ፈልግ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በስነ ምሕዳር ላይ የደረሰው ጉዳት እንዲያገግም ለመሥራት ወሰኑን ገለጸ! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በስነ ምሕዳር ላይ የደረሰው ጉዳት እንዲያገግም ለመሥራት ወሰኑን ገለጸ! 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በስነ ምሕዳር ላይ የደረሰው ጉዳት እንዲያገግም ለመሥራት ወሰኑን ገለጸ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሚቀጥሉት ዐስር አመታት ያህል በስነ ምሕዳር ላይ የደርሰው ጉዳት ያገግም ዘንድ በርካታ ውጥኖችን እና አቅዶችን በማንገብ ልያከናውን መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን ይህ በስነ ምሕዳር ላይ የደረሰው ጉዳት እንድያገግም የሚሰራው ሥራ እ.ኤ.አ. ሰኔ 5/2021 ዓ.ም የዓለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን በሚከበርበት ወቅት በይፋ እንደ ሚጀመር የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእዚያ እለት በበይነ መረብ አማካይነት በሚከናወነው ሥነ ስረዐት ላይ መልእክት እንዲያስተላልፉ ተጋብዘዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.አ.አ ሰኔ 5/2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚያዘጋጀው የዓለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን እንደ ሚከበር ይታወቃል።  በዚህ ዓመት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሥነ ምህዳር ላይ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት መልሶ እንዲያገግም ለማደረግ በተቀናጀ መልኩ ለሚቀጥሉት ዐስር አመታት ያህል የሚያከናውነውን ተግባር በይፋ ይጀምራል። የዚህ ዓመት የዓለም የአካባቢ ጥበቃ ቀን መሪ ሐሳብ  “አስተዋል፣ አዲስ መመስረት፣ መጠገን”  የሚለው መሪ ቃል እንደ ሚሆን የተገለጸ ሲሆን መጪው የተባበሩት መንግስታት ሥነ ምህዳራዊ ተሃድሶ የመፈፀም እቅድ ይፋ እንደ ሚሆን ይጠበቃል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከ 70 በላይ አገራት እርምጃ እንዲወሰድ የቀረበውን ሀሳብ ተከትሎ እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2019 ባስተላለፈው ውሳኔ እ.ኤ.አ. ከ 2021 እስከ 2030 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥነ ምህዳራዊ ተግዳሮቶችን ለመግታት ይቻል ዘንድ አፀፋዊ እርማጃ መውሰድ የሚያስችሉ አዋጅ ለማወጅ መወሰኑ ይታወቃል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ መርሃግብር (UNEP) እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO ) የሚመራው የዐስር አመቱ እቅድ ጠንካራ ፣ ሰፊ መሠረት ያለው ዓለም አቀፍ ንቅናቄን ለመገንባት እና በዓለም ዙሪያ የስነ ምህዳር ብልሹነቶችን ለመከላከል ፣ ለማስቆም እና ለመቀልበስ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማስተዋወቅ ታልሞ የሚከናወን ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥነ-ምህዳራዊ ተሃድሶ እቅድ

የዓለም አካባቢ ቀን ዋዜማ ዓርብ ቀን በበይነ መረብ አማካይነት አንድ ክስተት የታየ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥነ ምህዳራዊ ተሃድሶ መጀመሩን በደስታ ገልጿል። እንደ ፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን ፣ የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአከባቢ ጥበቃ ቀን አዘጋጅ የሆኑት የጀርመን መራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ፣ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአከባቢ ጥበቃ ፕሮግራም (UNEP) ዋና ዳይሬክተር ኢንገር አንደርሰን እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (FAO) ዳይሬክተር ጄኔራል ኪዩ ዶንግዩ ጨምሮ በርካታ የአለም መሪዎች በበይነ መረብ አማካይነ በሚከናወነው ስብሰባ ላይ እንደ ሚካፈሉ ይጠበቃል።

