ፈልግ

የኢቦላ ወረርሽን በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፤ የኢቦላ ወረርሽን በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፤  

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የኢቦላ ወረርሽን መከሰቱ ተገለጸ።

የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጎማ ከተማ ነዋሪዎች እንዲረጋጉ አሳስቦ በአካባቢው ቫይረሱ መኖሩ አስቀድሞ በመታወቁ የመዛመት ዕድሉን ይቀንሰዋል ብሏል።

በአገሪቱ ምስራቃዊ ክፍለ ሀገር፣ ጎማ በተባለ አካባባቢ የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝ ምልክት መታየቱን የአካባቢው የመንግሥት ባለ ስልጣን አስታውቋል። በቁጥር ወደ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት ጎማ ከሩዋንዳ ጋር የምትዋሰን ከተማ መሆኗ ታውቋል። ያለፈው ዓመት በመላው ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የተከሰተው ተላላፊ ትኩሳት የጎማ ከተማ ነዋሪዎችን በማጥቃት ለበርካታ ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። አሁን በጎማ ለታየው የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት የሆነው ያለፈው እሑድ በሕዝብ ማመላለሽ አውቶቡስ ተሳፍሮ ወረርሽኙ ክፉኛ ካጠቃው ከቡቴምቤ ከተማ ተነስቶ ወደ ጎማ የገባው እና የቫይሬሱ ተሸካሚ ግለሰብ ነው ተብሏል። ግለሰቡን አሳፍሮት የነበረው የሕዝብ ማመላለሻ፣ ሾፌሩን ጨምሮ ሌሎች 18 ስምንት ሰዎችን ይዞ መጓዙ ታውቋል። የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጎማ ከተማ ነዋሪዎች እንዲረጋጉ አሳስቦ በአካባቢው ቫይረሱ መኖሩ አስቀድሞ በመታወቁ የመዛመት ዕድሉን ይቀንሰዋል ብሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቫይረሱ በምዕራብ አፍሪቃ የአንድ ሚሊዮን ሰዎች መሞት ምክንያት ሆኗል፣

የኢቦላ ቫይሬስ ካለፈው የጎርጎሮሳዊያኑ 2018 ዓ. ም. ጀምሮ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ምስራቃዊ ክፍላተ ሀገራትን ክፉኛ ሲያጠቃ የቆየ መሆኑ ሲታወቅ ቀጥሎም በጎርጎሮሳዊው 2013 እና 2014 ዓ. ም. መካከል ወደ ምዕራብ አፍሪቃም በመዛመት፣ በጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን በድምሩ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ታውቋል። የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያመለከተው ባለፉት አጭር ጊዜያት በአገሪቱ ውስጥ 1,655 በቫይረሱ ተይዘው መሞታቸውንና 694 ሰዎች ደግሞ ፈጣን ሕክምና ተደርጎላቸው ከበሽታው መፈወሳቸውን አስታውቋል።

የድንበር የለሽ ሕኪሞች ስጋት፣

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፣ ጎማ ከተማ የታየው የኢቦላ ቫይሬስ እንዳሳሰበው በአካባቢው በሕክምና አገልግሎት ላይ ተሠማርቶ የሚገኝ፣ የድንበር የለሽ ሕኪሞች ቡድን አስታውቋል። የድንበር የለሽ ሕኪሞች ማሕበር ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ሩጄሮ ጁሊያኒ ለቫቲካን ሬዲያ ጣሊያንኛ ቋንቋ ክፍል እንዳስረዱት በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ምስራቃዊ ክፍል ከፍተኛ የሕዝቦች ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ሁኔታ ይታያል ብለው ይህም ቫይሬሱን ለማዛመት ከፍተኛ አስተዋጽዖን ያበረክታል ብለዋል። ይህን ችግር ለማቃለል ታስቦ የተዘረጋ እቅድ ተገባራዊ እየሆነ ይገኛል ብለው በአካባቢው በቁጥር በርካታ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን፣ የሕክምና መሣሪያዎች መመደባቸውን እና አዳዲስ የመከላከያ መድሐኒቶች መከፋፈላቸውን አስረድተው ይህ በመሆኑ በርካታ የቫይሬሱ ተጠቂዎችን ለመፈወስ ተችሏል ብለዋል። አሁንም ቢሆን ብዙ ሥራ መሠራት ይኖርበታል ያሉት አቶ ሩጄሮ ጁሊያኒ በተለይም የቫይሬሱ ተጠቂዎች የበሽታው ምልክት ሲሰማቸው ፈጥነው ወደ ሕክምና መስጫ ጣቢያዎች መምጣት እንዳለባቸው ማሳመን ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
16 July 2019, 17:29