ፈልግ

በየመን በመካሄድ ላይ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት በየመን በመካሄድ ላይ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት  

ካሪታስ የጣሊያን የበጎ አድራጎት ድርጅት በዓለም ዙሪያ የጦር መሳርያ ንግድ መስፋፋቱን ገለጸ

በጣሊያን የሚገኘው እና ካሪታስ በማባል የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበጎ አድራጎት ድርጅት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙርያ የሚካሄዱ ግጭቶች በመጠን እና በዓይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መሄዳቸውን አስታወቀ። ካሪታስ ጣሊያን ይህንን መግለጫ የሰጠው እ.አ.አ 2018 ዓ.ም ጠቅላላ አመታዊ ሪፖርት ባቀረበበ ወቅት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አስገራሚ በሆነ መልኩ በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና ጦርነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እና በዓይነት እየጨመሩ  መሄዳቸውን ገልጾ ይህም በርካታ የሆኑ ዜጎች እንዲፈናቀሉ በተለይም ሕጻናት እና ሴቶችን ለከፍተኛ መከራ እና ስቃይ እየዳረጉ የሚገኙ ግጭቶች መሆናቸውን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጹዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ካሪታስ ጣሊያን በዚህ በመገባደድ ላይ ባለው የአውሮፓዊያኑ 2018 ዓ.ም የግጭቶች መንስሄ የሆኑ ችግሮችን  ለይቶ በማውጣት ጥናት ማድረጉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ግጭቶች እና ጦርነቶች እንዲበራከቱ ካደርጉ ምክንያቶች በቀዳሚነት የሚገለጸው የጦር መሳሪያ ምርት በእጥፍ መጨመሩ መሆኑን አመልክቶ ድሃ የሚባሉ፣ ለመሰረተ ልማት ማስፋፊያ የገንዘብ አቅም የለንም የሚሉ ሀገራት ሳይቀር የጦር መሳርያን በመሸመት መጠመዳቸውን ጨምሮ ገልጹዋል።

በአለም ላይ ግጭቶች እየጨመሩ ሲሄዱ ዓለም አቀፍ የሆነ የደህንነት ዋስትና እያሽቆለቆለ መሄዱን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እምብዛም በመገናኛ ብዙሃን የማይዘገቡ አሰቃቂ የሆኑ ግጭቶች በአለም ዙርያ እየተካሄዱ መሆኑን ጨምሮ የገለጸው የካሪታስ ጣሊያን አመታዊ ሪፖርት እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2017 ዓ.ም ብቻ በድምሩ በዓለም ዙሪያ 378 ከፍተኛ የሆኑ ግጭቶች በተለያዩ የአለማችን አከባቢዎች ተከስተው እንደ ነበረ ያመለከተወ የካሪታስ ሪፖርት ከነዚህ ውስጥ 20ዎቹ ከፍተኛ የሆኑ ጦርነቶች እንደ ነበሩ አመልክቱዋል።

ሪፖርቱ ለየት ባለ ሁኔታ በዓለም ዙሪያ እየተካሄዱ የሚገኙ ግጭቶች እና ጦርነቶች እንዲጨምሩ ካደርጉት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ከፍተኛ የሆነ የጦር መሳርያ ምርት እንደ ሆነ የገለጸ ሲሆን የጦር መሣሪያ ገበያዎች በከፍተኛ ሁኔታ መበራከታቸውን ገልጾ  አልፎ አልፎ ይህ የጦር መሳርያ ንግድ ሕገወጥ በሆኑ አዘዋዋሪዎች ሳይቀር እየተቸበቸበ መሆኑን ጨምሮ ጠቁሟል። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በአለም ደረጃ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉ የጦር መሳርያዎችን ሳይቀር ለምሳሌም የኬሚካል የጦር መሳርያ፣ በበርሜል ታጭቀው የሚጣሉ ቦንቦችን፣ የክላስተር ቦንብ፣ እጅግ በጣም የረቀቁ እና በኮፒውተር በመተግዝ የሚወነጨፉ ሚሳየሎችን፣ የሳይበር ጥቃቶችን ጨምሮ በርካታ በዓይነታቸው እና በቁጥራቸው ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ ዓይነት የጦር መሳርያዎች ሳይቀር በጥቅም ላይ እየዋሉ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ እያስከተሉ እንደ ሚገኙ የካሪታስ ሪፖርት አመላክቱዋል። "እነዚህ የጦር መሳርያዎች የሕዝቡን የሰብአዊ መብት የሚጥሱ ክስተቶችን የሚፈጥሩ የጦር መሳሪያዎች መሆናቸውን የካሪታስ ኢጣሊያን ምክትል ዳይሬክተር ፓኦሎ ቤቼጋቶ አጽንዖት ሰጥተው የገለጹ ሲሆን በሁሉም ጦርነቶች ውስጥ ሰለባ የሚሆኑት እና እነዚህ ጦርነቶች እንዲቀሰቀሱ ምንም ዓይነት አስተዋጾ ያላደረጉ ሕጻንት እና ሴቶች በቀዳሚነት ተጠቂ መሆናቸው በጣም አስከፊ የሆነ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የጦርነቶች ሁሉ ሰላባ የሚሆኑት ስደተኞች ናቸው

እነዚህ ከፍተኛ ግጭቶች እና ጦርነቶች በሚያስከትሏቸው ጥፋቶች የተነሳ ለከፍተኛ ችግር እና ስቃይ የሚጋለጡት ስደተኞች እንደ ሆኑ በሪፖርቱ የተገለጸ ሲሆን በእነዚህ አሰቃቂ ግጭቶች እና ጦርነቶች የተነሳ ቤት ንብረታቸውን ጥሎ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን ገልጾ በዓለም ደረጃ በተለያዩ ምክንያቶች የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 70 ሚሊዮን መድረሱን የካሪታስ ኢጣሊያ አመታዊ ሪፖርት ጨምሮ ገልጹዋል። እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2017 ብቻ በየቀኑ በዓለም ደረጃ 44 ሺ ሰዎች በአስገዳጅ ሁኔታዎች የተነሳ አካባቢያቸውን ጥለው የሚስደዱ መሆናቸውን የማለከተው የካሪታስ ሪፖርት እነዚህም ሰዎች ቤት ንበረታቸውን ጥለው የሚሰደዱት በዋነኛነት በዓለም ዙርያ እየተከሰቱ ባሉት ግጭቶች እና ጦርነቶች ምክንያት እንደ ሆነ አመልክቶ ይህም በዚህ በመገባደድ ላይ ባለው የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2018 ላይ 40% ጭማሪ ማሳየቱን ካሪታስ የተባለ የጣሊያን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት 2018 ዓ.ም አመታዊ ሪፖርይ መግለጫ ያመለክታል።

11 December 2018, 16:41