ፈልግ

2018-01-24 lebbra viso 2018-01-24 lebbra viso  

ዓለም አቀፍ የስጋ ደዌ ሕሙማን ቀን ታስቦ ዋለ።

ለስጋ ደዌ ሕሙማን የሕክምና አገልግሎትን መስጠት ብቻ ሳይሆን ከሁሉ አስቀድሞ ሰብዓዊ ክብራቸውን መጠበቅ ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ጉይዶ ባርቤራ ገልጸው ይህ ተግባራዊ ከሆነ ሕሙማኑ ተፈውሰው ከማሕበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ ሰብዓዊ ክብራቸውን ባስጠበቀ መልኩ ከማሕበረሰብ ጋር የሚቀላቀሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይረዳል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዘንድሮ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ. ም. ታስቦ በዋለው ዓለም አቀፍ የስጋ ደዌ ሕሙማን ቀን፣ ሕመሙ አሁንም በብዙ አገሮች ውስጥ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን እነዝህን ሕሙማን ለመደገፍ የሚያስችል የገንዘብ እና የሕክምና አገልግሎት ተተናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መቅረቡ ታውቋል። ሕመሙን በሕክምና ማስወገድ እየተቻለ ነገር ግን ባሁኑ ጊዜ ደሃ በተባሉ 143 አገሮች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገኝና ወንዶችን፣ ሴቶችንና ሕጻናትን እንደሚያጠቃ ታውቋል። ከተጠቀሱት አገሮች መካከል በ12ቱ ብቻ ሕመሙ 94 ከመቶ ማደጉን የሕክምና አገልግሎቱን በማሊ፣ ቤኒን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኒ ቢሳው፣ ኒጀር፣ ሰነጋል፣ ኮንምጎ፣ ማውሪታኒያ፣ ጋቦን፣ ማዳጋስካር፣ ቻድ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሩን፣ ቶጎ፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ካምቦዲያ እና በቬትናም በማበርከት ላይ የሚገኝ የፎሌሮ ፋውንዴሽን ገልጿል።

ሕመሙ እያደገ መምጣቱ ተመልክቷል፣

የራኡል ፎሌሮ ዓለም አቀፍ የስጋ ደዌ ሕሙማን ማሕበር አባል ድርጅት መካከል አንዱ የሆነው ቮልዮ ቪቨረ የተባለ ድርጅት ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ጉይዶ ባርቤራ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት የስጋ ደዌ ሕመም በዓለማች አሁንም መኖሩ ብቻ ሳይሆን በመጨረሻዎቹ ዓመታት በአንዳንድ አገሮች ዘንድ እየተስፋፋ መምጣቱንም ተገንዝበናል ብለዋል። ምክንያቱንም ሲገልጹ የስጋ ደዌ ሕመም በድህነት ምክንያት ከማሕበረሰቡ በሚገለሉት ሰዎች ዘንድ በስፋት የሚታይ ሕመም መሆኑን ገልጸዋል።

የክስተቱ ምክንያት እና መከላከያው፣

ለሕመሙ መከሰት ዋናው ምክንያት በድህነት ምክንያት በቂ የጤና አጠባበቅ አገልግሎትን ካለማግኘት፣ ለጤና ተስማሚ የሆነ በቂ ምግብ ካለመመገብ የተነሳ እንጂ በትንፋሽ የማይተላለፍ፣ በስጋ ዝምድና የማይተላለፍ መሆኑን አቶ ጉይዶ ባርቤራ ገልጸዋል።

በሕመሙ ለተጠቁ ሰብዓዊ ክብርን መስጠት ማግለልን መዋጋት ያስፈልጋል፣

ለስጋ ደዌ ሕሙማን የሕክምና አገልግሎትን መስጠት ብቻ ሳይሆን ከሁሉ አስቀድሞ ሰብዓዊ ክብራቸውን መጠበቅ ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ጉይዶ ባርቤራ ገልጸው ይህ ተግባራዊ ከሆነ ሕሙማኑ ተፈውሰው ከማሕበረሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ  ሰብዓዊ ክብራቸውን ባስጠበቀ መልኩ ከማሕበረሰብ ጋር የሚቀላቀሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ይረዳል ብለዋል።

መደረግ ስላለበት ተግባር ጥሪ ቀርቧል፣

በቅርቡ ሰሜን ካሜሩንን ጎብኝተው የተመለሱት አቶ ጉይዶ ባርቤራ ለቫቲካን የዜና አገልግሎት እንዳብራሩት፣ በጎበኙበት አካባቢ በሕጻናት ላይ ሕመሙ ጎልቶ እንደሚታይ፣ በቂ ምግብ እና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሚጎድል ገልጸዋል። እውነቱ አንዱ ሌላውን ማፍቀር ነው የሚለውን የማሕበሩ መስራች የራኡል ፎሌሮ መፈክር ያስታወሱት አቶ ጉይዶ ባርቤራ መማር እና ዘወትር ማሰብ ያለብን የሚበቃንን ነገር ብቻ መፈለግ እንደሚያስፈልግ፣ በመተጋገዝን መማር እንደሚያስፈልግ፣ አንዱ ለሌላውን በማከበር ሰብዓዊ ክብሩም እንዳይጣስ ጥንቃቄን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።              

31 January 2019, 16:26