ፈልግ

bambina in preghiera, bambina che prega, strage, massacro di Orissa, India bambina in preghiera, bambina che prega, strage, massacro di Orissa, India 

ዛሬም ቢሆን በብዙ አገሮች ዘንድ የሕጻናት መብት እየተከበረ አለመሆኑ ተገለጸ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መጋቢት 9 ቀን 2007 ዓ. ም. በተከበረው ዓለም አቀፍ የሕጻናትና ልጆች ቀን ባስተላለፉት መልዕክታቸው አንድ ማሕበረሰብ ያለ ሕጻናት ሲቀር ያሳስባል ብለው፣ ይህም አሁን በዘመናችን እያየነው ያለ ሐቅ እንደሆነም መግለጻቸው ይታወሳል። ሕጻናት የሌሉበት ማሕበረሰብ፣ መሠረታዊ መብታቸውን የተገፈፉ በርካታ ሕጻናት መኖራቸው የዘመናችን ሐቅ እንደሆነና ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን አንዳንድ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሪፖርታቸው መግለጻቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በየዓመቱ ህዳር 11 ቀን ዓለም ዓቀፍ የሕጻናትና ልጆች ቀን ተብሎ እንዲከበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ1946 ዓ. ም. ጀምሮ መደንገጉ ይታወሳል።  በተጨማሪም ህዳር 11 ቀን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በ1981 ዓ. ም. የሕጻናትንና የልጆችን መብት ያጸደቀበት ዕለት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ዘንድሮ ህዳር 11 ቀን በተከበረው ዓለም አቀፍ የሕጻናትና ልጆች በዓል ወቅት ይፋ በወጣው መረጃ መሠረት ዛሬም ቢሆን በብዙ አገሮች ዘንድ የሕጻናትና ልጆች መብት እየተከበረ አለመሆኑ ተገልጿል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መጋቢት 9 ቀን 2007 ዓ. ም. በተከበረው ዓለም አቀፍ የሕጻናትና ልጆች ቀን ባስተላለፉት መልዕክታቸው አንድ ማሕበረሰብ ያለ ሕጻናት የሚያሳስብ ነው ብለው ይህም ብቻ ሳይሆን አሁን በዘመናችን እያየነው ያለ ሐቅ እንደሆንም መግለጻቸው ይታወሳል። ሕጻናት የሌሉበት ማሕበረሰብ ወይም መሠረታዊ መብታቸውን የተገፈፉ በርካታ ሕጻናት መኖራቸው የዘመናችን ሐቅ እንደሆነና ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን አንዳንድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች በርፖርታቸው መግለጻቸው ታውቋል።

ፍትህን የተነፈጉና አመጽ የሚነሳባቸው ሕጻናት፣

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩኒሴፍ ኢጣሊያ ዳይረክተር የሆኑት አቶ ፓውሎ ሮዘራ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት በብዙ አገሮች ሕጻናት መብታቸውን ተነፍገው እንደሚኖሩ፣ አመጽና በደል እንደሚደርሳቸው አስረድተዋል።

የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር፣

በዓለማችን ዕድሜአቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት መካከል በአምስት ሰኮንድ ውስጥ 1 ሕጻን እንደሚሞትና በ2009 ዓ. ም. ብቻ የሞቱት ሕጻናትና ልጆች ቁጥር 6.2 እንደነበር ታውቋል። ከእነዚህ መካከል 5. 4 ሚሊዮን ሕጻናት በመጀመሪያዎቹ አምስት ዓመት ዕድሜ እንደሚሞቱና ከእነዚህም ግማሽ የሚሆኑ አዲስ የሚወለዱ እንደሆነ ታውቋል። በ1982 ዓ. ም. በዓመት የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር ከ12. 6 ሚሊዮን እጅጉን ማሽቆልቆሉ ታውቋል።

በተመጣጣኝ ምግብና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ እጥረት፣

ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑትን ሕጻናት የሚያጋጥም የተመጣጣኝ ምግብ እጥረት በየዓመቱ ለሦስት ሚሊዮን ሕጻናት ሞት ምክንያት ሆኗል ተብሏል። በዓለማችን በተመጣጣኝ ምግብ እጥረት የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር ከ200 ሚሊዮን በላይ ነው ተብሏል። በየመን ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ሲገልጽ በየመን በተመጣጣኝ ምግብ እጥረት የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር በዓመት 30 ሺህ እንደሆነ ታውቋል። በዓለማችን ከ900 ሚሊዮን ሕጻናት በላይ በቂ የንጽህና አገልግሎትን እንደማያገኙና 66 ከመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ መሠረታዊ የንጽህናን አገልግሎት እንደሚያቀርቡ ታውቋል።

