ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከመጋቢት 26-29/2013 ዓ.ም ደረስ 33ኛውን ሐዋርያዊ ግጉብኝት በኢራቅ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከመጋቢት 26-29/2013 ዓ.ም ደረስ 33ኛውን ሐዋርያዊ ግጉብኝት በኢራቅ ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢራቅ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የወንድማማችነት መንፈስ የፈጠረ ጉዞ ነበር።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በኢራቅ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የወንድማማችነት መንፈስ የፈጠረ ጉዞ ነበር።

የክርስትና እና የሙስሊም እምነት መሪዎች እ.ኤ.አ. መጋቢት መጀመሪያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ በኢራቅ አድርገውት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማካፈል ሐሙስ ግንቦት 26/2013 ዓ.ም በብይነ መረብ አማካይነት ውይይት ማደረጋቸው ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የሰብዓዊ ወንማማችነት ማሕበር ከፍተኛ ኮሚቴ ይህንን በበይነ መረብ አማካይነት የተካሄደውን ውይይት መምራቱ የተገለጸ ሲሆን “የአንድ አፍታ የወንድማማችነት መንፈስ-የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ታሪካዊ የኢራቅ ጉብኝት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ውይይት ነበር።

ዝግጅቱ ከመላው መካከለኛው ምስራቅ የተውጣጡ የሃይማኖት እና የሲቪክ መሪዎችን በማሰባሰብ የሊቀ ጳጳሱ በኢራቅ የነበራቸው ሐዋርያዊ ጉዞ አስፈላጊነት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለመጋራት እንዲሁም ኢራቅን መልሶ በመገንባቱ ቀጣይ እርምጃዎች እና ሀገሪቱ እንዴት መረጋጋት ፣ እርቅ ፣ እና ለወደፊቱ የተሻለ ተስፋ ማሰራራት ይችል ዘንድ በእነዚህ ሐሳቦች ላይ ያተኮረ ውይይት እንደ ነበረም ተገልጿል።

የሰው ልጅ ሕብረ ብሔራዊነት ለአብሮነት

የሰብዓዊ ወንድማማችነት ማሕበር ከፍተኛ ኮሚቴው ዋና ፀሀፊ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ሞሃመድ አብደሰላም በበይነ መረብ የተደርገውን ውይይት ከከፈቱ በኋላ ሲያስረዱ “ዛሬ እዚህ የተሰበሰብነው ይህንን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጉብኝት እንዴት በትግባር መተግበር እንዳለብን እና ምን ማድረግ እንደምንችል እና በሚመሰረትባት ኢራቅ ውስጥ ወንድሞቻችንን እንዴት መርዳት እንደምንችል በአንድ ላይ ለማሰብ ነው። መልካም የሆነ ማህበራዊ ጨዋነት እና ለሰው ልጅ በጋራ መኖር አስደናቂ የሆነ ሕብረ በሔራዊነት የያዛቸውን መልካም እሴቶች አስጠብቆ ወደ ፊት መጓዝ ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገልጿል።

ይህ መልካም የሆነ ሕብረ ብሔራዊነት እና መልካም ገጽታው ግን “በኢራቅ ሕዝብ ውስጥ ትልቅ ቁስል ጥሎ ያለፉ” ጦርነቶች ፣ ግጭቶች እና የሽብርተኞች ጥቃት የተነሳ ተጎድቷል ያሉ ሲሆን የኢራቅ ተጋድሎዎች “የዚህን ህዝብ ያልታበሰ እንባ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጉብኝት የተነሳ ሊታበስ መቻሉን አክለው ገልጸዋል።

የሕግ ባለሙያ የሆኑት እና የሰብዓዊ ወንድማማችነት ማሕበር ከፍተኛ ኮሚቴ የሆኑት አብዱልሰላም “በዚህ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ ለመገንባት የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ” ለተሳታፊዎች ማረጋገጫ የሰጡ ሲሆን ታላቁ የአል-አዝሃር ኢማም እንዲሁ ኢራቅን መጎብኘት ይችላሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከመጋቢት 26-29/2013 ዓ.ም ደረስ 33ኛውን ሐዋርያዊ ግጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢራቅ ማቅናታቸው የሚታወስ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእዚያው በነበራቸው ቆይታ “ወደ አንተ ስመለከት ፣ የኢራቅ ህዝብ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ብዝሃነት ይታየኛል ፣ ይህ ደግሞ መላው ክልሉ ለወደፊቱ የሚጠብቀውን ውበት የሚያሳይ ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “እዚህ መገኘታችሁ ውበት አንድ ወጥ ብቻ የሆነ ነገር ሳይሆን ነገር ግን በልዩነት ውስጥ የሚበራ መብራት እንደ ሆነ እንገነዘባለን” ማለታቸው ይታወሳል።

