ፈልግ

የቤተክርስቲያን ሕንጻ ውድመት በሶርያ የቤተክርስቲያን ሕንጻ ውድመት በሶርያ 

በሶርያ የክርስቲያኖች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተነገረ።

ሶርያን ጨምሮ በመካከለኛው የምስራቅ አገሮች ውስጥ የክርስቲያኖች ቁጥር እየቀሰ ስለመምጣቱ ዋናው ተጠቃሽ ምክንያት በአካባቢው አገሮች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶችና ጦርነቶች ናቸው

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሶርያ የቅስድት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ዘናሪ፣ ለዓመታት ያህል በጦርነት ውስጥ በወደቀች ሶርያ የክርስቲያኖች ቁጥር ቀንሶ ወደ ሁለት ከመቶ መድረሱን አስታወቁ። ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ዘናሪ ይህን ይፋ ያደርጉት በሃንጋሪ ባደረጉበት ጉብኝት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ለክርስቲያኖች ቁጥር መቀነስ ዋናው ምክንያት፣ 8 ዓመታትን ያስቆጠረ እና የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋበት አሰቃቂ ጦርነት መሆኑንም አስረድተዋል። 

በመካከለኛው የምስራቅ አገሮች ውስጥ የክርስቲያኖች ቁጥር እየቀሰ ስለመምጣቱ ዋናው ምክንያት በአካባቢው አገሮች መካከል  የሚቀሰቀሱ ግጭቶችና ጦርነቶች መሆኑን የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ዘናሪ፣ ጦርነት በሚያስከትለው ጥፋት የአምልኮ ስፍራዎች መውደማቸው እና ክርስቲያኖች መኖሪያቸውንና የትዋልድ አካባቢያቸውን ለቀው በመሰደዳቸው ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።

ሃንጋሪ ለሶርያ የምታደርገው ድጋፍ፣

በሶርያ የቅስድት መንበር ሐዋርያዊ እንደራሴ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ዘናሪ በሃንጋሪ መዲና ቡዳፈስት በሚገኘው ፒተር ፓዝማኒ በሚል ስም በሚታወቅ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የሶርያ ክርስቲያኖች ቁጥር ከአገሩ ሕዝብ መካከል 25 ከመቶ እንደነበር፣ የቅርብ ዓመታት ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ማለትም ከ8 ዓመታት በፊት ማለት ነው ወደ 6 ከመቶ ዝቅ ማለቱን አስረድተዋል። ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ዘናሪ በሶርያ የክርስቲያኖች እየቀነሰ መምጣት ሌላው ምክንያት፣ በክርስቲያን ቤተሰብ መካከል አዲስ የሚወለዱ ሕጻናት ቁጥር በመቀነሱ እንደሆነ አስረድተዋል። የብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ዘናሪ የሃንጋሪ ጉብኝት ዓላማ፣ ባሁኑ ጊዜ በሶርያ ለ4,500 የጦር ጉዳተኞች ሕክምናን በመስጠት ላይ የሚገኙ ሆስፒታሎችንና የሕክምና መስጫ ማዕከላት ለማገዝ የሚያስችል የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታን ለማሰባሰብ መሆኑ ታውቋል። በያዝነው የጥር ወር አጋማሽ ላይ የሃንጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ቪክቶር ኦርባን፣ በጦርነት የተጎድችው ሶርያን መልሶ ለመገንባት የሚያግዝ አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ዩሮ ማበርከታቸው ይታወሳል። በጦርነትም ይሁን በሌሎች የተለያዩ ችግሮች ምክንያት አደጋ ላይ የወደቁትን አገሮች የሚያግዝ መንግሥታዊ ያልሆነ ማሕበር ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ጃምፓዉሎ ሲልቨስትሪ፣ በሶርያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ያሉትን የዕርዳታ አቅርቦት ፕሮግራሞችንና የጤና ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች ዝርዝር ለጉባኤው ተካፋዮች አብራርተዋል። አቶ ጃምፓውሎ ሲልቨስትሪ ሪፖርታቸውን ለጉባኤው ባቀረቡበት ወቅት ባሰሙት የምስጋና ንግግራቸው፣ በሶርያ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የእርዳታ መስጫ ተቋማትን በመደገፍ የሃንጋሪ መንግስት በቀዳሚነት ስላደረገው ትብብር አመስግነው፣ ይህን ማሳሌ በመከትል ሌሎችም መንግሥታት ተመሳሳይ እገዛን እንደሚያደርጉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

በሶርያ አሁንም አስተማማኝ ሰላም አልመጣም፣

በሌላ ወገን በሶርያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ብሔራዊ ጽሕፈት ቤት ይፋ በደረገው ዘገባ መሠረት፣ በኢድሊብ ከተማ በደረሰው የቦምብ ፍናዳታ ጥቃት፣ ትክክለኛ ቁጥር ባይታወቅም በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን ድርጅቱ ገልጿል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
01 February 2019, 15:41