ፈልግ

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በአውሮፓ ፓርላማ ላይ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በአውሮፓ ፓርላማ ላይ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ፣ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ “አውሮፓ የቀድሞ አባቶች የአንድነት ጎዳና መከተል ይኖርበታል”።

አውሮፓ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አስቸጋሪ ጊዜን በመጋፈጥ ላይ እንደሚገኝ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት ጥንታዊው የአውሮፓ አህጉር ወደ ነበርበት ደረጃ ለመመለስ የቀድሞ አባቶች ህልም መከተል አስፈላጊ መሆኑ ተመልክቷል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስም ይህን ሕልም “እውነተኛ የአንድነት ሕልም” ማለታቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

መጭው ግንቦት 1/2012 ዓ. ም. የአውሮፓ አገሮች አንድነት የተመሰረተበት 35ኛ ዓመት የሚከበርበት ዕለት መሆኑ ታውቋል። ዘንድሮ የሚከበረው የአውሮፓ ቀን አንዳንድ የአውሮፓ ሕብረት አገሮች ወደ ተረጋጋ ማኅበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ህደት ለመመለስ የመጀመሪያ ሙከራ ያደረጉበትን አጋጣሚ እንዲያስታውሱ ሲጋብዝ ፣ ዘንድሮ የሚከበረው 35ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ለተቀሩት አገሮች ልዩ ትዝታን ፈጥሮ የሚያልፍ እንደሚሆን ተመልክቷል። አንዳንዶች በቅርብ ወራት ውስጥ ከገቡበት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመውጣት ደፋ ቀና የሚሉበት ወቅት እንደሚሆን ታውቋል። 35ኛ ዓመት በዓሉ የአውሮፓ አገሮች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ያጋጠማቸው ቀውስ፣ በጋራ ሆነው፣ አንዴ ቆም ብለው እንዲያስቡበት የሚጋብዛቸው ነገር ቢኖር፣ የአውሮፓ የጋራ ማንነትን እና ተልዕኮ መሆኑ ታውቋል። በቁጥር ጥቂት የሆኑ አውሮፓውያን ይህን ቀን የራሳችው አድርገው ሲመለከቱት እጅግ ጥቂቱ ደግሞ ዕለቱ ለምን እንደተመረጠ ያስተውላሉ ተብሏል።

ዘንድሮ የአውሮፓን ምስረታ 70ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል እንደሚከበር የተነገረ ሲሆን እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ግንቦት 9/1950 ዓ. ም. የአውሮፓ ቀን መታሰብ በተጀመረበት ወቅት በወቅቱ የፈረንሳይ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮቤርት ሹማን ታሪካዊ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል። አቶ ሮቤርት ሹማን በዚህ ንግግራቸው ስድስት የሚሆኑ የአውሮፓ አገሮች ተባበረው የኢንዱስትሪ ምርታቸውን ለማቅረብ ሃሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል። ይህ ውጥናቸው ወደ ሌሎች የአውሮፓ አገሮች በመድረስ ከአርባ ዓመት በፊት ለተመሰረተው የአውሮፓ ሕብረት መንገድ መክፈቱ ይታወሳል። በወቅቱ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ሮበርት ሹማን ሃሳባቸውን ባቀረቡበት ወቅት የአውሮፓ አገሮች ወደ ትኩስ ጦርነት የገቡበት ጊዜ በመሆኑ ይህን ጦርነት መከላከል የሚቻለው ሰላምን እና አንድነትን በመፍጠር ብቻ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማከልም “አውሮፓ በአጭር ቀናት ውስጥ ብቻ ወይም በአንድ ውጥን ብቻ መመስረት አይቻልም” ብለው የአውሮፓ አግሮች በመካከላቸው አንደነትን ማምጣት የሚችሉት ተጨባጭ የሆኑ መልካም ውጤቶችን በማስመዝገብ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል። ስድስቱ የአውሮፓ አገሮች የኢንዳስትሪ ምርት አምራች ሕብረት ቀዳሚ ዓላማ፣ በተለይም ፈረንሳይና ጀርመን በኅብረት የሚያመርቱት የኢንዳስትሪ ምርቶች በአገራቱ መካከል ልዩነት ሳይፈጥር ወደ ሁሉም የዓለማችን ክፍሎች በመዳረስ፣ የሰዎችን የኑሮ ደረጃን ከፍ በማድረግ ሰላማዊ እድገት ለማስመስገብ የታለመ መሆኑ ታውቋል። የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሮቤርት ሹማን ትንቢታዊ ንግግር ከበርካታ ዓመታት በኋላ የአውሮፓ ምክር ቤት በጣሊያን ከተማ ሚላኖ፣ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ሰኔ ወር 1985 ዓ. ም. በተደረገ የአውሮፓ ቀን ጉባኤ ላይ መጠቀሱ ይታወሳል።

