩክሬናውያን አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ገልጾ ከእነዚህ መካከል ወደ ዘጠና ከመቶ የሚደርሱት ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸውን አስታውቋል።

ጦርነቱ በመቀጠሉ የስደተኛው ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ ታውቋል። በተለይም የዩክሬን ደቡባዊ ክፍል ያለማቋረጥ በሩሲያ ጦር ሠራዊት እየተከበበ መሆኑን፣ የማሪፑል ከተማ እና አካባቢዋ በሩሲያ ጦር ሠራዊት ቁጥጥር ሥር እንደምትገኝ እና 5,000 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን የከተማዋ ከንቲባ ገልጸዋል። አክለውም የዩክሬን ባለስልጣናት በዶኔትስክ እና በሉጋንስክ ክልሎች "ከባድ ውጊያ" እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው፣ ሩሲያ በአካባቢዎቹ የምታደርገውን የማጥቃት ዘመቻዎችን የማታቋርጥ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢርፒን ከንቲባ፥ “ከተማዋ ነፃ ወጣች”

በሰሜናዊው የዩክሬን ግዛት፣ ቼርኖቤል አካባቢ በተከሰተው ኃይለኛ የቦምብ ፍንዳታ ምክንያት የቃጠሎው ስጋት እየጨመረ መምጣቱ የተነገረ ሲሆን እንደ ሞስኮ ገለጻ መሠረት የጨረሩ ሁኔታ "የተረጋጋ" መሆኑ ታውቋል። በይክሬን የኢርፒን ከተማ ከንቲባ፣ ከተማቸው ከወራሪ ኃይል ነፃ መውጣቷን ገልጸው፣ በአገሪቱ መዲና ኪዬቭ ውስጥም በዩክሬን ታጠቁ ኃይሎች በኩል በተሰነዘረው ጥቃት የሩሲያ ወታደሮች እንቅስቃሴ መገታቱን ተናግረዋል። በመጨረሻም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ፣ አቶ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "ለፖለቲካ ድርድር ሂደት እና ለሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት” መንገዶች እንዲመቻቹ ሁለቱ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነቶች እንዲያደርጉ በማለት ጥረታቸውን ጀምረዋል።

30 March 2022, 14:54