ፈልግ

ተ.መ.ድ  ሥደተኞችን በኮቪድ­19 መከላከል ሂደት ውስጥ ማካተት ይገባል አሉ። ተ.መ.ድ ሥደተኞችን በኮቪድ­19 መከላከል ሂደት ውስጥ ማካተት ይገባል አሉ።  

ተ.መ.ድ ሥደተኞችን በኮቪድ­19 መከላከል ሂደት ውስጥ ማካተት ይገባል አሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ላይ፥ሐገራት በኮቪድ­19 ትግሎቻቸው እና ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ ስደተኞችን ማካተት ይኖርባቸዋል አለ።እንዲሁም ስደተኞች ኢኮኖሚን ለማነቃቃት አስፈላጊ በመሆናቸው ሊታገዙ ይገባል በማለት አክሎ ገልጿል።

ሥደተኞች በስደት ላሉበት ሀገር እና ለእናት አገራቸውም ኢኮኖሚ መነቃቃት አስፈላጊዎች ናቸው።በመሆኑም በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ መልሶ የማገገም እቅድ ውስጥ መካተት ይኖርባቸዋል ብሏል ድርጅቱ። ይህ የሚሆነው ማሕበራዊ አገልግሎቶችን ማግኘታቸውን እና አለማግኘታቸውን በማረጋገጥ እንደ ሆነ ድርጅቱ የገለጸ ሲሆን በመሆኑም የሚገባቸውን ክብር እና ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል ብሏል። እንዲሁም ደህንነቱ በተጠበቀ፣በሥርዓት እና በመደበኛ የስደተኞች ፍልሰት አማካይነት በማስተዳደር ሥደተኞች ኢኮኖሚን እንዲያጎለብቱ፣ የበለጠ ሁሉን አቀፍ እና ጠንካራ ማሕበረሰብ እንዲገነቡ ማድርግ ይቻላል በማለት አብራርቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪውን ያቀረበው በታኅሳስ 09/2013 ዓ.ም ተከብሮ ባለፈው የሥደተኞች ዓመታዊ ክብረ­በዓልን ምክንያት በማድረግ ነበር። እ.አ.አ ታህሳስ 18/2020 ዓ.ም በየዓመቱ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን እ፣አ፣አ በ2000 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ የተቋቋመ ሲሆን ሥደተኞች ሰብዓዊ መብታቸው እና ነጻነታቸው ሙሉ በሙሉ እንዲከበር በማሰብ የሚከበር በዓል ነው። የዚህ ዓመት የበዓሉ መሪ ቃል “የሰው ልጅን እንቅስቃሴ እንደገና ማሰብ” የሚል መጠሪያ ያለው ነበር።

ቦታ ያልተሰጠው የሥደተኞች ሚና  

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ለበዓሉ ባስተላለፉት መልዕክት፥በዚህ ዓለም አቀፍ የወረርሽኝ ወቅት ሕብረተሰቡ በየአካባቢው የሚገኙትን ሥደተኞች ላይ ጥገኛ ስለመሆኑ አመላክቷል በማለት ተናግረዋል።በመሆኑም ይሕ የወረርሽኝ ወቅት እነዚህ ሥደተኞች በሕብረተሰቡ ውስጥ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳይቷል ብለውም አበክረው ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው አያይዘውም ሥደተኞች ለነበርንበት እና አሁንም ያለንበት የወረርሽኝ ቀውስ የከፈሉት ግንባር ቀደም አስተዋጽዎ በሚገባ ሊደነቅ ይገባል ብለዋል። እንዲሁም ይህ ታላቅ ሚናቸው የታመሙ አዛውንቶችን ከመንከባከብ አንስቶ እስክ ምግብ አቅርቦትን ከማረጋገጥ አንፃር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል በማለት አጽንዖት በመስጠት አብራርተዋል፡፡ሥደተኞች ለማሕበረሰባችን ወሳኝ እንደሆኑ ሁሉ እነሱም በመልሶ ማገገሚያ እቅዶቻችንም መካተት ይኖርባቸዋል ሲሉም በሚገባ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ሁሉም አገራት ከወረርሽኙ መልሶ የማገገሚያ ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ በተለይም በጤና እና በክትባት መርሃግብር ውስጥ ሥደተኞች መካተት አለባቸው ብለው ትኩረት በመስጠት አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም “የጥላቻ ንግግሮችን እና ዘረኝነትን መሠረት ያደረጉ ድርጊቶችን መቃወም ደግሞም ማስወገድ ይኖርብናል” ሲሉም አሳስበዋል።አክለውም እነዚህ ሥደተኞች ያለ ገቢ እና ያለ ሕጋዊ ከለላ እንዳይተው ጥሪ አቅርበዋል።በተጨማሪም የሚገባቸውን እንዲደረግላቸው በሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሰዎችን እንቅስቃሴን እንደገና ማሰብ

