ፈልግ

የሰሜን እና የደቡብ ኮርያ አገሮች፤ የሰሜን እና የደቡብ ኮርያ አገሮች፤ 

የሁለቱ ኮርያዎች ሕዝቦች ሰላምን የሚናፍቁ መሆኑ ተነገረ።

በደቡብ ኮርያ የዳይጆን ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ላዛሮ ዩ ሁንግ ሲክ ለቫቲካን ኒውስ እንዳስታወቁት የሁለቱም ኮርያዎች ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት በመካከላቸው የቆየው ጥላቻ ተወግዶ ሰላም እንዲወርድ ከፍተኛ ምኞት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከቅርብ ወራት በፊት በሁለቱ ኮርያዎች መካከል ሊደረግ የተቃረበው እርቅ እየቀዘቀዘ መምጣቱ ይታወሳል። በሁለቱ ኮርያዎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ወደ ሳይደረስ ለ70 ዓመታት የዘለቀ መሆኑ ታውቋል። “የሁለቱም ኮርያዎች ሕዝቦች ወንድማማች እና እህትማማች ናቸው” ያሉት ብጹዕ አቡነ ላዛሮ፣ ይህን ግንኙነት ጠብቆ በማቆየት ወደ እርቅ እና ሰላም መድረስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የቫቲካን ዜና፤

እስከ ጎርጎሮሳዊያኑ 2018 ዓ. ም. ድረስ ሲካሄድ ቆይቶ የተቋረጠው የሰላም ውይይት መልካም ጎዳና እንደነበረው ሲነገር፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ ወዲህ መሉ በሙሉ መቋረጡ ታውቋል። የሰሜን ኮርያ እና የደቡብ ኮርያ በሚዋሰኑበት ድንበር አካባቢ የሚገኝ የሰላም ውይይት ማዕከል በሰሜን ኮርያ እጅ መውደሙ ሰሜን ኮርያ ለሰላም ያላትን ፍላጎት ማቋረጥ እንደምትፈልግ የገለጸችበት ነው ተብሏል። ሰሜን ኮርያ ከደቡብ ኮርያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቋረጥ የወሰነችው በቅርቡ ከደቡብ ኮርያ በኩል በተሰነዘረባት ወታደራዊ ጥቃት ነው ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ደቡብ ኮርያ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሰሜን ኮርያ ግዛት መበተኗ የቅርብ ጊዜ ተግባሯ እንዳልሆነ የሰሜን ኮርያ መንግሥት አስታውቆ፣ ይህም ጉዳዩን ወደ ባሰ ደረጃ ሊያደርሰው እንደሚችል አስታውቋል።

የሁለቱ ባሕረ ሰላጤው አገሮች ታሪክ እና የወደ ፊት ዕጣ ፈንታ፣

ከአሜሪካ መንግሥት ምንም የገንዘብ ድጋፍ እንዳልተደረገ የስታወሱት ብጹዕ አቡነ ላዛሮ፣ አሜሪካ ሁለቱ መንግሥታት ለሰላም እና እርቅ የሚያደርጉትን ጥረት በትዕግስት እንድትመለከተው እና የሁለቱን ኮርያዎች ሕዝቦች ምኞት በማስቀደም ለድርድር እና ለዕርቅ ያላቸውን ፍላጎት እንዲደግፉ በማለት መልዕክት የሚያቀርቡ መሆኑን አቡነ ላዛሮ አስታውቀዋል።

ለሰላም የሚደረግ ጸሎት፣

የሰሜን እና የደቡብ ኮርያዎች ሕዝቦች አንድ ሕዝቦች፣ አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወንድማማች እና እህትማማች ሕዝቦች ነን ያሉት ብጹዕ አቡነ ላዛሮ፣ በዚህ መንፈስ ተነሳስተው በሰኔ 25/2020 ዓ. ም. ለሁለቱ ኮርያዎች አንድነት እና ሰላም የሚደረግ የዘጠኝ ቀናት ዓመታዊ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። 2020 ዓ. ም. በሁለቱ ኮርያዎች ሰላም የሚወርድበት ዓመት እንዲሆን ጸሎታቸውን ወደ እግዚአብሔር ዘንድ የሚያቀርቡ መሆኑን ገልጸዋል። ከስድስት ዓመታት በፊት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ደቡብ ኮርያ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ያስታወሱት ብጹዕ አቡነ ላዛሮ፣ በጉብኝታቸው ወቅት “ሁላችንም ወንድማማቾ እና እህትማማቾች በመሆናችን ወደ አንድነት እርቅ ለመድረስ በጸሎት በመበርታት በትዕግስት መጠበቅ ያስፈልጋል” ማለታቸውን አስታውሰዋል። በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውጥረት አልረገበም ያሉት ብጹዕ አቡነ ላዛሮ፣ የአገራቸው ወጣቶች ሰላምን እንደሚናፍቁት ገልጸው፣ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ምክንያቶች ከሰላም እና እርቅ ሊያግዱን አይችሉም ብለዋል።   

18 June 2020, 19:56