ፈልግ

በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ የየመን ሕጻናት በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ የየመን ሕጻናት 

በጦርነት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት ለመሐይምነት ይዳረጋሉ።

ድርጅቱ በተጨማሪም የትምህርት እድል የተነፈገ ሕጻን ለአመጽ፣ ለጭቆና እና ለሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እንደሚጋለጥ ገልጾ በተለይም ሴቶች የትምህርት እድል የማያገኙ ከሆነ ከማሕበረሰቡ መካከል እንዲገግለሉ እና ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚጋለጡ አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት “ዩኒሴፍ” በቡርኪና ፋሶ፣ በማሊ እና በኒጀር 400, 000 የሚሆኑ ወጣቶች በጦርነት እና በአካባቢያቸው አለመራጋጋት ምክንያት ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን አስታውቋል። የሕጻናት መርጃ ድርጅት በማከልም እድሜአቸው ከ5 እስከ 17 ከሚሆናቸው 5 ልጆች መካከል አንዱ በየቀኑ ከትምህርት ገበታ ላይ እንደሚቀር ገልጿል። በዓለም ደረጃ የተመለከትን እንደሆነ ወደ 300 ሚሊዮን የሚጠጉ ልጆች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ አስታውቆ ከእነዚህም መካከል ወደ 100 መቶ ሚሊዮን የሚጠጉ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡት በጦርነት እና ጦርነት በሚያስከትልው ቀውስ እና አደጋ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል። ድርጅቱ በተጨማሪም የትምህርት እድል የተነፈገ ሕጻን ለአመጽ፣ ለጭቆና እና ለሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እንደሚጋለጥ ገልጾ በተለይም ሴቶች የትምህርት እድል የማያገኙ ከሆነ ከማሕበረሰቡ መካከል እንዲገግለሉ እና ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚጋለጡ አስታውቋል።

በቡርኪና ፋሶ፣ በማሊ እና በኒጀር 2000 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣

በዓለማችን ውስጥ በርካታ ሕጻናት በተለያዩ ማሕበራዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ የተገደዱት በሰሜን አፍሪቃ የሚገኙ አገሮች ሲሆኑ፣ በቡርኪና ፋሶ፣ በማሊ እና በኒጀር ወደ 2000 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች በአመጽ እና በጦርነት ምክንያት መዘጋታቸውን ወይም የትምህርት አገልግሎትን እንዳይሰጡ መታገዳቸውን በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት አስታውቋል። በዚህም ምክንያት 400 ሺህ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ፣ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መምህራንም ከሥራ  ገበታቸው እና ከመኖሪያቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን ድርጅቱ አክሎ አስታውቋል።

ትምህርት የሰላም መሠረት ነው፣

በትምህርት ተቋማት ላይ፣ በተማሪዎች፣ በመምህራን ላይ የሚደርስ ጥቃት እና የትምህርት ተቋማት በሚገኙባቸው ስፍራዎች የሚደረጉ ወረራዎች ከፍተኛ የሕጻናት መብቶች ጥሰት እንደሚያስከትል በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት “ዩኒሴፍ” ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄንሬታ ፎር ተናግረዋል። በአመጽ እና በጦርነት ምክንያት ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው በሚቀሩበት ጊዜ የሚኖሩበትን አካባቢ ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ የሚያሳችላቸውን እውቀት ከማጣት ሌላ ለጭቆና፣ ለብዝበዛ፣ ያለ እድሜአቸው ለውትድርና አገልግሎት እና ለጾታ ጥቃት ይጋለጣሉ ብለው ለሕጻናት የትምህርት ዕድልን ማመቻቸት፣ የመማር መብታቸውን ከማስክበር በተጨማሪ ለሰላም ግንባታም ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳለው አስረድተዋል።     

ከ 80 አገሮች በላይ አስተማማኝ የትምህርት ቤት ደህንነት የማስጠበቅ ስምምነት ፈርመዋል።

በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሄንሬታ ፎር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የሚገኙ 84 አገሮች፣ የትምህርት ቤቶችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ ስምምነት በ2007 ዓ. ም. መፈረማቸውን ገልጸው የቡርኪና ፋሶ፣ የማሊ እና የኒጀር መንግሥታትም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። ስምምነቱም የትምህርት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ጸጥታ የሚያስከብር ሰራዊት ማሰማራትን እንደሚያካትት ገልጸው ጦርነት በሚካሄድበት አካባቢ ለልጆች የሚሰጥ የትምህርት አገልግሎት እንዳይቋረጥ መንግሥታት ሃላፊነት እንዲወስዱ ጠይቀው በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅትን ማገዝ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የደህንነት ዋስትና በሌለበት የመማር መብትን ማስከበር አይቻልም፣

በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት “ዩኒሴፍ” ከሰሃል አገሮች መካከል ቡርኪና ፋሶን ማሊን እና ኒጀርን፣ የሥርዓተ ትምህርት እቅዶችን በማዘጋጀት በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ጠግነው እንዲከፈቱ፣ ከሥራ ገበታቸው እና ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ መምህራን ወደ ሥራ ገበታችው እንዲመለሱ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።  

ለትምህርት ቤቶች የሬዲዮ ትምህርት አገልግሎትን ማቅረብ፣

በቡርኪና ፋሶ፣ በካሜሩን እና በኒጀር ትምህርትን በሬዲዮ በኩል የማሰራጨቱ አገልግሎት መጀመሩን የገለጸው የሕጻናት መርጃ ድርጅቱ አገልግሎቱ ተጠናክሮ ጦርነት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በተለያዩ ቋንቋዎች ትምህርትን ለሕጻናት ማዳረስ እንደሚያስገልግ አሳስቧል። ይህ እቅድ በማዕከላዊ የአፍሪቃ ሪፓብሊክ፣ በጊኒ ቢሳው፣ በሴራሊዮን እና በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ በመሳሰሉት አገሮች ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።   

07 March 2019, 17:53