በአካባቢ እና በምድራችን ላይ እይደረሰ የሚገኘውን ጉዳት ለመከላከል ይቻል ዘንድ ግንባር ቀድም በሆነ መልኩ ጥረት በማደረግ ላይ የሚገኙት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ አጋጣሚ “የጋራ ቤታችን” በሚል አርእስት መልእክት እንዲያስተላልፉ እቅድ ተይዞላቸዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ “ላውዳቶ ሲ’ በአማርኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል አርዕስት ለጋራ ቤታችን እንክብካቤ እናድርግ፣ በሚል መሪ ቃል ያልተስተካከለ የሸማቾች አጠቃቀም እና ኃላፊነት የጎደለው ልማት ወደ አካባቢያዊ ወደ ሆነ ውድመት እና የዓለም ሙቀት መጨመር የሚወስዱ ክስተቶች መሆናቸውን አብከረው የገለጹበት ጳጳሳዊ መልእክት እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን ሁሉንም “ፈጣን እና አንድ ወጥ የሆነ ዓለም አቀፍ እርምጃ ” እንዲወስዱ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅ እ.አ.አ ከነገ ቅዳሜ ሰኔ 05/2021 ዓ.ም ጀምሮ ለመጪዎቹ ዐስር አመታት በምድራችን ላይ በደርሰው የስነ ምሕዳር ጉዳት እንዲያገግም ለማደረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን የወጠነው አቅድ በይፋ እንደ ሚጀመር የተገለጸ ሲሆን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ዘላቂ የልማት ግቦች ቀን እ.አ.አ 2030 ዓ.ም በሚጠናቀቅበት ወቅት ከእዚህ ጋር ተያይዞ ይህ የጊዜ ሰሌዳ የከፋ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የመጨረሻው እድል ነው እንደ ሚሆን ተገልጿል። በመሬት ላይ በሺዎች በሚቆጠሩ ተነሳሽነት ዓለምን በዘላቂነት ወደ ፊት ለማምጣት ስኬታማ ሥነ ምህዳራዊ መልሶ የማቋቋም አስፈላጊነት ግንዛቤን ያሳድጋል።

በመገናኛ አውታሮች፣ በክስተቶች እና በተለያዩ በበይነ መረብ በሚሰጡ መድረኮች አማካይነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአስር ዓመት በነደፈው ፕሮጀክቶች፣ አጋሮችን ፣ የገንዘብ ድጋፍን እና የተሃድሶ ጥረቶቻቸውን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስችላቸውን እውቀት ለማግኘት የተሃድሶ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ድጋፉን እንደ ሚሰጥ ተገልጿል።

በዓለም ላይ እየተከሰቱ ያሉ ሥነ ምህዳራዊ ለውጦች

ጤናማ ሥነ-ምህዳር የሰዎችን ኑሮ ያሳድጋሉ ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ይቋቋማል እንዲሁም የብዝሃ-ህይወት ውድቀትን ያስቆማል። ሥነ ምህዳራዊ ሥርዓቶች እንደ ደን ትልቅ ወይም እንደ ኩሬ ትንሽ ሊሆኑ ይችላሉ። በተባበሩት መግሥታት ድርጅት የአከባቢ ጥበቃ ፕሮግራም (UNEP) ምደባ መሠረት 8 ዋና ዋና የስነ ምህዳር ዓይነቶች አሉ- የእርሻ ቦታዎች ፣ ደኖች ፣ ሐይቆች እና ወንዞች ፣ የግጦሽ ስፍራዎች እና በሳር የተሞሉ ስፍራዎች፣ ተራሮች ፣ ውቅያኖሶች እና ዳርቻዎቻቸው፣ ረግረጋማ ስፍራዎች እና የከተማ አካባቢዎችን እንደ ሚያጠቃልል ይፋ ማደረጉ ይታወሳል። ብዙዎች ለሰው ልጅ እና ለህብረተሰቡ ወሳኝ ናቸው ፣ ለሰው ልጆች የውሃ ፣ የምግብ ፣ የግንባታ ቁሳቁስ እና ሌሎች በርካታ አስፈላጊ ነገሮችን ይሰጣሉ። እንዲሁም እንደ የአየር ንብረት ጥበቃ እና ብዝሃ ሕይወት ጥበቃን የመሳሰሉ ለምድራችን አጠቃላይ የሆነ ጥቅሞችን ይሰጣሉ። ነገር ግን ከቅርብ አሥርተ ዓመታት ወዲህ የሰው ልጅ ለተፈጥሮ ሀብቶች ያለው ረሃብ እና ያለ ስስት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያደርገው ብዝበዛ  ብዙ ሥነ-ምህዳሮችን  ከድጡ ወደ ማጡ ደረጃ እንዲገፋ አድርጓል። የእነሱ ተሃድሶ እንደ ዛፎች ማደግ ፣ ከተማዎችን አረንጓዴ ማድረግ ፣ የአትክልት ስፍራዎችን እንደገና መገንባት ፣ የአመጋገብ ለውጥ ወይም ወንዞችን እና የባህር ዳርቻዎችን ማፅዳትን የመሳሰሉ ብዙ ቅርጾችን ሊወስድ ይችላል።

ለረዥም ጊዜ የሰው ልጅ በምድር ላይ ሥነ ምህዳርን በመበዝበዝ እና በማጥፋት ላይ ይገኛል ፡፡ በየሦስት ሴኮንዶች ዓለም የእግር ኳስ ሜዳ ለመሸፈን የሚያስችል በቂ ጫካ ወይም የደን አከባቢ ታጣለች። ከ 4.7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ደኖች - ከዴንማርክ የሚበልጥ ስፋት ያለው አከባቢ በየአመቱ ይጠፋል።

