ፈልግ

ኮ ሃራም በገና ዋዜማ ናይጄሪያ ውስጥ 11 ሰዎችን ገደለ ኮ ሃራም በገና ዋዜማ ናይጄሪያ ውስጥ 11 ሰዎችን ገደለ 

ቦኮ ሃራም በገና ዋዜማ ናይጄሪያ ውስጥ 11 ሰዎችን ገደለ

ቦኮ ሃራም የተባል አክራሪ የእስልምና እምነት ክንፍ አሸባሪ ቡድን በናይጄሪያ ደቡብ ምሥራቅ አካባቢ በገና ዋዜማ 11 ሰዎቸን ገድሏል። 

የቫቲካን ዜና

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ከሳምቢሳ ጫካ ወጥተው በመኪና እና በሞተር ሳይክል በመሆን ያለምንም ርህራሄ መተኮስ ጀመሩ።ይሕ የሆነውም በደቡብ ምሥራቅ የቦርኖ ክፍለ ሃገር ፔሚ በተባለች  መንደር ነው።መንደሪቱም ብዙ ክርስቲያኖቸ የሚኖሩባት ነች።በጥቃቱም ሳቢያ 11 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል።የሞቱ ሰዎች ብዛትም የታወቀው ከአካባቢው ለኤኤፍፒ (AFP) በተሰጠው የዜና ምንጭነት መሠረት ነው። 

በጌታችን የልደት በዓል ሁለት የተከሰቱ ጥቃቶች

ቤተክርስቲያን አቃጥለዋል።በገና በዓል ቀን ምግብ ለማከፋፈል የተዘጋጀ ማከፋፈያም ተዘርፏል።እንዲሁም መድሐኒቶች ተዘርፈው የአካባቢው ሆስቢታሊም በእሳት ተቃጥሏል።

በጥቃቱ ወቅት የመንደሩ ነዋሪዎች ወደ ጫካ በመሸሻቸው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችል ነበር።እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ያሉበት ሁኔታም የታወቀ አይደለም፡፡በሌላ ያልተረጋገጠ ዜናም አንድ ካህን ታፍነው የተወሰዱ መሆኑን ተሰምቷል፡፡ሐሙስ ዕለት በሌላ ጥቃትም ታጣቂዎች በአጎራባች በአዳማዋ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ጋርኪዳ በተባለ አካባቢ ሌላ የክርስቲያኑ ማሕበረሰብ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል።እንዲሁም ቤቶች ተቃጥለዋል።ነዋሪዎቹ ለኤ፥ኤፍ፥ፒ እንዳሉትም መድኃኒት ቤቶች እና የምግብ ማከማቻዎች ተዘርፈዋል።

በዚያ ጥቃት የደረሰ የሟቾች ወይም የተጎዱ ሰዎች ሪፖርት አልተገኘም፡፡ቀደም ባሉት ጊዜያት የተከሰተውን ሁኔታ ተከትለው የደህንነት ተቋማት በክርስቲያኖች በዓል ወቅት የጥቃት አደጋ ሊኖር እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር።

የቦኮ ሃራም ሽብርተኝነት

ቦኮ ሃራም በሰሜን ናይጄሪያ መንግሥትን ከስልጣን ለማውረድ እና እስላማዊ መንግሥት ለመፍጠር በሚያደርገው ትግል በርካታ ጥቃቶችን ፈጽሟል፡፡ከአስርት ዓመታት በላይ የቆየው በናይጄሪያ ደቡብ ምሥራቅ በኩል ያለው ግጭት ለ36 ሺህ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሆኗል።እንዲሁም እንደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እሳቤም ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቀለዋል። 

ፔሚ የተባለችው መንደር የምትገኘው ከቺቦክ 20 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ነው።ቺቦክም ቦኮ ሃራም ከ6 ዓመታት በፊት 200 መቶ ሴት ተማሪዎችን ወስዶ ያገተበት ቦታ ነው።

በተመሳሳይ በባለፈው ዓመትም ቦኮ ሃራም አንድ ቪዲዮ ለቆ ነበረ።ቪዲዮውም የሚያሳየው በገና በዓል ቀን በቦርኖ ክፍለ ሃገር 11 ሰዎችን መግደሉን የሚያመላክት ነው። 

እ᎐አ᎐አ ሕዳር 28 ቦኮ ሃራም በኮሼቤ ቦርኖ 110 የሚሆኑ ገበሬዎችን ገድሏል።በዚሁ በያዝነው ወር ታህሳስ ሁለተኛ ሳምንት መጀመሪያ ላይ 330 ተማሪዎችን አግቷል።እነዚህ ተማሪዎች የተወሰዱትም መንግሥት ከሚያስተዳድረው አዳሪ ትምህርት ቤት ነው።ይሕ ትምህርት ቤት የሚገኘው በደቡ ምዕራብ በምትገኘው ካሲና ክፍለ ሃገር ነው።ይሕ ሁሉ የሚሆነው በዚሁ የሽብር ቡድን ነው።ከታገቱት ውስጥም ከአጋቾቹ ጋር በተደረገ ፊልሚያ ብዙ ተማሪዎች ከዚህ ሽብርተኛ ቡድን ድነዋል።በብዙ የናይጄሪያ ክፍሎች ማሕበረሰቡ ከመከላከያ ጋር በማበር እራሱን መከላከል ጀምሯል።ይሕ ሕገወጥነት እና ሽብርተኝነትም በጎረቤት ሃገር ኒጀርም መታየት ጀምሯል።እንዲሁም ወደ ቻድ እና ካሜሮንም ችግሩ መስፋቱ አልቀረም።ይሕም የሚያሳየው የሽብርተኛውን ቡድን በጋራ ለማጥቃትም የሚያበረታታ ነው።

የፕረዚደንቱ ውሳኔ

ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪም ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ “የቦኮ ሃራም አመጽን እና ሌሎች ወንጀሎችን በመቋቋም ረገድ አስተዳደራቸው ደፋር ሆኖ እንደሚቆይ ቃል መግባታቸውን” ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም በፅሑፍ ባስተላለፉት የገና በዓል መልእክትም “ለእኔ በአገሪቱ ውስጥ ላሉት ነዋሪዎ ሁሉ ደህንነትን ማስጠበቅ የእምነት ቃሌ ሆኖ ይኖራል” በማለት ገልጸዋል፡፡

የሊቀ ጳጳሱ ይግባኝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮም አርብ ዕለት “ኡርቢ ኤት ኦርቢ” የገና በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት ናይጄሪውያንን ጨምሮ በተለያዩ ግጭቶች በተጎዱ የዓለም አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲኖር ጸልየዋል፡፡በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ በህዳር 28 ቀን አርሶ አደሮች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ተደርጓል።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትም ይሕንን ተከትሎ በታህሳስ 2 ቀን በነበራቸው ስብሰባ ለሁሉም ለተጎጂዎች እና ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለገዳዮቹም ከመጥፎ ሥራቸው እንዲመለሱ ጸሎት አድርገዋል፡፡

27 December 2020, 10:42