ፈልግ

በብራዚል ውስጥ የሚታይ የአየር ብክለት በብራዚል ውስጥ የሚታይ የአየር ብክለት 

ሰብዓዊ መብት እና የአየር ንብረት ጉዳይ ለዴሞክራሲ አዲስ ፈተናዎች ናቸው ተባለ

በስትራስቡርግ ከተማ በተዘጋጀው የዲሞክራሲ መድረክ ላይ የዓለማችን ሙቀት መጨመር፣ የፖለቲካ እና የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ በዓለም ውስጥ የሚታዩ አዲስ ፈተናዎች መሆናቸውን የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሉካ ሳልታላማኪያ አብራርተዋል። መድረኩን በመቀላቀል በውይይቱ የተሳተፉት የተቋማት ተወካዮች ብቻ ሳይሆኑ በዓለም ውስጥ ታዳሽ የኃይል ምንጭን የሚደግፉ እና የሚያራምዱ ወጣቶች ጭምር መሆናቸውን የአውሮፓ ምክር ቤት አባል ወ/ሮ ክላውዲያ ሉቺያኒ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በስትራስቡርግ ከተማ በሚገኘው የአውሮፓ ምክር ቤት የዲሞክራሲ መድረክ ላይ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ ባለሞያዎች እና ከመላው ዓለም የተወጣጡ ወጣቶች ስለ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እና ስለ አካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ታውቋል። በዛሬው ዕለት የተጠናቀቀው አሥረኛ ዙር ዓለም አቀፍ የዲሞክራሲ መድረክ፣ በአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ላይ በማትኮር መወያየቱ ታውቋል። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የውይይት መድረኩ በአውሮፓ ምክር ቤት ዋናው ጽሕፈት ቤት ውስጥ በበይነ መረብ አማካይነት ሲካሄድ መቆየቱ ታውቋል። በውይይት መድረኩ የተለያዩ አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኢራቅ የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ቪራግ ካውፈር፣ አውዳሚ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በመግታት ረገድ ከፍተኛ ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።

አስተዳደር፣ የሕዝብ እና የግል መብትን በተመለከተ

የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ የትኛውን የአስተዳደር መርህ መከተል እንደሚገባ፣ በዚህ ላይ የሕዝብ እና የግል ሚና ምን መሆን አለበት? በሚለው ሃሳብ ላይ ውይይት መካሄዱ ታውቋል። የሕግ ባለሞያ የሆኑት አቶ ሉካ ሳልታላማኪያ፣ ከሕዝብ እና ከግል መብት ጋር የአካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ የሕግ ጽንሰ-ሀሳብ መካተት አለበት ብለዋል።  

ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብትን ለማረጋገጥ እየሞተሞከረ መሆኑን የሕግ ባለሙያው አስታውሰው፤ ይህም አስፈላጊ እንደሆነ እና በተረጋጋ የአየር ንብረት ውስጥ የመኖር መብት ሊመሠረት እንደሚገባ፣ ውጤቱም አመጾችን ለመከላከል የሚረዱ መብቶችን ያጎናጽፋል ብለዋል። በተስማሚ የአየር ንብረት ውስጥ የመኖር መብት የመንግሥታት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን ዜጎችም አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በውይይቱ መዘንጋት እንደሌለበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሊዲያ ናሮንሃ ተናግረዋል።

10 November 2021, 14:49