ፈልግ

ጸሎት እና ጾም፣ ጸሎት እና ጾም፣ 

ግንቦት 6፥ የሐይማኖት ተቋማት ያቀረቡት ጸሎት ለፍጥረት ትኩረት እንድንሰጥ የሚያሳስብ ነበር።

በጣሊያን የሚገኙ የወንጌላዊያን ሕብረት ዛሬ ግንቦት 6/2012 ዓ. ም. የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲቆም ተብሎ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን በሳተፋቸው ታውቋል። የጸሎት ሥነ ሥርዓቱን በበላይነት ያዘጋጀው ከልዩ ልዩ የሐይማኖት ተቋማት የተወጣጡ የሰብዓዊ ወንድማማችነት ምክር ቤት ከፍተኛ ኮሚቴ መሆኑ ሲታወቅ በዚህ ምክር ቤት ውስጥ የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረትም እንደሚገኝበት ታውቋል። በኮሮርና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በስቃይ ላይ ለሚገኝ የዓለማችን ሕዝብ አንድነታቸውን የገለጹት የልዩ ልዩ እምነት ተከታዮች እና መላው የዓለም ሕዝብ መሆኑን መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።

የቫቲካን ዜና፤

መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ በቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ በዓለማችን የተዛመተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ ሕዝቦች የኑሮ ስልታቸውን በመቀየር ለእግዚአብሔር ፍጥረታት የሚገባውን ክብር እንዲሰጡ የሚያሳስብ ነው ብለዋል። ግንቦት 6/2012 ዓ. ም. በዓለም ሕዝቦች ዘንድ የተፈጸመው የጸሎት እና የጾም ሥነ ሥርዓት ይህን ከፍተኛ ግንዛቤን ያረጋግጣል በማለት በጣሊያን የባፕቲስት ቤተክርስቲያን መጋቢ እና የወንጌላዊያን ሕብረት ፕሬዚደንት የሆኑት መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ አስገንዝበዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን “ሁላችንም በአንድ ጀልባ ውስጥ ተሳፍረን እንገኛለን” ያሉትን ያስታወሱት መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ፣ የልዩ ልዩ እምነት ተከታዮች በሕብረት ሆነው የመጸለይ አስፈላጊነትን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ ብለው፣ የዓለማችን ሐይማኖቶች አንዱ ሌላውን በመቃረን ላይ በሚገኙበት ባሁኑ ጊዜ ከሁሉም በላይ ሰብዓዊ አንድነትን ማስቀደም እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተው፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲቆም በማለት የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት በጋራ ለመጸለይ ፍላጎታቸውን መግለጻቸው መልካም ተስፋ መሆኑን መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።

ይህ ወቅት የአኗኗር ዜይቤአችንን እንድንቀይር ያሳስበናል፣

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲቆም በማለት ግንቦት 6/2012 ዓ. ም. በዓለም ዙሪያ የተካሄደው የጸሎት እና የጾም ሥነ ሥርዓት፣ ብዙ ነገሮችን እንድናስተነትን ጋብዞናል የሉት መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ፣ ዓላማው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተጎዱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጎን በመሆን እርዳታችንን እንድናቀርብላቸው የሚያሳስብ መሆኑን ገልጸው፣ መጋቢ ሉካ በማከልም የጋራ ጸሎቱ የአኗኗር ዜይቤአችንን እንድንቀይር፣ ከራስ ወዳድነት እንድንላቀቅ፣ በተፈጥሮ ላይ የሚደረግ ምሕረት የለሽ ብዝበዛን እንድናቆም፣ በምድራችን ላይ ለሚገኙት ነፍሳት በሙሉ ክብርን እንድንሰጥ የሚያሳስብ ነው ብለዋል። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኩል የደረሰብን ስቃይ እንዳይቀጥል ለማድረግ ከፈለግን ያልተስተካከሉ የኑሮ ዜይቤአችንን መቀየር አለብን በማለት መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

የጋራ ወንድማማችነት አስፈላጊነት መንከባከብ ያስፈልጋል፣

በዛሬው ዓለማችን የሰው ልጅ በተለያዩ ግድግዳዎች፣ አጥሮች እና ጭፍን አመለካከቶች ተለያይቶ ይገኛል ያሉት መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ፣ የጋራ ስብዕናችንን ማወቅ፣ የሰው ልጆች መሠረታዊ ወንድማማችነት፣ ሰላማዊ ዓለምን ለመገንባት እንደሚያግዝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። መጋቢ ሉካ ማርያ ኔግሮ በመጨረሻም የሰብዓዊ ወንድማማችነት ምክር ቤት ያቀረበው መልዕክት ከፍተኛ ተኩረት የሚሰጠው መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ካልሆነ ግን ወደሚፈለገው ግብ መድረስ አንችልም ካሉ በኋላ፣ በልዩ ልዩ እምነት ተከታዮች ዘንድ እውነተኛ ወንድማማችነትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።                     

14 May 2020, 19:36