ፈልግ

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ የባምባሪ መጠለያ ካምፕ ነዋሪዎች፣ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ የባምባሪ መጠለያ ካምፕ ነዋሪዎች፣ 

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርስ ጥቃት እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ።

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ፣ የቦሳንጎዋ ሃገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኔስቶር ደዚሬ በሃገሪቱ እየደረሰ ያለውን መከራ አስመልክተው በቅርቡ ፊደስ ለተባለ የዜና ማሰራጫ ማዕከል እንደገለጹት፣ በያዝነው የአውሮጳዊያኑ 2018 ዓ. ም. መሣሪያ ታጣቂ ሃይሎች በከፈቱት ጥቃቶች፣ 5 ካህናት መገደላቸውን፣ ቤተክርስቲያኖች መቃጠላቸውን፣ ቅዱሳት ምስሎች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ህዳር 25 ቀን 2011 ዓ. ም.፣ ኢፒ በተባለ ካምፕ ውስጥ በተጠለሉ ሰዎች ላይ ጥቃት መድረሱ ተገልጿል። ጥቃቱን ያደረሰው ራሱን በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ ሰላምን ለማምጣት የሚታገል ሕብረት ብሎ የሚጠራ ቡድን መሆኑ ታውቋል። ይህ ቡድን ከዚህ በፊት ማለትም በህዳር 6 ቀን 2011 ዓ. ም. አሊንዳዎ በተባለ ግዛት ውስጥ ለተገደሉት 60 ንጹሓን ዜጎችና ከእነዚህም መካከል የሁለት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ካህናት መገደል ሐላፊነትን መውሰዱ የሚታወስ ነው። ፊደስ የተባለ የዜና ማሰራጫ ማዕከል እንደዘገበው መሣሪያ ታጣቂዎቹ በስፍራው ጥቃቱን ያደረሱት በአገሩ የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ እንደሆነ ገልጾ፣ ጥቃቱን ለማምለጥ ብለው ከስፍራው የሸሹት ተፈናቃዮች በአካባቢው በሚገኘው በቅዱስ ዛቬር፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከለላን ማግኘታቸውን አክሎ ገልጿል። ጥቃቱ ሲፈጸም በስፍራው የነበሩት የዓይን እማኞች እንደገለጹት ራሱን በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ ሰላምን ለማምጣት የሚታገል ሕብረት ብሎ የሚጠራ ቡድን በኢፒ መጠለያ ካምፕ በአራቱም አቅጣጫዎች ተኩስ መክፈቱንና ተፈናቃዮችም በተገኘ ቀዳዳ ጥቃቱን ለማምለጥ ብለው መሸሻቸውን ገልጸዋል።          

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ ያለ እርዳታ ሰጭ መቅረት፣

በኢፒ መጠለያ ካምፕ ጥቅት ሲደርስ በስፍራው የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ወታደር መከላከል ይችል እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን፣ የኢፒ ከተማ የሰላም ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የሆኑት ክቡር አባ ሮጀር ስታኒስላስ ጃማዋ እንደገለጹት የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ ሕዝብ ያለ ጠባቂና ተከላካይ እንደቀረ፣ የወደ ፊት ዕድሉንም ብቻውን እንዲወስን መደረጉን ገልጸዋል። በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ፣ ኢፒ በተባለ ካምፕ ውስጥ በደረሰው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ባይታወቅም እስካሁን ድረስ ሦስት ሰዎች በጠና መቁሰላቸውንና ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ሕጻናት መሆናቸውን ፊደስ የተባለ የዜና አውታር ገልጿል።      

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ በአገሪቱ የሚከሰቱ አመጾች እንዲያከትሙ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ብጹዓን ጳጳሳቱ ክርስቲያኖችና የሌሎች እምነት ተከታዮች ሰላምንና እርቅን ለማውረድ በመተባበር የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ መማጸናቸው ይታወሳል።

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ፣ የቦሳንጎዋ ሃገረ ስብከት ጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኔስቶር ደዚሬ በሃገሪቱ እየደረሰ ያለውን መከራ አስመልክተው በቅርቡ ፊደስ ለተባለ የዜና ማሰራጫ ማዕከል እንደገለጹት፣ በያዝነው የአውሮጳዊያኑ 2018 ዓ. ም. መሣሪያ ታጣቂ ሃይሎች በከፈቱት ጥቃቶች፣ 5 ካህናት መገደላቸውን፣ ቤተክርስቲያኖች መቃጠላቸውን፣ ቅዱሳት ምስሎች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፓብሊክ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በቀዳሚነት ሐዋርያዊ አገልግሎትን የማበርከት ተልዕኮ እንዳለባት፣ ከዚህም ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ ሰላምን፣ በሕዝቦች መካከል ፍቅርን፣ አንድነትንና ወንድማማችነትን ማሳደግ፣ በጦርነትና በአመጽ ለተጎዱት፣ ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉት ዜጎች መጠለያን ማዘጋጀት እንደሆነ የሃገሪቱ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ከዚህ በፊት ይፋ ባደረገው መልዕክቱ መግለጹ ይታወሳል። 

06 December 2018, 16:49