ፈልግ

እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም 820 ሚልዮን ሕዝቦች በቂ ምግብ እንዳልነበራቸው ተገለጸ። እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም 820 ሚልዮን ሕዝቦች በቂ ምግብ እንዳልነበራቸው ተገለጸ።  

እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም 820 ሚልዮን ሕዝቦች በቂ ምግብ እንዳልነበራቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ላይ እንደ ገለጸው እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም በአለማችን ውስጥ የሚገኙ 820 ሚልዮን ሕዝቦች በቂ ምግብ እንዳልነበራቸው መዘገቡ የታወቀ ሲሆን ይህንን ሪፖርት በተመለከተ ቅድስት መንበርን በመወከል በተባበሩት መንግሥታ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ቋሚ ታዛቢ የሆኑት የእኔታ አባ ፈርናዲ ኪካ አሬላኖ እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታየውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ከእዚህ የተሻለ ጥረት ሊደረግ ይችል እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን የምግብ እጥረት የሚታይባቸው አገራት ያላቸውን ችግር ለመፍታት በአለማቀፍ ደረጃ ትብብር ማደረግ እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

“ሰብአዊው ማሕበረሰብ በጣም ድሃ የሆኑትን ወንድሞቹን የመርዳት ግዴታውን በቂ በሆነ ሁኔታ አልተገበረውም” በማለት የተናገሩት ቅድስት መንበርን በመወከል በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ቋሚ ታዛቢ የሆኑት የእኔታ አባ ፈርናዲ ኪካ አሬላኖ በኒዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት በዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ላይ ተተርሶ በወጣው የ2019 ዓ.ም ጉባሄ ላይ የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO)፣ አለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ (IFAD)፣ የአለም የምግብ ፕሮግራም (PAM)፣ በተባበሩት መንግሥታ የሕጻናት መርጃ ድርጅት፣ ዜሮ ረሃብ የተባሉ ድርጅቶች ይህንን ስብሰባ መታደማቸው የተገለጸ ሲሆን እነዚህ ቀድም ሲል የተጠቀሱ ድርጅቶች እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተጉ የሚገኙ ድርጅቶች መሆናቸውም ጨምሮ ተገልጹዋል።

ለባለፉት ተከታታይ ሦስት አመታት በአለም አቀፍ ደረጃ የምግብ እጥረት ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ቅናሽ አለማሳየቱ በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም 820 ሚልዮን ሕዝቦች በቂ የሆነ ምግብ አለማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ቁጥር እ.አ.አ. በ 2017 ዓ.ም 811 በቂ ምግብ ከማያገኙ ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም በቂ ምግብ ያላገኙ ሰዎች ቁጥር በዘጠን ሚልዮን ከፍ ማለቱ ተገልጹዋል።

እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም ጤናማ ከሆነ የሰውነት ክብደት በታች ሆነው የተወለዱ ሕጻናት 20.5 ሚልዮን እንደ ነበሩ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅ ካወጣው ሪፖርት ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም በአዐዝ ሲገለጽ ከሰባት ሕጻናት መካከል አንዱ ጤናማ ከሆነ የሰውነት ክብደት በታች ሆኖ የሚወለድ እንደ ሆነም ተገልጹዋል። በአሁኑ ወቅት በአለም ደረጃ ከአምስት አመት እድሜ በታች የሆኑ 148.9 ሚልዮን ሕጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸውን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጹዋል። በተለይም ደግሞ ዘገምተኛ የሆነ የኢኮንሚ እድገት ባላቸው አገራት ውስጥ የሚከሰተው ረሃብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለጸው የተባበሩት መንግሥታት ድረጅ ሪፖርት በተለይም መካከለኛ ገቢ ያላቸውና ጥሬ ዕቃዎችን ለዓለም አቀፉ ገበያ በማቀረብ ላይ በሚገኙ አገራት ውስጥ ረሃብ እየጨመረ እንደ ሚገኝ ዘገባው ጨምሮ ያትታል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት ጨምሮ እንደ ገለጸው ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ውፍረት ያላቸው ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመሩ መምጣታቸውን የገለጸ ሲሆን ከልክ ያለፈ ውፍረት በመላው ዓለም በተለይም በትምህርት ገበታ ላይ በሚገኙ ህጻናት እና አዋቂዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተዋል እንደ ሚገኙ ሪፖርቱ ይፋ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ አህጉራት በተለይም ደግሞ በላቲን አሜሪካ ውስጥ ከወንዶች ይልቅ የላቀ ቁጥር ያላቸው ሴቶች በምግም እጥረት እንደ ሚጠቁ ሪፖርቱ ያሳያል።

