ፈልግ

የሞት ቅጣት ፍርድ እንዲቀር ተደረገ። የሞት ቅጣት ፍርድ እንዲቀር ተደረገ።  

በሰሜን አሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት ያስተላለፈው የሞት ቅጣት ፍርድ እንዲቀር ተደረገ።

በሰሜን አሜሪካ፣ ኢንዲያና ግዛት ውስጥ ከአስራ ሰባት ዓመት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞት ቅጣት ፍርድ እንዲሰረዝ መደረጉ ተገለጸ። በዚሁ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተበየኑት ሌሎች ሁለት የሞት ቅጣት ፍርዶችም መሰረዛቸው ታውቋል።

የቫቲካን ዜና፤

በሰሜን አሜሪካ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2003 ዓ. ም. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የነጭ የበላይነትን በሚያቀነቅን፣ ባል እና ሚስትን ጨምሮ የስምንት ዓመት ልጃቸውን የገደለው ወንጀለኛ ዳንኤል ሊ ላይ የተሰጠው የሞት ቅጣት ፍርድ እንዲሰረዝ መደረጉ ታውቋል። የፍርድ ቤቱ ዳኞች በዳንኤል ሊ ላይ የተጣለውን የሞት ቅጣት ፍርድ ለማንሳት የተገደዱት በሟችች ቤተሰብ በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑ ታውቋል። የሞት ቅጣት ፍርድን የተቃወሙት ቤተሰቦች ከዚህ በፊት ለአገሪቱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕም መልዕክት ልከው እንደነበር ታውቋል።

በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተበየኑ እና በሐምሌ እና ነሐሴ መካከል ተግባራዊ ተግባራዊ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ አራት የሞት ቅጣት ፍርዶች መኖራቸው ሲታወቅ እነዚህ የሞት ቅጣት ፍርዶች እንዲሰረዙ በማለት የሃገሪቱ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት፣ ልዩ ልዩ የሐይማኖት መሪዎች እና በርካታ ሰዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸው ይታወሳል። የሐይማኖት መሪዎቹ እንደገለጹት ነፍስን ከሞት መጠበቅ እና መከላከል እንጂ ለሞት አሳልፎ መስጠት ተገቢ አይደለም በማለት ድምጻቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸው ታውቋል። ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት በአንድ ወቅት ይፋ ባደረጉት መግለጫቸው፣ የሞት ቅጣት ፍርድ ሲሰጥ የሰው ልጅ ከወደቀበት ስህተት ተመልሶ ወደ ትክክለኛው ጎዳና የሚመለስበት ተስፋ መኖሩም መዘንጋት የለበትም በማለት ማሳሰባቸው ይታወሳል። ባለፉት 45 ዓመታት ውስጥ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኩል ሦስት ሰዎች የሞት ቅጣት ፍርድ የተበየነባቸው መሆኑ ታውቋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የሞት ቅጣቱ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ ጠይቀዋል፤

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከእርሳቸው በፊት የነበሩትን ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት አቋም በመከተል፣ ለመላው ዓለም መንግሥታት ባቀረቡት ማሳሰቢያ የሞት ቅጣት ፍርድ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ በማለት በተደጋጋሚ መጠየቃቸው ይታወሳል። የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር ምን ጊዜም ቢሆን የሚሻር አይደለም ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የሰው ልጅ ነፍስ እንክብካቤ እና ጥበቃ የሚያሻው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ገልጸው፣ የሰው ልጅ ነፍስ የሌሎች ስጦታዎች እና መብቶች ሁሉ ምንጭ ነው በማለት አስረድተዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም ጥፋተኛው ጥፋቱን በማመን ምሕረትን የሚጠይቅበት ዕድል ሊነፈግ አይገባም ብለዋል።        

13 July 2020, 18:48