“የመጨረሻው ቃል የእግዚአብሔር፣ በኃጢአትና በሞት ላይ ድል አድራጊ የሆነው የልጁ ነው” በማለት በወቅቱ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሽብርተኝነት እና በጦርነት ውድመት መካከል እንኳን በእምነት ዐይን የሞትን የሕይወት ድልን ማየት እንችላለን” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በወቅቱ መናገራቸው ይታወሳል።

በመቀጠልም “በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን አመስገኑ” እና “በጸጋው እኛን የሚጠብቀን እና ፈጽሞ በማያሳዝነን” በአምላክ በመታመን በእምነት ላይ የነበሩትን የአባቶቻችሁን እና የእናቶቻችውን ምሳሌ እና ትሩፋት ማስታወስ ይገባል ብለው ነበር።

“ይህንን ውርስ አጥብቃችሁ ያዙ! እሱ የእናንተ ጥንካሬ ምንጭ ነው! ” በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ  "አናንተ ብቻችሁን አይደላችሁም! መላው ቤተክርስቲያን በጸሎት እና ተጨባጭ በሆነ መልኩ ድጋፉን ለእናንተ ያቀርባል። እናም በዚህ ክልል ውስጥ ብዙ ሰዎች በችግራቸው ጊዜ እንኳን ሳይቀር በሮቻቸውን ለሌሎች ክፍት አድርገዋል” ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ከአሸባሪዎች ጥቃት በሕይወት የተረፉት ሰዎች ይቅርታ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው” በድጋሚ ገልጸዋል። ይህ ይቅር ባይነት ቅዱስ አባታችን እንደ ገለጹት ከሆነ “በፍቅር ለመቆየት እና ክርስቲያናዊ ሆኖ ለመቀጠል አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ በወቅቱ ቅዱስነታቸው አክለውም እንደ ገለጹት ይቅር ለማለት መቻል እና ተስፋ ላለመቁረጥ ድፍረትን እና ብርታትን ለማግኘት በፍቅር ጎዳና ላይ ለመራመድ አሁንም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል ፣ ነገር ግን አሁንም በእግዚአብሔር በኩል እና በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር “እንብይ ለሽብርተኝነት፣ በሃይማኖት ስም ማጭበርበር ” ይቅር ማለት እንደ ሚገባ አክለው ገልጸው ነበር።

ቅዱስነታቸው በወቅቱ በኢራቅ በነበራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት አክለው እንደ ገለጹት “ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት የንስሐ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል - ለዓመታት የተጫነባችው መስቀል በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ስም ወደ እዚህ አገር ሰዎች ራሴን ቅርብ ባለማድረጌ፣ ወደዚያ ሰማዕት ቤተክርስቲያን መቅረብ ባለመቻሌ፣ በቃራቆሽ መግቢያ ላይ ወደ ተቀመጠው ግዙፍ መስቀል ራሴን ቅርብ ባለማድረጌ አዝናለሁ። በተለይ ቁስሎቹ አሁንም ክፍት ሆኖ እንዳሉ መመልከቴ እጅግ በጣም ተሰምቶኛል፣ የበለጠ ደግሞ ከዓመፅ እና ከስደት የተረፉትን ሰዎች ተገናኝቼ ምስክርነታቸውን ስሰማ እጅግ በጣም አዝኜ የነበረ ሲሆን እናም በተመሳሳይ ጊዜ የክርስቶስን መልእክት በመቀበል ደስታን በዙሪያዬ አየሁ። ለእዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ የተመረጠው መሪ ቃል በሆኑት በኢየሱስ ቃላት ውስጥ “ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ” (ማቴ 23፡8) የሚለው ሲሆን አጠቃላይ ለሰላም እና ለወንድማማችነት አድማስ የመክፈት ተስፋን ስንቄ ወደ እዚያው አቅንቼ ነበር፣ ያንን ተስፋ በእዚያ አገር ውስጥ ተመልክቻለሁ። በሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት ንግግር ውስጥ ይህ ተስፋ ተሰማኝ። በብዙ ሰላምታዎች እና ምስክርነቶች፣ ሕዝቡ ባቀረበው ሙዚቃዎች እና ያሳያቸው ምልክቶች ውስጥ ተገነዘብኩ። በወጣቶች ብሩህ ገፅታዎች ላይ እና በአረጋውያን ንቁ በሆኑ ዓይኖች ላይ ይህንን ተስፋ አነበብኩኝ” ማለታቸው ይታወሳል።

