ፈልግ

2018.11.06 Figlia di Asia Bibi 2018.11.06 Figlia di Asia Bibi 

የአሲያ ቢቢ ልጅ ኤሻም፣ እናቷን በሕይወት ስታገኛት የሚሰማት ደስታ ታላቅ ይሆናል አለች።

ኤሻም ከአባቷ ጋር በመሆን ወደ ሮም ከመጓዟ ጥቂት ቀናት በፊት እስር ቤት የነበረች እናቷን እንደጎበኘቻትና ወደ ሮም በምታደርገው ጉብኝት ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን እንደምታገኛቸው እና ሮም በሚገኘው ኮሎሴውም ውስጥ ቀይ መብራት በርቶ መላው የዓለም ሕዝብም በጸሎት እንደሚያስታውሳት ለእናቷ መናገሯ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የአሲያ ቢቢ ልጅ ኤሺያም እናቷ ከእስር እንድትፈታ በጸሎት የተባበሩትን በሙሉ አመስግና እናቷን በአካል ስታገኛት የሚሰማት ደስታ ከፍተኛ እንደሚሆን ገልጻለች። ኤሻም፣ ስደትና ስቃይ ለሚደርስባት  ቤተክርስቲያን የዕርዳታ እጁን ለሚዘረጋ አንድ የጳጳሳዊ ፋውንዴሽን በላከችው የቪዲዮ ምስል መልዕክቷ እንደገለጸችው፣ እናቴን እስካሁን በዓይኔ ባላገኛትም ከእስር ቤት የመፈታቷ ዜና ሲደርሰኝ የተሰማኝን ደስታ በቃላት ልገልጸው አልችልም ብላለች።

ለጸሎታችሁ አመሰግናለሁ፣

እናቷ አሲያ ቢቢ የሃሰት ክስ ተመስርቶባት በቁጥጥር ስር ስትውል ኤሻም እድሜዋ 9 ዓመት የነበራት ሲሆን፣ እናቷ ከእስር ነጻ መለቀቋ ሁሉንም ያስደሰተ ዜና እንደሆነ ገልጻ፣ በእነዚህ በርካታ ዓመታት በጸሎት የረዷትን በሙሉ አመስግናቸዋለች። ያለፈው ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ. ም. እናቷ አሲያ ቢቢ ከእስር መፈታቷን በማስመልከት ባሰማች ንግግር እንደገለጸችው የእናቷን ነጻ መለቀቅ የሰማችበት ዕለት በሕይወቷ ውስጥ ልዩ የደስታ ዕለት እንደነበረ ገልጻለች። በመሆኑም እግዚአብሔር ጸሎታችንን ስለሰማልን አመሰግነዋለሁ ብላለች።

ኤሻም ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ስትገናኝ፣

ኤሻም ከአባቷ ከአሺክ ማሲ ጋር በመሆን ባለፈው ዓመት የካቲት ወር 2010 ዓ. ም. ወደ ሮም መጥተው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ማግኘታቸውና በወቅቱም በሮም ታላቅ የጸሎት ስነ ስርዓት መዘጋጀቱ ይታወሳል። ኤሻም ከአባቷ ጋር በመሆን ወደ ሮም ከመጓዟ ጥቂት ቀናት በፊት እስር ቤት የነበረች እናቷን እንደጎበኘቻትና ወደ ሮም በምታደርገው ጉብኝት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን እንደምታገኛቸውን ሮም የሚገኘው ኮሎሴውም ቀይ መብራት በርቶበት መላው የዓለም ሕዝብም በጸሎት እንደሚያስታውሳት መናገሯ ይታወሳል። አሲያ ቢቢም፣ በልጇ በኩል ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ልባዊ ሰላምታዋን መላኳ ይታወሳል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኤሻምንና የኤሻምን አባት በቫቲካን ተቀብለው ባነጋገሯቸው ወቅት፣ አሲያ ቢቢን በጸሎታቸው እንደምያስታውሷት ገልጸው፣ አሲያ ቢቢ ጠንካራ ሰማዕት እንደሆነች መናገራቸው ይታወሳል።

ለአሲያ የተደረገ ምሕረት፣

የ47 ዓመት ዕድሜ ያላት አሲያ ቢቢ የካቶሊክ እምነት ተከታይና የ5 ልጆች እናት መሆኗ ታውቋል። የእስልምናን ሐይማኖት አንቋሽሻለች፣ የነብዩ መሐመድን ስም አጥፍታለች የሚል የወንጀል ክስ ተመስርቶባት፣ የሞት ቅጣት ፍርድ የተፈረዳባትን አሲያ ቢቢን፣ የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ. ም. ነጻ ማሰናበቱን ተከትሎ የአገሩ እስላማዊ የፓለቲካ ድርጅት በርካታ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ለአሲያ ቢቢ የሕይወት ዋስትናን ለመስጠት ሲባል ከጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ወደ አንድ ያልታወቀ ስፍራ መዛወሯ ታውቋል። አሲያ ቢቢ በአገሩ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ነጻ ብትለቀቅም በፓክስታን እስላማዊ የፓለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች  የተቃውሞ ሰልፎችን እያካሄደ መሆኑ ታውቋል። አሲያ ቢቢ በበኩሏ ለሚጠሏት፣ በእስር ላሰቃዩዋትም በሙሉ ምሕረትን እንዳደረገችላቸውና በጸሎቷም እንደምታስታውሷቸው ገልጻለች።

ቤተሰቦቿ በፓክስታን ሊቆዩ እንደማይችሉ፣

የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ካገሩ ሁለት እስላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያደረገ ባለው ድርድር በአሲያ ቢቢ ጉዳይ ላይ ለመስማማትና የመጨረሻ ውሳኔን ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል። የአገሪቱ እስላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተከታታይ ለሦስት ቀናት በመላው ፓክስታን ሰላማዊ ሰልፎችን አድርጎ እንደነበር ይታወሳል። የአሲያ ቢቢ ባለቤት አሺክ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት ከባለቤታቸው ከአሲያ ቢቢ ተለይተው መኖር አስቸጋሪ እንደነበር አስታውሰው፣ አሲያ ቢቢ ከተጣለባት ቅጣት ነጻ ብትሆንም በፓክስታን ውስጥ የመቆየት ዕድላቸው አጠራጣሪ እንደሆነ አስረድተዋል።

የሁለት አክራሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች በፍርድ ቤት ቀርበው፣

የፓክስታን ጠቅላይ አቃቤ ፍርድ ቤት በሁለት አክራሪ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች ላይ የቀረበውን የክስ ሰነድ ተቀብሎ መመልከቱ ሲታወቅ፣ በእነዚህ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ላይ የቀረበው ክስም ባለፉት ቀናት የአሲያ ቢቢን ከእስር መፈታትን ተከትሎ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ሕገ ወጥ ነበር የሚል ሲሆን ተከሳሾቹ የእስላማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ትናንት ህዳር 3 ቀን 2011 ዓ. ም. ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
13 November 2018, 15:30