ድህነት፣

በዓለማችን ዕድሜአቸው በአስራዎቹ መካከል የሚገኙ ልጆች በድህነት ሕይወት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል። የድህነት ሕይወት የሚኖሩ ልጆች ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች የሚኖሩ ብቻ ሳይሆኑ ለምሳሌ በምዕራቡ ዓለም 30 ሚሊዮን የሚሆኑ ልጆች በድሕነት ሕይወት ውስጥ እንደሚገኙ ጥናቱ ያመላክታል። በአውሮጳ ሕብረት አገሮች ውስጥ ወደ 20 ከመቶ የሚሆኑ ልጆች ለድሕነት ሕይወት ተጋልጠው እንደሚገኙና በዚህም ምክንያት ከማሕበረሰቡ የመገለል አደጋ ላይ መኖራቸው ታውቋል።

ሕጻናት ከአቅማቸ በላይ ለሆነ ሥራ፣

በማደግ ላይ ባሉት አገሮች ከሚኖሩት፣ እድሜ አቸው ከ 5 እስከ 17 ዓመት ካላቸው 4 ሕጻናት መካከል አንዱ በጤና ላይ ጉዳት ሊያስከትል በሚችል ከባድ የሥራ ዓይነት ላይ እንደተሰማራ ታውቋል። እነዚህ ሕጻናት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች እንደሚገኙና ዕድሜ አቸውም ከ 5 እስከ 17 ዓመት ከሚሆናቸው መካከል 29 ከመቶ የሚሆኑ እንደሆነ ታውቋል።

የአስቸኳይ እርዳታ ፈላጊ ሕጻናት ቁጥር፣

በዓለማችን ከሚገኙ ሕጻንት መካከል ከ4 ውስጥ አንዱ በጦርነትና በተፈጥሮ አደጋዎች በተጠቁ አገሮች ውስጥ እንደሚኖር የታወቀ ሲሆን ቢያንስ 117 ሚሊዮን ሰዎችም ከላይ በተጠቀሰው ችግር ምክንያት ያለ ንጹ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሚኖሩ ታውቋል።

አመጽ፣

በዓለም ደረጃ ዕድሜ አቸው ከ13 እስከ 15 ዓመት ካላቸው ተማሪዎች መካከል 3ቱ በጓደኞቻቸው ጥቃት እንደደረስባቸ ታውቋል። ወደ 720 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕጻናትም በትምሕርት ቤት የግርፋት ቅጣት በሚፈጸምባቸው አገሮች የሚኖሩ እንደሆነ ታውቋል።

የትምሕርት ዕድል፣

በዓለማችን እድሜአቸው ከ5 እስከ 17 ዓመት የሆናቸው ልጆችና ወጣቶች ወደ ትምህርት ቤት እንደማይሄዱና በተለይም እነዚህ ሕጻናትና ልጆች የሚኖሩበት አገር በጦርነትና በተፈጥሮ አድጋ የተጠቁ መሆናቸው ታውቋል።

ስደት፣

30 ሚሊዮን የዓለማችን ሕጻናት በጦርነትና ግጭቶች በሚታዩባቸው አገሮች ውስጥ እንደሚኖሩ የታወቀ ሲሆን ይህ ቁጥር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ከተመዘገበው እጅግ ከፍ ያለ እንደሆነ ታውቋል። ወደ 80 በሚጠጉ አገሮች ውስጥ ቁጥራቸው ከ300 ሺህ በላይ ሕጻናት ያለ ተነከባካቢ ወላጅ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን ከኣነዚህ ሕጻናት መካከል 28 ከመቶ የሚሆኑ ሕጻናት ወላጆቻቸው በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ወንጀለኞች የተወሰዱ መሆናችው ታውቋል።

የHIV/AIDS ጠተቂዎች፣

ያለፈው ዓመት ብቻ በዓለማችን ውስጥ ዕድሜአቸው ከ19 ዓመት በታች የሆኑ 130, 000 ሕጻናትና ወጣቶች በኤች አይ ቪ በሽታ የሞቱ እንደሆነ፣ 430, 000 የሚሆኑ ደግሞ በበሽታው የመያዝ ምልክት  የታየባቸው እንደሆነ ታውቋል። በ2009 ዓ. ም. በአንድ ሰኣት ውስጥ፣ ዕድሜአቸው ከ15 እስከ 19 ዓመት ከሆናቸው ወጣቶች መካከል 30 ወጣቶች በቫይረሱ እንደሚጠቁ ከእነዚህም ሁለት ሶስተአኛው ሴቶች መሆናቸው ታውቋል። 

22 November 2018, 16:54