አክለውም “የኢራቅ ህዝብ በሰላም የመኖር መብት አለው ፤ የእነሱ የሆነውን ክብራቸውን እንደገና የማግኘት መብት አላቸው። የእነሱ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ መሰረታቸው ከሺዎች ዓመታት በፊት የተጀመሩ ናቸው-የሜሶፖታሚያ የሥልጣኔ መነሻ ናት። በታሪክ ደረጃ ባግዳድ በመጀመሪያ ደረጃ አስፈላጊነት ከተማ ናት። ለብዙ መቶ ዘመናት በዓለም ውስጥ እጅግ ብዙ መጽሐፍት ያለው ቤተ-መጻሕፍት ነበራት። እና ማን አጠፋው? ጦርነት። ጦርነት ሁል ጊዜ በዘመን ለውጥ ራሱን የሚቀይር እና የሰውን ልጅ መብላት የሚቀጥል ጭራቅ ነው፣ ጦርነት” ብለው እንደ ነበረ ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጋብት 01/2013 ዓ.ም ባደረጉት ሳምንታዊው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው እርሳቸው ከየካቲት 26-29/2013 ዓ.ም ደረስ በኢራቅ አድርገውት በነበረው 33ኛውን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በተንፀባረቁት አብይት ክንውኖች ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በጉብኝታቸው ወቅት የተሰማቸውን የጸጸት ስሜት እንዲሁም የኢራቅ ህዝብ የክርስቶስን መልእክት በደስታ በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ አጉልተው ገልጸዋል።ቅዱስነታቸው በወቅቱ በኢራቅ የነበራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት አስመልክተው በተናገሩበት ወቅት “ነገር ግን ለጦርነት የሚሰጠው ምላሽ ሌላ ጦርነት አይደለም ፣ ለመሣሪያ የሚሰጠው ምላሽ ሌላ መሳሪያ መሆን አይገባውም። ምላሹ ወንድማማችነት ነው። ይህ ለኢራቅ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ተግዳሮት ነው። በግጭቶች ውስጥ ለብዙ ክልሎች እና በመጨረሻም ለመላው ዓለም ተግዳሮት የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

አክለውም “በዚህ ምክንያት እኛ ከአራት ሺህ ዓመታት በፊት አብርሃም የእግዚአብሔርን ጥሪ በተቀበለበት በዑር አገር ከሚገኙ የክርስቲያን እምነት ተወካዮች እና ከሙስሊም እምነት ተከታዮች እንዲሁም ከሌሎች የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ተገናኝተን በጋራ ጸሎት አቅርበን ነበር። አብርሃም ብዙ ዘር እንደ ሚሰጠው ቃል የገባለትን የእግዚአብሔርን ቃል ስለሰማ በእምነት አባታችን ነው። ሁሉንም ነገር ትቶ ሄደ። እግዚአብሔር ለተስፋዎቹ ታማኝ ነው እናም እስከ ዛሬ ድረስ ወደ ሰላም የሚወስደውን እርምጃችንን ይመራል። ወደ ሰማይ እይታቸውን በማደረግ በምድር ላይ የሚጓዙትን ሰዎች እርምጃዎች ይመራል። እናም በዑር - በእነዚያ ብሩህ ሰማይ ስር አብረን ቆመን ፣ በሰማይ የሚገኘው አባታችን አብርሃም ያየነው ተመሳሳይ ሰማይ እየተመለከትን፣ እኛ የእርሱ ዘርማንዘር የሆንን - ሁላችሁም ወንድማማቾች እና እህተማማቾች ናችሁ የሚለውን በጋራ የምናስተጋባ ይመስላል” ማለታቸው ይታወሳል።

04 June 2021, 10:58