ፈልግ

የጦር መሣርያዎች እያስከተሉ የሚገኙትን ውድመት የምንቃወምበት አለም አቀፍ ቀን ተከበረ። የጦር መሣርያዎች እያስከተሉ የሚገኙትን ውድመት የምንቃወምበት አለም አቀፍ ቀን ተከበረ። 

የጦር መሣርያዎች እያስከተሉ የሚገኙትን ውድመት የምንቃወምበት አለም አቀፍ ቀን ተከበረ።

በጦርነት ጊዜያት እና በትጥቅ ትግሎች የተነሳ በአከባቢያችን እና በምድራችን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ጥቃት እና የሚፈጸሙትን ጥፋቶች የምንቃወምበት ዓለም አቀፍ ቀን ዛሬ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ መዋሉ ይታወቃል። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለው ቀን ለተፈጥሮ ሀብቶቻችን ጥበቃ ማደረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላምን ለማስከበር የሚደረጉትን ጥረቶች እውን ለማደረግ የሚያስችል ስልት ነው።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የማነኛውም ዓይነት ግጭቶች እና ጦርነቶች ሰለባ ወታደሮች እና ሲቪሎች ብቻ አይደሉም። የትጥቅ ትግል ግጭቶች ታሪካዊ ገጽታ የሚያሳየው በግጭቶች እና በጦርነቶች አማካይነት የሚወድሙት ታሪካዊ ስፍራዎች እና ከተሞች፣ እንዲሁም የሚያስከተለው ስደት እና መከራ ብቻ አይደለም።  ብዙን ጊዜ እኛ የምንዘነጋው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎጂ የሆኑ፣ ነገር ግን ሊታዩ የማይችሉ ጠባሳዎችን የሚያስከትለው በጦር መሳሪያዎች የተነሳ በምድራችን ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደ ሚያስከትል እና በአከባቢ የአየር ንበረት ለውጥ ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽኖ እንደ ሚያስርፍ እሙን ነው። በጦርነቶች እና በጦር መሳርያዎች አማካይነት በሚከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ በምድራችን ላይ የሚድረሰውን ከፍተኛ ውድመት ለመከላከል ታስቦ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተሰየመው ዓለም አቀፍ ቀን ዛሬ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።

በምድራችን ላይ የተከሰቱ ቁስሎች አሁንም ክፍት ናቸው

በጦርነቶች አማካይነት በአካባቢያችን እና በምድራችን ላይ ባስከተለው ጥፋት ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ የጤና እክል እና ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ይታወቃል። የቤልጅየም እና የፈረንሳይ ግዛቶች አንደኛው የዓለም ጦርነት በተካሄደበት ወቅት በጦር መሳሪያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ በዋሉ ከባድ ብረቶች እና ባሩዶች ባስከተሉት ብክለት እይተሰቃዩ ይገኛሉ። በአፍጋኒስታን ለባለፉት አስር ዓመታት ያህል በጦር መሣሪያ ድጋፍ እየተካሄዱ በሚገኙት ግጭት ምክንያት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የሀገሪቱ ደኖች ወድመዋል ወይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በኮሎምቢያ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ለአስር አመታት ያህል በተካሄዱት ጦርነቶች ሳቢያ የአገራቱ ስነ-ምህዳር በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጎዳ አድርጉዋል።

