ፈልግ

በሶሪያ የሚገኙ ገዳማዊያት ብርታትን የሚያመልክት ጥናታዊ ፊልም ይፋ ሆነ በሶሪያ የሚገኙ ገዳማዊያት ብርታትን የሚያመልክት ጥናታዊ ፊልም ይፋ ሆነ 

በሶሪያ የሚገኙ ገዳማዊያት ብርታትን የሚያመልክት ጥናታዊ ፊልም ይፋ ሆነ

ለባለፉት ስምንት ዓመታት ያህል በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦረነት በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ጦርነት በርካታ ወድመት ያስከተለ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ የሆኑ ሰዎችን ነፍስ የቀጠፈ፣ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰደዱ ያደረገ፣ ከተማዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማፈራረስ እንዳልነበሩ ያደርገ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከታዮ ጦርነቶች ሁሉ አስከፊ የሚባል የእርስ በእርስ አንዱ እንደ ሆነ ይታወቃል። ይህ የሶርያ አስቃቂ የሆነ የጦርነት ታሪክ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በእየለቱ እየተገለጸ የሚገኝ የእርስ በእርስ ጦርነት ሲሆን የሶርያን የእርስ በእርስ ጦረነት በተመለከተ “የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከተደረገው የመጀመሪያው አመጽ” አንስቶ ያለውን ታሪክ የሚገልጽ እና ማርያ ሉዚያ ፎሬንሳ በተባለች የፊልም ዳይሬክተር የተሰራ ጥናታዊ ፊልም በታኅሳስ 04/2011 ዓ.ም በቫቲካን ለእይታ መብቃቱን ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።  “ይህ ጥናታዊ ፊልም “Mother Fortress” የሚል አርእስት የተሰጠው ጥናታዊ ፊልም ሲሆን ጥናታዊ ፊልሙ በሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት እየከፋ በመጣበት ወቅት የቅዱስ ያዕቆብ ገዳም ተብሎ በሚታወቅበት ሥፍራ የነበሩ ገድማዊያን/ ገዳማዊያት እና መነኮሳት ታሪክ ላይ በማጠንጠን በጦርነቱ ወቅት ያሳዩትን ከፍተኛ የሆነ ብርታት ልዩ በሆነ እይታ የሚያቀረብ ጥናታዊ ፊልም እንደ ሆነ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህ “Mother Fortress” በሚል አርእስት ለእይታ የበቃው ጥናታዊ ፊልም “በሶሪያ የተደርገውን የእርስ በእርስ ጦርነት የሚዘገብ ጥናታዊ የሆነ ፊልም ሳይሆን፣ ነገር ግን በተቃራኒው በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት የነበረውን ሰብዓዊ ሁኔታ የምያመልክት” ጥናታዊ ፊልም እንደ ሆነ ፊልሙ በቫቲካን ለእይታ በቀረበበት ወቅት የተገለጸ ሲሆን ይህ ጥናታዊ ፊልም የእርስ በእርስ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት የነበረውን “የመጀመሪያዎቹን የአመፅ ቀናት፣ የጦርነቱን አጀማመር እና ከእዚያም ቀጥሎ የተከናወኑትን የነፍስ አድን” ድርጊቶችን የምያመልክት ጥናትዊ ፊልም እንደ ሆነም በምረቃው ወቅት ተያይዞ ተገልጹዋል።

ይህን ጥናታዊ ፊልም የቅድስት መንበር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት፣ በቅድስት መንበር ሥራ የሚተዳደረው ጳጳሳዊ የባሕል ጉዳዮችን የሚመለከተው ምክር ቤት እና የጣልያን ብጹዕን ጳጳሳት ጉባሄ የኮምንኬሽን ጽ/ቤት በጋር ባደርጉት ድጋፍ ለእይታ የበቃ ጥናታዊ ፊልም ሲሆን ዘጠኝ ክፍሎች ያሉት እና በአሁኑ ወቅት ለእይታ የበቁት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ክፍሎች መሆናቸውን በምረቃው ወቅት ተገልጹዋል።

ሶርያ እንደገና ትወለዳለች

ከሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ በአልቃይዳ የተከበበ እና እራሱን የእስላማዊ መንግስት ለመስፋፋት እንደ ሚሰራ የሚገልጸው እስላማዊ ጽንፈኛ ቡድን ተከቦ በበረሃ ውስጥ እንዳለ የውሃ ስፍራ በመሆን የሚቆጠረው የቅዱስ ያዕቆብ ገዳም በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ ሕጻናትን ፣ መበለቶችን፣ ስደተኞችን፣ በመቀበል አንቡላንሶችን በማዘጋጀት ተጎችጂዎች ሰብዓዊ የሆነ እርዳታ ወደ ሚያገኙበት ሥፍራ እንዲሄዱ በማድረግ ከፍተኛ ሚና የነበረው ገዳም እንደ ሆነ ይህ “Mother Forteress ” የተሰኘው ዘጋቢ ፊል ይገልጻል።  በዚህ የነፍስ አድን ተግባር ላይ ከተሳተፉት የቅዱስ ያዕቆብ ገዳም አባላት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት እማሆይ ባዴሳ አኜስ የተባሉ መነኩሴ ሲሆኑ እርሳቸው ከሌሎች ከሊባኖስ፣ ከፈረንሳይ፣ ከቤልጂዬም፣ ከፖርቱጋል፣ ከቺሊ፣ከቬንዙዌላ፣ የአሜሪካ ግዛት ከሆነቺው ከኮሎራዶ የተውጣጡ ገድማዊያን እና ገድማዊያት በጋራ በመሆን ታላቅ ገድል ማከናወናቸውን የሚገልጽ ጥናትዊ ፊልም ነው።

14 December 2018, 15:50