ፈልግ

ሰው ሠራሽ አዕምሮ ሰው ሠራሽ አዕምሮ  

በሰው ሠራሽ አዕምሮ ላይ የሚወያይ ሴሚናር ተካሄደ

በሰው ልጆች እና በሰው ሠራሽ አዕምሮ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለመረዳት የሚያግዙ ጥናቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸው ሲነገር ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 3/2013 ዓ. ም የአውታረ መረብ ላይ ሴሚናር መካሄዱ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሰዎች እና አዲስ በሚመጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ መሆኑ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያስነሳ ሲያወያይ መቆየቱ ይታወቃል። በርካታ የቴክኖሎች ውጤቶች ወደ ሰዎች መድረሱ ለሰዎ ልጅ ሕይወት ምን ያህል ጥቃሚነት አለው የሚል ጥያቄን አስነስቷል። ለዚህ እና በቴክኖሎጂ እድገት ዙሪያ ለሚነሱሎች ጥያቄዎች የተለያዩ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በሳክሮ ኩዎሬ ካቶሊካዊ ዩኒቨርስቲቲ ውስጥ የባለሞያዎች ውይይት በደረጉ ታውቋል።

በርዕሠ ጉዳዩ ላይ መወያየት አስፈላጊ ነው

የካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ ያለው የአዲስ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ማደግ ባሕላዊ ትንተናዎች እና ሳይንሳዊ ምርምሮች እንዲካሄዱበት በማድረግ፣ በክስተቱ የሰው ልጅ ልምድ ምን እንደሚመስል ለማወቅ የሚያግዝ መሆኑን አስታውቋል። የሰው ልጅ ቴክኖሎጂ ላብራቶሪ በመባል በሚታወቅ የጥናት ማዕከል የሰው ሠራሽ አዕምሮ ጠበብትን እና በተመሳሳይ ዘርፍ ጥናታዊ ምርምር የሚያደርጉ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲዎች አባላት በጋራ አንድ የጥናት ውጤታቸውን በሕትመት ይፋ የሚያደርጉ መሆኦኑ ታውቋል።

የሰው ልጅ ቴክኖሎጂ ላብራቶሪ ዕድገት

በዓይነቱ የመጀመሪያ የተባለለት የሰው ልጅ ቴክኖሎጂ ላብራቶሪ የተመለከተ እና የጥናት ሥራ ውጤቶችን ይፋ ያደረገ የአውታረ መረብ ላይ ሴሚናር ዛሬ መካሄዱ ታውቋል። ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው በዚህ የአውታረ መረብ ሴሚናር በዘርፉ ሳይናሳዊ ጥናት ያካሄዱ ምሁራን የተሳተፉ ሲሆን ሳይንሳዊ ጥናታቸው በሰው ሰራሽ አዕምሮ እና በዲጂታል የኢንዱስትሪ አገልግሎት ላይ ያተኮረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።      

10 June 2021, 16:28