ረግረጋማ የነበሩ ስፍራዎች እንዲነጥፉ ወይም እንዲደርቁ እየተደረገ ለግብርና ሥራ እዲውሉ እየትደረገ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ምክንያት ደግሞ ባለፉት 300 ዓመታት ውስጥ በዓለም ዙሪያ 87 በመቶ የሚሆኑት ረግረጋማ  ስፍራዎች ጠፍተዋል። ባለፈው ምዕተ ዓመት ውስጥ ብቻ ግማሹን ረግረጋማ መሬቶቻችንን አጥፍተናል። ወደ 80 ከመቶው የሚጠጋ በዓለም ውስጥ የተጠቀምንባቸው ቆሻሻ የፍሳሽ ውሃ ህክምና ሳይደረግለት ወደ ውቅያኖስፕቻችን እና ወንዞቻችን ለቀናል። ምንም እንኳን የዓለም ሙቀት መጨመር በ 1.5 ድግሪ ሰልሼስ አያደገ እና ጭማሪ እያሳየ ቢመጣም እ.አ.አ እስከ 2050 ዓ.ም በአለም በባሕር ወልል ላይ የሚገኘው ሥነ ምሕዳር 90 በመቶ የሚሆነው ሊጠፋ ይችላል ፡፡

ከ 180 በሚበልጡ ሀገሮች ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ረግረጋማ ስፍራዎች ለስነ ምሕዳር እጅግ በጣም አስፈላጊነት ያላቸው ሥነ ምህዳሮች ናቸው። ምንም እንኳን እነሱ የሚሸፍኑት ከዓለም መሬት ውስጥ 3 በመቶውን ብቻ ቢሆንም ወደ 30 ከመቶው የአፈር ካርቦን ልቀትን ሊያስወግዱ እንደ ሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

ዓለም አቀፍ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀቶች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ አድገዋል እናም ምድራችን አስከፊ ወደ ሆነ የአየር ንብረት ለውጥ እየተጓዘች እንደ ምተገኝ ያሳያል።

የኮቪ -19 ወረርሽኝ የስነ ምህዳር መጥፋት ውጤቶች ምን ያህል አስከፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ አሳይቷል።እንስሳት የሚኖሩበት የተፈጥሮ መኖሪያ አካባቢን በመቀነስ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን - ኮሮናቫይረስን ጨምሮ - እንዲስፋፉ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥረናል።

በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ሪፖርት መሰረት ፓኪስታን በተለይ የክረምት ወቅት መለዋወጥ እየጨመረ በመምጣቱ የሂማላያን የበረዶ ግግርን በመቀነስ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና ድርቅን ጨምሮ ከባድ ክስተቶች እና አደጋዎችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። እነዚህም የምግብ እና የውሃ እጥረትን መጨመር ያስከትላሉ። ብሉምበርግ እንደሚገምተው በሀገሪቱ 5 በመቶ ብቻ የደን ሽፋን ያለ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ በአማካይ 31 ከመቶ ጋር ሲነፃፀር ለአየር ንብረት ለውጥ በጣም ተጋላጭ ከሆኑ ስድስት ሀገራት አንዷ እንድትሆን ያደርጋታል።

በፓኪስታን ያለው የአከባቢ ችግር በሕዝብ ብዛቷ አማክይነት ተባብሷል-በአለም ላይ እየጨመረ የሚሄድ እና በዓለም ላይ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ከሚገኝባቸው አገራት መካከል አምስተኛዋ ናት። በተጨማሪም በዓለም ባንክ ሪፖርት መሰረት 24 በመቶ የሚሆነው የፓኪስታን ህዝብ በድህነት አዝቅት ስር እንደሚኖር ፣ ይህም ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲወድቁ ያደርጋል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ማለት ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት በአብዛኛው በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ከፍተኛ ጥገኛ ስለሆኑ እና የአየር ንብረት መለዋወጥን የመቋቋም አቅማቸው አነስተኛ ስለሆነ ነው።

ሆኖም በዚህ ዓመት እ.አ.አ በሰኔ 5/2021 ዓ.ም የሚከበረው የዓለም የአካባቢ ቀን ዓለም አቀፋዊ አስተናጋጅ የሆነው የደቡብ እስያ ሀገር በአስር ቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል የሱናሚ ፕሮጀክት በሚል መጠሪያ በሥነ-ምህዳር ላይ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለማቋቋም መንገድን ለመምራት መዘጋጀቱን አሳይቷል። ይህ ፕሮጀችት ባወጣው የድርጊት መርሃ ግብር እቅድ መሰረት እ.ኤ.አ. በ 2023 ዓ.ም አስር ቢሊዮን ዛፎችን ለመትከል ያለመ እቅድ መያዙ ይታወቃል።

04 June 2021, 21:06