ፈልግ

 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በርካታ ተጨማሪ ሰራተኞችን ወደ ድህነት ይገፋል አሉ! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በርካታ ተጨማሪ ሰራተኞችን ወደ ድህነት ይገፋል አሉ! 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኮቪድ -19 ወረርሽኝ በርካታ ተጨማሪ ሰራተኞችን ወደ ድህነት ይገፋል አሉ!

በተባበሩት መንግሥታት ጥላ ስር የሚሰራው የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በዓለም ውስጥ የሚገኘውን የሥራ ስምሪት እና ማህበራዊ እይታ ላይ ለሥራ ገበያው የሚረዱ አኃዞችን ያካተተ አመታዊ ሪፖርት ይፋ ማደረጉ የተገለጸ ሲሆን በቅርቡ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ችግር እና ወረርሽኙ ባይከሰት ኖሮ ሊኖር ስለሚችለው ሁኔታ ​​ጋር ሲነፃፀር በዓመቱ መጨረሻ ላይ 75 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሥራ አጥ እንደ ሚሆኑ ገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት የተፈጠረው ቀውስ በዓለም ዙሪያ ከ 100 ሚሊዮን በላይ ሠራተኞችን ወደ ድህነት አዝቅት እንዲገፉ እንዳደረጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰራተኛ ኤጄንሲ ረቡዕ ግንቦት 25/2013 ዓ.ም ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።

እ.አ.አ ከ 2019 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር በዓለም ዙሪያ በግምት 108 ሚሊዮን ተጨማሪ ሠራተኞች በመካከለኛ ወይም በጣም ድሃ ተብለው የተፈረጁ ሲሆን ይህም ቤተሰቦቻቸው በቀን አንድ ሰው ከ 3.20 ዶላር በታች የሆነ ገቢ ብቻ እንዳላቸው የሚያመለክት መሆኑን የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ድርጅት ዓመታዊ የዓለም የሥራ ስምሪት እና የማኅበራዊ ዕይታ ሪፖርት ያሳያል ፡፡

ይህ ከፍተኛ የድህነት መጨመር በወረርሽኙ ወቅት በተተገበሩ በቤት ውስጥ የመቆየት እርምጃዎች ፣ በግልጽ የሥራ ማጣት እና ጥሩ ጥራት ያላቸው ሥራዎች ተደራሽነት ማሽቆልቆል እና እንዲሁም የሥራ ሰዓታት በመቆራረጣቸው ምክንያት እንደ ተከሰተ ተገልጿል።

ሪፖርቱ “የሥራ  አጥነትን ለማስወገድ እና የሥራ እድሎችን ለማሻሻል በማሰብ ለባለፉት አምስት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ይህ ነው የሚባል ለውጥ ባለማስገኘታቸው ምክንያቱም አሁን እየታየ የሚገኘው የሥራ አጥ የድህነት መጠን እ.አ.አ በ2015 ዓ.ም ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመውረድ ተገዷል” ብሏል።

የሰራተኛ ገበያ ከባድ-ችግር

የዓለም የሰራተኞች ድርጅት (ILO) በወረርሽኙ የተፈጠረው የሥራ ገበያ ቀውስ አሁንም ገና ያላበቃ መሆኑንና የሥራ ስምሪት እስከ መጀመሪያው እ.አ.አ እስከ 2023 ዓ.ም ድረስ ወደ ቅድመ-ወረርሽኝ ደረጃ ይመለሳል ተብሎ እንደማይጠበቅ ያስጠነቅቃል።

እ.ኤ.አ. በ 2021 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በምድራችን ላይ ይህ የኮቪድ 19 ወረርሽኙ ባይከሰት ኖሮ ከነበረበት ጋር ሲነፃፀር አሁንም 75 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች ሥራ አጥ እንደ ሚሆኑ ሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን እናም እስከሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ድረስ በግምት ከ23 ሚሊዮን ያነሱ የሥራ እድሎች ብቻ እንደ ሚፈጠሩ አክሎ ገልጿል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ያልተስተካከለ የኢኮኖሚ ቀውስ መልሶ እንዲያገግም ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ሂደት እ.አ.አ በ 2021 ዓ.ም ሁለተኛ አጋማሽ በክትባት እድገት እና በትላልቅ የበጀት ወጪዎች ይጀምራል ተብሎ እንደ ሚጠበቅ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ደረጃ የሚታየው የኢኮኖሚ ቀውስ መልሶ እንዲያገግም ለማድረግ እየተደረጉ የሚገኙ ጥረቶች በዚህ ዓመት 100 ሚሊዮን የሥራ ዕድል እና በ 2022 ተጨማሪ 80 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጠሩ ተገምቷል።