የአውሮፓ ቀን መታሰቢያ በዓል የአውሮፓ አገሮች ህልማቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት መከበሩ፣ የሕብረቱ መስራች አባቶች በወቅቱ ያጋጠማቸውን ችግር ለማሸነፍ የወሰዱትን እርምጃ ዛሬ የአውሮጳ ኅብረት አገሮች መሪዎችን ካጋጠማቸው ችግር ጋር በምንም መልኩ የሚወዳደር አለመሆኑ ተመልክቷል። የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛን መልዕክት ስናስተውስ ”ከሥነ-ምግባር ጋር የተዛመደ በመሆኑ ተጨባጭ በሆነ ተግባራቸው የሚታወቁ ፖለቲከኞች ፖለቲካ ንፁህ እንዳልሆነ ይረዱት ነበር” ማለታቸው ይታወሳል። በትውልድ አውሮፓዊ ያልሆኑት የመጀመሪያው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተናገሩት እና የቀድሞ የአውሮፓ አባቶች የተከተሏቸውን መልካም እሴቶች የአውሮፓ ኅብረት አገሮች መሪዎችን እና ሕዝቦች ልብ መንካቱ ያታወሳል። በቅርቡ በተከበረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መታሰቢያ በዓል ዕለት ለሮም ከተማ እና ለዓለም ሕዝብ ያስተላለፉት መልዕክትም ክርስቲያኖችን እና ክርስቲያን ያልሆኑ ወገኖችን ልብ መንካቱ ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአውሮፓ አገሮች ከወደቁበት መነሳት መቻላቸውን አስታውሰው ለዚህም የበቁት በመካከላቸው አንድነትን እና መተጋገዝን በማምጣታቸው መሆኑን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም የመከፋፈል እና ራስ ወዳድነት ቫይረስ የተወገደው በአንድነት እና በኅብረት ክትባት፣ ወይም ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሚመች አገላለጽ “በሰብዓዊ ወንድማማችነት” ሊወገድ ችሏል።

ዛሬ ላይ ሆነን የወደፊቱን ለማቀድ ያለፉ ታሪኮችን ማስታወሱ ምንም ዓይነት አስተማማኝ ነገር በሌለበት ጊዜም አስፈላጊ በመሆኑ ተመልክቷል። ከሩቅ የዓለማችን ክፍል የመጡት እና ከጥንታዊት አውሮፓ ከተሰደዱት ቤተሰቦች የተወለዱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህን ሃቅ በቫቲካን እና በስትራስቡርግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ማስታወሳቸው ሲታወቅ በአውሮፓ አገሮች፣ የፖለቲካ እና የኤኮኖም ማዕከል ባልሆኑ፣ በአልባንያ እና በቅርቡም ወደ ሮማኒያ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ወቅትም መናገራቸው ይታወሳል። ምናልባትም ርዕሥ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮሶ እጅግ አስደናቂ በሆነ መንገድ የአውሮፓን ጥንታዊ ታሪክ በማብራራት የተናገሩት፣ የቻርልማኝ ሽልማት አሸናፊ የሆኑት አውሮፓዊ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐስን ጳውሎስ ዳግማዊ ፈለግ የተከተሉ ሁለተኛ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት እንደሆኑ ይነገርላቸዋል። እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በግንቦት 6/2016 ዓ. ም. ለአውሮፓ ተቋማት መሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት የኤሊ ዊስል ንግግር በማስታወስ በአውሮፓ ውስጥ የቀድሞ ትዝታዎችን ለአዲሱ ትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል ማለታቸው ይታወሳል።  በናዚ ወሂኒ ቤቶች የደረሰባችውን ስቃይ ተቋቁመው በሕይወት ለሚገኙት ባደረጉት ንግግር ከዚህ በፊት የተፈጸሙ ጥፋቶች እንዳይደገሙ መፍቀድ የለብንም ካሉ በኋላ፣ እነዚያ ጥፋቶች ህዝባችን ያጋጠሟቸውን ታሪካዊ መንገዶች በጥሩ ሁኔታ እንድንመለከታቸው የረዱን ናቸው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለአውሮፓ ያላቸው ህልም ከቀድሞ የአውሮፓ ኅብረት መስራች አባቶች ህልም ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ታውቋል። ቅዱስነታቸው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ሰኔ 2/2019 ዓ. ም. ወደ ሮማንያ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ሲመለሱ እንደተናገሩት፣ ወደ ቀድሞ የአውሮፓ ኅብረት መስራች አባቶች ህልም መመለስ ያስፈልጋል ማለታቸው ይታወሳል። ይህ ህልምም ከምን ጊዜም በላይ ለአውሮፓ አስፈላጊ የሆነው አንድነት ነው። የሮም ስምምነት በ60ኛ ዓመት መታሰቢያ ወቅት ለአውሮፓ ኅብረት አገራት መሪዎች ባደረጉት ንግግር፣ አውሮፓ ተስፋን የምታገኘው አንድነትን በመፍጠር ነው ብለው፣ እነዚህን ፍላጎቶችን በተግባር በመግለጽ መሆኑን አስረድተዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም በአውሮፓ ውስጥ አንድነትን ለመጀመር ስናስብ አውሮፓዊያኑ በተጓዙበት መንገድ መሆን አለበት ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር መጋቢት 24/2017 ዓ. ም. ይህን ከተናገሩ ከሦስት ዓምታት በኋላ፣ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ አውሮፓ መሸከም ከምትችለው ስቃይ በላይ ሞትን እና መከራን በማስተናገድ ላይ መሆኗ ታውቋል። የአውሮፓ ኅብረት አገሮች በተናጠል ሊወጡት የሚችሉት ቀውስ አለመሆኑን በመገንዘብ አንደነታቸውን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሳስበዋል።                                     

21 April 2020, 18:29