ፈልግ

World AIDS Day preparations in Nepal World AIDS Day preparations in Nepal 

የኤች አይ ቪ ኤይድስ ስርጭትን በተመለከተ የሚሰጥ ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ፣

እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር በሰማንያዎቹና በዘጠናዎቹ ተጠርጥረው ለምርመራ የሚቀርቡት በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን በቁጥር በርካታ የሆኑ የእድሜ ባለ ጸጎችም የበሽታው ተጠቂዎች ሆነው መገኘታቸውን አስረድተዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በሮም ከተማ በሚገኘው በአጎስቲኖ ጀመሊ ሆስፒታል ውስጥ የተላላፊ በሽታዎች ምርምር ዩኒቨርሲቲ ፋውንዴሽን ፕሮፌሰር የሆኑት ሮበርቶ ካውዳ እንደገለጹት ስለ ኤች አይ ቪ ኤይድስ ስርጭት አልፎ አልፎ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ካልሆነ በቀር ብዙ እንደማይወራ፣ በማሕበረሰብም መካከል የሚሰጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክትም በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ገልጸዋል። እንደ አውሮጳውያኑ አቆጣጠር፣      በሰማንያዎቹ ዓመታት ውስጥ በሽታው ላይ የሚደረግ ምርምርና ጥናት ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሱት ፕሮፌሰ ሮበርቶ በሽታው ባሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር በሰማንያዎቹናቅ በዘጠናዎቹ ተጠርጥረው ለምርመራ የሚቀርቡት በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን በቁጥር በርካታ የሆኑ የእድሜ ባለ ጸጎችም የበሽታው ተጠቂዎች ሆነው መገኘታቸውን አስረድተዋል። ፕሮፌሰር ፍራንኮ በማከልም የዕድሜ ባለጸጎቹ በበሽታው የመያዝ ምልክትን ማሳየት ብቻ ሳይሆን ከዚያም አልፎ ተርፎ የብዙዎች ሕይወት እየተቀጠፈ መሆኑን ገልጸዋል። በአውሮጳም ቢሆን የበሽታው ስርጭት የተወሰን መጠን ቢያሳይም የመቆጣጠሪያ ምድሐኒት ስርጭት ከቀድሞ እንደቀነሰ፣ ገበያ ላይ አሉ የሚባሉ የመድሕኒት ዓይነቶችም በሽታውን የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ መሆኑ እጅግ እንዳሳሰበና፣ በበሽታው የሚለከፉት ሰዎች ቁጥርም መጨመሩን ተናግረዋል።

የድንበር የለሽ ሐኪሞች ማህበር ወቀሳ፣

በሽታው ላይ የሚደረግ የምርመራ ደረጃ ማሳደግና፣ በበሽታው ለተጠቁት ሕጻናት የሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት አስመልክቶ፣ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማህበር፣ በመድሐኒት አምራች ድርጅቶች ላይ ወቀሳ አቅርቦ፣ መድሐኒት አምራች ድርጅቶቹ በበሽታው ላይ ምርምር ካደረጉ በኋላ የሚያመርቱት መድሃኒቶችና የምርምር ውጤቶች ዘግይተው በመውጣታቸው የተሰማቸውን ቅሬታ ገልጸዋል። ድንበር የለሽ የሕክምና ባለሞያዎች ማህበር ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው በበሽታው ለተጠቁ ህጻናት የሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት ችላ እየተባለ እንደሆነ አስታውሶ የመድሐኒት አምራች ድርጅቶችም ቢሆኑ በሽታው የተያዙ ሕጻናትን ለማከም የሚረዱ የመድሐኒት ምርት መቀነሳቸውን ገልጿል። የመድሐኒት አምራች ድርጅቶች መድሃኒቶችን አምርተው ለማውጣት የሚወስዱት ጊዜ መራዘሙ ለሕጻናት የሚሆኑ ሌሎች አዳዲስ መድሐኒቶችን በፍጥነትና በጥራት ለማምረት እንቅፋት መፍጠሩን ድንበር የለሽ ሐኪሞች ማህበር ገልጿል።

ካለፈው ዓመት ጀምሮ፣

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማህበር ባደረገው ገለጻ መሠረት ካለፈው ዓመት ወዲህ የመድሐኒት አምራች ድርጅቶች ለሕጻናት እንደዚሁም በኤች አይ ቪ ለተያዙት የዕድሜ ባለጸጎች በሚሰጡ መድሐኒቶች ላይ የተደርገ መሻሻል በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ አስታውቋል። ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማህበር በማከልም በማደግ ላይ ያሉ አገሮች፣ ከዓለም የጤና ድርጅት በሚሰጣቸው መመሪያና ደንብ መሠረት በበሽታው ለተጠቁ ዜጎቻቸው መድሐኒቶችን ለማዳረስ መቸገራቸውንም ገልጸዋል። ሕጻናት መውሰድ ያሉባቸው መድሐኒቶችም ጊዜውን ጠብቀው በሚፈለጉበት ቦታ እንደማይገኙ የሐኪሞች ማሕበር ተናግሯል።

03 December 2018, 16:23