ከእዚህ ቀደም የነበሩ ነባር ቀውሶች እያሻቀቡ መሄድ ጀምረዋል

ሪፖርቱ በተጨማሪ እንዳመለከተው ኮቪድ -19 ከተከሰተ በኋላ ወረርሽኙ በሥራው ላይ ቀደም ሲል የነበሩትን ልዩነቶችን ያባባሰ ሲሆን ዝቅተኛ የሆነ የሙያ ችሎታ ያላቸው ሠራተኞች ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና ስደተኞች በጣም ከተጎዱት መካከል እንደ ሆኑም ሪፖርቱ ይጠቁማል።

ብዙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችም እንዲሁ በኪሳራ ውስጥ ገብተዋል ወይም እርግጠኛ ያልሆነ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደ ሚገጥማቸው ሪፖርቱ አክሎ የገለጸ ሲሆን በእርግጥ ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው በግምት ሁለት ቢሊዮን ሠራተኞች - ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በመቶኛ ሲሰላ 60.1 % መደበኛ ያልሆኑ ሠራተኞች በ 2019 ዓ.ም መደበኛ ባልሆኑ ሠራተኞች “ከመደበኛ አቻዎቻቸው በሦስት እጥፍ ይበልጣሉ፣ ከሥራ ፈጣሪዎች ደግሞ በ 1.6 % እጥፍ ይበልጣሉ። በችግሩ ምክንያት ሥራቸውን ለማጣት ይገደዳሉ ”ብለዋል።

ችግሩ በጾታ እኩልነት ላይ የሚደረገውን ጥረት አደጋ ላይ ይጥላል የሚል ስጋት ስላለ ሴቶች ከወንዶች በላቀ ደረጃ ከስራ ገበያው እንደ ሚወገዱ እና ብዙዎች በወረርሽኙ የተነሳ ትምህርት ቤት መሄድ ያልቻሉ ህፃናትን የመንከባከብ ሚና የወሰዱ ሲሆን በዚህም ምክንያት ሥራቸውን ሰርተው ያልተከፈለባቸው የሥራ ጊዜ እንዳለ ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ስደተኞች ሠራተኞች ያለ ክፍያ ወይም የደመወዝ ክፍያ በመዘግየት ምክንያት በድንገት ሥራቸውን ለማቋረጥ እንደ ተገደዱ ሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን ብዙዎቹ እንዲሁ የገቢ ኪሳራቸውን ሊያካክስላቸው የሚችል የማኅበራዊ ጥበቃ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት እንደ ተቸገሩ ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

ሰው-ተኮር የፖሊሲ አጀንዳ አስፈላጊ ነው

ከአስከፊው ሁኔታ አንፃር ሪፖርቱ ከአራት ነጥቦች ጋር የተዋቀረ ሁሉን አቀፍ እና የተቀናጀ ፖሊሲን ያማከለ ፖሊሲን እንዲተገበር ምክረ ሐሳብ ያቀረበ ሲሆን አንደኛ ፣ ሰፋፊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማስፋፋትና ጥሩ ሥራዎችን ሊያገኙ በሚችሉ እና የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን እና የደመቀ የሠራተኛ ገበያን በሚደግፉ ዘርፎች ውስጥ ኢንቬስት በማድረግ ምርታማ የሥራ ስምሪት መፍጠር የሚለው ነው። በተጨማሪም በችግር ጊዜ በጣም የተጎዱትን የቤተሰብ ገቢዎች እና የሠራተኛ ገበያ ሽግግሮችን በሠራተኛ ገበያ ፖሊሲዎች አማካይነት እና በይፋ ጥራት ባለው እንክብካቤ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል በማለት አክሎ ገልጿል።

እንዲሁም ሰው-ተኮር በሆነ መልኩ መልሶ ማህበራዊ ጥበቃ ስርዓቶችን በማጎልበት እና ለሁሉም ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የሥራ ሁኔታን በማረጋገጥ ሁሉን አቀፍ ፣ ዘላቂ እና የማይበገር የኢኮኖሚ እድገት ተቋማዊ መሠረቶችን ማጠናከር ይኖርባቸዋል በማለት ሪፖርቱ ሁለተኛውን ምክረ ሐሳብ ያቀርባል።

በመጨረሻም ሪፖርቱ በመንግስት ፣ በአሰሪዎች እና በሰራተኞች ማህበራት መካከል የሰው-ተኮር የመልሶ ማገገሚያ ስልቶችን ውጤታማ አተገባበር ለማሳደግ በማህበራዊ ውይይት ውስጥ ተሳትፎ እንዲጨምር ጥሪውን ካቀረበ በኋላ ሪፖርቱ ተጠናቋል።

03 June 2021, 16:45