ፈልግ

ከሊቢያ ተነስተው ወደ አውሮፓ ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞች መካከል 57ቱ መሞታቸው ተገለጸ። ከሊቢያ ተነስተው ወደ አውሮፓ ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞች መካከል 57ቱ መሞታቸው ተገለጸ።  

ከሊቢያ ተነስተው ወደ አውሮፓ ሲጓዙ የነበሩ ስደተኞች መካከል 57ቱ መሞታቸው ተገለጸ።

በተለይም የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ትኩረት በመስጠት እየተከታተለ የሚገኘው በኢየሱሳዊያን ማሕበር ጥላ ሥር የሚተዳደረው ድርጅት በሐምሌ 20/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንደ ገለጸው በአሁኑ ወቅት “በሊቢያ የሚገኙትን ስደተኞች ለመርዳት ይቻል ዘንድ ሕጋዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን የሚፈቅዱ ፖሊሲዎችን ለመደገፍ የሚመደበው የገንዘብ ድጋፍ መቆም እንደ ሚገባው እና በተቃራኒው ደግሞ ወደ አውሮፓ አህጉር ለመግባት የሚያስችል ሕጋዊ መንገዶችን በመክፈት” ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሂደትን መግታት እንደሚቻል ድርጅቱ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ከሊቢያ የባሕር ዳርቻ ተንስተው ወደ አውሮፓ አሕጉር ለመግባት በባሕር ላይ ጉዞ ጀምረው የነበሩ ስደተኞች ትላንት ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም በጀልባቸው ላይ በደረሰው የመስመጥ አደጋ  57 ሰዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከእነዚህም ሰለባዎች መካከል ቢያንስ 20 ሴቶች እና 2 ሕፃናት እንደሚገኙበትም ተገልጿል። በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ዘገባ መሠረት እ.ኤ.አ. በ 2021 ዓ.ም በማዕከላዊ ሜዲትራኒያን ከተከሰቱት አደጋዎች ጋር ተዳምሮ የሟቾችን ቁጥር ግምት ወደ አንድ ሺህ ያህል ከፍ የሚያደርግ አሳዛኝ ክስተት እንደ ሆነ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል። በዚህ ምክንያት የስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ ትኩረት በመስጠት እየሰራ የሚገኘው የኢየሱሳዊያን ማሕበር ጥላ ሥራ የሚተዳደረው ድርጅት በሐምሌ 20/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው ለሟቾች አሰቃቂ ሞት “ጥልቅ ሀዘን” እንደ ተሰማው የገለጸ ሲሆን  የእነዚህ ሁሉ ሰዎች አሰቃቂ እልቂት “የአውሮፓ መንግስታት እና የማህበረሰብ ተቋማት ግድየለሽነትን” ያሳያል በማለት ድርጅቱ ስለሁኔታው የተሰማውን ሐዘን ገልጿል። በተመሳሳይ መልኩም፣ በተመሳሳይ መንገድ ደህንነታቸው ባልተጠበቀ እና ደረጃ ያላሟሉ ጀልባዎችን በመጠቀም  ከሊቢያ ወደ አውሮፓ አህጉር ባለፈው ዓመት ለመግባት ሲሉ በባሕር ላይ ሲጓዙ ነፍሳቸውን ያጡ የተጎጂዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ያስረዳ ሲሆን በእውነቱ የስደተኞችን ጭፍጨፋ ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ “አስቸኳይ እና ቅድሚያ” ተደርጎ መቆጠር የሚገባው አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።

ከሊቢያ ጋር ያለው ግንኙነት

በተለይም ድርጅቱ እንደገለጸው “ህጋዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለሚፈቅዱ ፖሊሲዎች ለመደገፍ ታስቦ ለሊቢያ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ማቆም ይገባል” በማለት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን በተቃራኒው “ወደ አውሮፓ ለመግባት ለሚፈልጉ ስደተኞች የመግቢያ ሕጋዊ መንገዶችን መክፈት ይገባል፣ ይህ ደግሞ አማራጭ ሆኖ በስደተኞች ዘንድ የሚወሰደውን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መንገዶችን ይዘጋል” በማለት ድርጅቱ አክሎ ገልጿል። ድርጅቱ ለአውሮፓ ህብረት በላከው ማስታወሻ ላይ “መዋቅራዊ የመግቢያ ፖሊሲዎችን ማንቃት እና ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ስደተኞች በአባል ሀገሮች መካከል በእኩል እንዲከፋፈሉ” ድርጅቱ አጥብቆ መጠየቁም ተገልጿል።

በተጨማሪም ከስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ትኩረት በመስጠት በመከታተል ላይ የሚገኘው በኢየሱሳዊያን ማሕበር ጥላ ስር የሚተዳደረው ተቋም የአውሮፓ ህብረት ያልሆኑ የውጭ ዜጎችን መደበኛ መኖሪያ ስፍራ፣ ማህበራዊ ሕይወት ዋስትና መስጠት እና የሥራ ዕድልን መክፈት አዳዲስ ህጎችን የሚያስተዋውቁትን አዲስ ህጎች በተመለከተ "እኔ የውጭ አገር ሰው ነበርኩ - መልካምነትን የሚፈጥረው ግን ሰብዓዊነት ነው" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው እንቅስቃሴ ይህንን ሕግ  እንዲያፀድቁ ለጣሊያን ፓርላማ እ.አ.አ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ለተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ይህ ሀሳብ “ለስደተኞች መብትና ክብር ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ለረጅም ጊዜ እና ያለማቋረጥ በሚጠይቅ የሲቪል ማህበረሰብ ትልቅ ክፍል የተደገፈ” እንቅስቃሴ መጀመሩን ድርጅቱ አስታውሷል።

 የስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ትኩረት በመስጠት እየተከታተለ የሚገኘው በኢየሱሳዊያን ማሕበር ጥላ ሥራ የሚተዳደረው ድርጅት ፕሬዝዳንት አባ ካሚሎ ሪፓሞን “በዚህ መልኩ ሰዎች እንዲሞቱ በመፍቀድ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ አይደለም” ያሉ ሲሆን ብሔራዊ እና የበላይ ተቋማት ዋና ተግባራቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን - የሰብአዊ መብቶችን እና እድገትን በማረጋገጥ የእያንዳንዱን ሰው ሕይወት እና ነፃነት በማክበር ዋስትና መስጠት ይኖርብናል” በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል።

ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እየሰራ የሚገኘው የኢየሱሳዊያን ማሕበር ጥላ ሥራ የሚተዳደረው ድርጅት የኢየሱሳዊያን የስደተኞች አገልግሎት ድርጅት ዋናው መሥሪያ ቤት በጣሊያን በሮም ከተማ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ሲሆን ጦርነቶችን እና ዓመፅን ሸሽተው ወደ ጣሊያን የሚሰደዱትን ሰዎች መብቶችን ማረጋገጥ፣ የማገልገል እና የመጠበቅ ዓላማ ባላቸው ተግባራት እና አገልግሎቶች ውስጥ ለ 40 ዓመታት ያህል ሲሳተፍ የቆየ ድርጅት መሆኑም ተዘግቧል።

28 July 2021, 15:25