ቅድስት መንበርን በመወከል በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ቋሚ ታዛቢ የሆኑት የእኔታ አባ ፈርናዲ ኪካ አሬላኖ ይህንን በተመለከተ ከቫቲካን ዜና ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት “በእንደዚህ ዓይነት የምግብ እጥረት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች እና ሕዝቦች ብሩህ የሆነ የወደፊት ጊዜ እንደ ማይታያቸው” የገለጹ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማኅብረሰብ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ይችላ ዘንድ በርትቶ ሊሥራ እንደ ሚገባው ገልጸው በተለይም ግጭቶች፣ ጦርነቶች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና የአየር ንብረት ለውጥ የመሳሰሉት በሰው ልጆች አማካይነት የሚከሰቱ ችግሮችን ለማስወገድ የአለማቀፉ ማኅበረሰብ ቁርጠኛ ፈቃድ እንደሌለው አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

ከእስያ እና ከአፍሪካ አህጉር የሚመጡ የእርዳታ ጥሪዎች

የተመጣጠነ ምግብ ችግር እየተጠቁ ከሚገኙ 500 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሚገኙት በደቡባዊው የእስያ ክፍል እንደ ሆነ ያመለከተው ሪፖርቱ በአፍሪካ አህጉር አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በረሃብ እና በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር በርካታ እንደ ሆነ ሪፖርቱ አክሎ ገልጹዋል። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በበኩሉ እንደ ገለጸው ሁሉም የአለማችን ሕዝቦች ረሃብን ለማጥፋት የበኩላቸውን ርብርብ ማደረግ እንደ ሚገባቸው የገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ  በአደጉ አገራት የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የምግብ ብክነት በማስወገድ በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ አገራትን ማገዝ እንደ ሚገባ ገልደዋል።

በዓለም ደረጃ የሚታየውን የምግብ እጥረት ለማስወገድ ከሚደረገው የእርሻ ልማት ሥራዎች ጋር በተያያዘ መልኩ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ውስጥ የሚስተዋሉትን ግጭቶች ለመፍታት መሞከር እና ሰላም እንዲረጋገጥ ማደረግ እንደ ሚገባ የገለጸው ሪፖርቱ እ.አ.አ በ2030 ዓ.ም ላይ ከረሃብ የጸዳ አለም ለመፍጠር የሚድረገውን ጥረት ሁሉም በተቻለው አቅም አለማቀፉ ማኅበረሰብ ሊደግፍ እንደ ሚገባው ሪፖርቱ ይገልጻል።

በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ በምግብ እጥረት እና በረሃብ ከሚሰቃዩ ሰዎች ውስጥ 513.9 ሚልዮን ሰዎች በኢስያ አህጉር የሚገኙ ሲሆን፣ 256.1 ሚልዮን ሕዝቦች ደግሞ በአፍሪካ አህጉር፣ የተቀሩት 42.5 ሚልዮን ሕዝቦች ደግሞ በላቲን አሜሪካ አገራት ውስጥ እንደ ሚገኙ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅ ካወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት  እ.አ.አ በሐምሌ 16/2019 ዓ.ም ያወጣው አመታዊ ሪፖርት በምግብ እጥረት እና በረሃብ ከሚሰቃዩ ሰዎች ባሻገር ከእዚህ ተቃራኒ በሆነ መልኩ ከመጠን በላይ በመመገባቸው የተነሳ ለከፍተኛ ከመጠን ያለፈ ውፍረት የተዳረጉ ሕዝቦችን ጭምር በሪፖርቱ ውስጥ ያመላከተ ሲሆን ከመጠን በላይ በሆነ የሰውነት ውፍረት ያላቸው ወጣቶች ቁጥር በአለም ደረጃ 672 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች በከፍተኛ ውፍረት የተነሳ እየተሰቃዩ እንደ ሚገኙ ሪፖርቱ ጨምሮ የገለጸ ሲሆን ይህ አሃዝ በመቶኛ ሲሰላ 13% የሚሆኑ የአለማችን ሕዝቦች (ከስምንት ሰዎች ከማከል አንዱ ማለት ነው) ከመጠን በላይ በሆነ የሰውነት ውፍረት እንደ ሚሰቃይ ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጹዋል።

ከእዚህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅ ሪፖርት የምንረዳው ችግሩ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በሚታየው የምግብ እጥረት እና ረሃብ ከሚሰቃዩ ሰዎች ባሻገር ከመጠን በላይ በሆነ የሰውነት ውፍረት ምክንያት ጭምር የሚክሰተውን ችግር ያመላከተ ሪፖርት ሲሆን ይህንን ሁለት ጽንፍ የረገጠውን የአአለማችን ችግር ለመፍታት የአለማቀፉ ማሕበርሰብ ተባብሮ መሥራት እንደ ሚገባው ቅድስት መንበርን በመወከል በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ቋሚ ታዛቢ የሆኑት የእኔታ አባ ፈርናዲ ኪካ አሬላኖ መልእክት አስተላልፈዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
16 July 2019, 14:48