የአከባቢ ስነ-ምህዳር ወይም የምድራችን አቀማመጥ በተጓዳኝ እንደ ጦር መሳርያ ጋሻ ሆኖ አገልግሏል-ለምሳሌ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት  የጦር ሠራዊቶችን እንቅስቃሴ ለመግታት የውሃ መንገዶች በመቀየር ወይም በመለወጥ መንገዶችን ለመዝጋት በተደረጉ ጥረቶች ሳቢያ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እንዲከሰት ምክንያት ሁኑዋል፣ ይህም ከፍተኛ የአፈር መሸርሸር እንዲከሰት አድርጉዋል። የጠላትን ተዋጊዎች ለማጥፋት በቪዬትናም ከፍተኛ የሆነ መጠን ያለው ጥቅጥቅ ደን በኬሚካል እንዲወድም እና እንዲቃጠል ተደርጉዋል። የትጥቅ ትግል ግጭቶች የሚያስከትሉት አደጋ አሁንም ቀጣይነት ያለው ሲሆን ከከፍተኛ የዝናብ መጥን እና ከከፍተኛ ሙቀት ጋር በተያያዘ መልኩ በፕላስቲክ ብክለቶች እና መርዛማ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ከምድራችን የውሃ ምንጮች ጋር በመገናኘት አከባቢያችንን እና በአከባቢያችን ላይ የሚኖሩ ሕያዋን ፍጥረታትን እየመረዙ እና እየበከሉ ይገኛሉ። ዛሬም ቢሆን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለማስፋፋት በሚደረጉ ጥረቶች ሳቢያ የውሃ ጉድጓዶች ተበክለዋል ፣ ሰብሎች ተቃጥለዋል፣ መሬታችን መርዛማ በሆኑ ንጥረ ነገሮች ተበክላለች።

የጦር መሳርያዎች በአከባቢያችን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጣፍት ያስከትላሉ

“ጦርነት ሁል ጊዜ በአካባቢያችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በላቲን ቋንቋ Laudato si በአማርኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በተሰኘው ሐዋርያዊ ምልእክታቸው ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን  “አንዳንድ የተፈጥሮ ሐብቶቻችን እየተሟጠጡ በሚሄዱበት ጊዜ ለአዳዲስ ጦርነቶች ምቹ ሁኔታን መፍጠር እንጀምራለን” በማለት በአጽኖት መግለጻቸው ይታወሳል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስነታቸው ሲናገሩ . . .

ጦርነት ሁል ጊዜ በአካባቢያችን እና በሰዎች ባህላዊ ብልጽግና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፣ በተለይም ደግሞ በኒውክሌር እና ባዮሎጂካል በሆኑ መሳርያዎች ምክንያት የሚቃጣው ጦርነት ጉዳቱን ወይም ውድመቱን የከፋ ያደርገዋል። በእርግጥ ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የኬሚካል እና ባዮሎጂካል የሆኑ መሳርያዎችን ተጠቅሞ ጦርነት ማካሄድ የሚከለክል ቢሆንም የተፈጥሮ ሚዛንን ሊቀይሩ የሚችሉ አዳዲስ አፀያፊ የጦር መሳሪያዎችን ለማምረት የሚደረገው ጥረት አሁንም ቢሆን በምርምር ጣቢያዎች ውስጥ እንደቀጠለ ነው።

አከባቢ እና ሰላም

በጦርነት ጊዜያት እና በትጥቅ ትግሎች የተነሳ በአከባቢያችን እና በምድራችን ላይ እየደርሰ የሚገኘውን ጥቃት እና የሚፈጸሙትን ጥፋቶች የምንቃወምበት ዓለም አቀፍ ቀን ዓላማው ጦርነት እና የትጥቅ ትግል ግጭት በአከባቢው ላይ ስለሚያስከትለው ጉዳት ያለንን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ የሚከበር ቀን ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2030 ዓ.ም ባስቀመጠው የልማት ግብ “ሰላምና ደህንነት ሳይኖር ዘላቂ ልማት ሊገኝ እንደማይችል” በግልፅ ያስቀምጣል። ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግጭትን መከላከል እና የሰላም ማስከበር ተግባር ዓላማ ለማስጠበቅ ከተደረጉት ሰፊ ስልታዊ እንቅስቃሴዎች መካከል ተቀዳሚ መሆን አለባቸው። በእርግጥ የተፈጥሮ ሀብቶች ከወደሙ እና የምድር እና የሥነ-ምህዳር ሚዛን ከተዛባ ለዘላቂ ሰላም ዋስትና አይሰጥም።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
06 November 2019, 15:46