አያይዘውም ጉተሬዝ እንዲህ በማለት ጥሪ አቅርበዋል።ይኸውም፦“በዚህ ዓለም አቀፍ የሥደተኞች ቀን፥ዓለም አቀፍ ደህንነት፣ሥርዓት ያለው እና መደበኛ ፍልሰትን ለመተግበር ወረርሽኙ ያመጣልንን በአብሮነት የማገገም እድልን መጠቀም አግባብ ነው ብለዋል።በመሆኑም የሰዎች እንቅስቃሴን እንደገና በማሰላሰል፣ሥደተኞች በሥደት ባሉበት አገር ውስጥ  እና ለእናት አገራቸውም ኢኮኖሚ እድገት አቀጣጣይ እንዲሆኑ ማብቃት ተገቢ ነውም በማለት አብራርተዋል።እንዲሁም የበለጠ አካታች እና ጠንካራ ማሕበረሰብን መገንባት የሚቻለው በአብሮነት መሆኑንም ገልጸዋል።

የመቋቋም ችሎታ የአሸናፊዎች አሸናፊ

 

የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የሥደተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አንቶኒዮ ቪቶሪኖ፥ ሥደተኞች “ጊዜያቶች አስቸጋሪ በሚሆንበት ወቅት የመቋቋም ችሎታ የአሸናፊዎች አሸናፊ” ያደርጋል በማለት  ገልጸዋል። እንዲሁም ዓለማችን ከተከሰተባት ወረርሽኝ ተሻግራ ወደ መደበኛ ሕይወት እንድትመለስም ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ በማለትም አበክረው አስገንዝበዋል፡፡

ዩኒሲኤፍ-የሥደተኞች መገለል

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መራጃ ፈንድ (ዩኒሲኤፍ) ዘገባ መሠረት፥ሥደተኞች እና የተፈናቀሉ ሕጻናት በዓለም አቀፉ መድረክ ወረርሽኙን ከመከላከል እቅድ ውስጥ አልተካተቱም።እንዲሁም ከበሽታው መልሶ ለማገገምም በሚደረገው ጥረት አለመካተታቸውን ዘገባው ያስረዳል።በተጨማሪም አስፈላጊ አገልግሎቶች እና እንክብካቤን ከማግኘት አኳያም በብዙ የተጓደለባቸው መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

በቅርቡ በዩኒሲኤፍ ከ159 ሀገራት ናሙና ተወስዶ የተደረገ ጥናት እንደሚያመላክተው ከ272 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ሥደተኞች 33 ሚሊዮን የሚሆኑት ሕጻናት ልጆች ናቸው። እንዲሁም 12᎐6 የሚሆኑት ሕጻናት ሲሆኑ 1᎐5 የሚሆኑት ደግሞ ጥገኝነት ጠያቂዎች ናቸው።

እንዲሁም በ10 ሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ በገዛ ሀገራቸው ሥደተኛ ሆነው ይኖራሉ።ለምሳሌ በሕንድ ሀገር ከ93 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት በሀገራቸው ሥደተኞች ሆነዋል።በዓለም አቀፍም ከ21᎐5 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት በግጭት እና በተለያዩ ችግሮች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

ለተጋላጭ ሕጻናት ቅድሚያ መስጠት

በዚሁ ዓለም አቀፍ የሥደተኞች ቀን፥ዩኒሲኤፍ ለመንግሥታቱ ሁል ጥሪ አቅርበዋል።ይኸውም፦የተጋላጭ ሕጻናት ዋስትናን ይመለከታል።በተለያዩ ሀገራት በጥገኝነት እና በሥደት ያሉት ሁል እንዲሁም በቀያቸው ለተፈናቀሉትም ጭምር ከዚህ ወረርሽኝ መልሶ ለማገገም በሚደረግ ጥረት ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።መገለል እና መድልዎ ሳይደርስባቸውም በጤና፣በጥበቃ እና በትምህርት አገልግሎትም ሊታገዙ ይገባል በማለት ተማጽኗል።

የዩኒሲኤፍ ዋና ዳይሬክተር ሄርኒታ ፎሬም በበኩላቸው በጣም የተጋለጡ ሕጻናትም እገዛ ያልተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።በዚህ በወረርሽኝ ጊዜ ሕጻናት ችላ ተብለዋልም ብለዋል።ይሕ የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት ድርጅትም እነዚህን ሕጻናት ለማገዝ ዓለም አቀፍ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።ሁሉም በየፊናው ሕጻናትን ለመታደግ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሊተባበር ይገባልም በማለት አበክረው አስገንዝበዋል።   

22 December 2020, 12:05