ፈልግ

2018.11.03 ASIA BIBI 2018.11.03 ASIA BIBI 

በፓክስታን ለአሲያ ቢቢ ልጅ የሕይወት ዋስትና አልተገኘላትም ተባለ።

የአሲያ ቢቢ ልጅ ኤሻም እንደገለጸቸው እናቷና አባቷ መንግሥት ባዘጋጀላቸው ድብቅ ስፍራ እንደሚገኙ ተናግራ፣ የእርሷ የሕይወት ዋስትና ግን አደጋ ላይ መውደቁን ገልጻለች። ኤሽም በማከልም እናቷ ከእስር ነጻ ከወጣችበት ካለፈው ወር ጀምሮ የሕይወት ዋስትናን ለማግኘት የመኖሪያ ቤቷን አራት ጊዜ እንደቀየረች ገልጻለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የእስምናን ሐይማኖት ከማጉደፏም በላይ የነቢዩን መሐመድ ስም አጥፍታለች በሚል ወንጀል የሐሰት ክስ ተመስርቶባት የሞት ቅጣት ፍርድ የተፈረደባትና፣ ከ9 ዓመት እስራት በኋላ በቅርቡ የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ ነጻ የለቀቃት የአሲያ ቢቢ ልጅ ኤሻም፣ በአገሯ የግድያ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚደርስባት ገልጻለች። ከእስር ነጻ የተለቀቀች አሲያ ቢቢ ባሁኑ ጊዜ በፓክስታን ውስጥ ባልታወቀ ስፍራ ተደብቃ እንደምትገኝ የሚታወቅ ሲሆን ልጇ አሺያም ግን በምትኖርበት መንደር ከማሕበረሰቡ ተገልላ የግድያ ማስፈራሪያ እንደሚደርስባት ገልጻለች።          

ሁኔታውን በቅርብ በመከታተል ላይ ያለና በስቃይና መከራ ውስጥ ለምትገኝ ቤተክርስቲያን ድጋፍን በመስጠት ላይ የሚገኝ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን ከአሲያ ቢቢ ጠበቃ ከሆኑት ከአቶ ዮሴፍ ናዲም ጋር በመተባበር ኤሻምን ከአባቷ ጋር ወደ ውጭ አገር መጓዝ እንዲችሉ አስፈላጊውን መስፈርቶችን ሲያሟሉላቸው መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ዛሬ የአሲያ ቢቢ ልጅ ኤሻምና የአሲያ ጠበቃ የሆኑት ዮሴፍ ናዲም ከነቤተሰቦቻቸው ጋር ለሕይወታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ መገኘታቸውን በሮም የሚገኝ በስደት ላይ ለሚገኝ ቤተክርስቲያን ድጋፍን የሚሰጥ ጳጳሳዊ ፋውንዴሽን አስታውቋል። የአሲያ ቢቢ ልጅ ኤሽም እንደገለጸቸው እናቷና አባቷ መንግሥት ባዘጋጀላቸው ድብቅ ስፍራ እንደሚገኙ ተናግራ፣ የእርሷ የሕይወት ዋስትና ግን አደጋ ላይ መውደቁን ገልጻለች። ኤሽም በማከልም እናቷ ከእስር ነጻ ከወጣችበት ካለፈው ወር ጀምሮ የመኖሪያ ቤቷን አራት ጊዜ እንደቀየረች ገልጻለች።

የአሲያ ጠበቃ ይሆኑት አቶ ዮሴፍ ናዲም እንዳስረዱት አሲያ ቢቢ የምትገኝበት ሁኔታ አስጊ እንደሆነ፣ ለልጇም እጅግ መጨነቋን ገልጸዋል። የአሲያ ጠበቃ አቶ ዮሴፍ በማከልም አሲያ ቢቢ ከሴት ልጆቿ ጋር የስልክ መልዕክቶችን ከመለዋወጥ ባሻገር በአካል የማግኘት እድልን አላገኘችም ብለዋል። የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ከጎናቸው መቆሙ እጽናንቶናል ያሉት የአሲያ ቢቢ ጠበቃ የሆኑት አቶ ዮሴፍ በጸሎት ድጋፋቸውን ለገለጹት በሙሉ በአሲያ ቢቢ ልጆችና በራሳቸው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በማከልም ለሕይወታቸው ዋስትና ከሌላቸው ከፓክስታን በቅርቡ እንደሚወጡ ያላቸውን ተስፋ ገልጸው ቢቀናቸው የአውሮጳዊያኑን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓልን በሮም ለማክበር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ኤሻም ከአባቷ ከአሺክ ማሲ ጋር በመሆን ባለፈው ዓመት የካቲት ወር 2010 ዓ. ም. ወደ ሮም መጥተው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ማግኘታቸውና በወቅቱም በሮም ታላቅ የጸሎት ስነ ስርዓት መዘጋጀቱ ይታወሳል። ኤሻም ከአባቷ ጋር በመሆን ወደ ሮም ከመጓዟ ጥቂት ቀናት በፊት እስር ቤት የነበረች እናቷን እንደጎበኘቻትና ወደ ሮም በምታደርገው ጉብኝት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን እንደምታገኛቸውን ሮም የሚገኘው ኮሎሴውም ቀይ መብራት በርቶበት መላው የዓለም ሕዝብም በጸሎት እንደሚያስታውሳት መናገሯ ይታወሳል። አሲያ ቢቢም፣ በልጇ በኩል ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ልባዊ ሰላምታዋን መላኳ ይታወሳል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኤሻምንና የኤሻምን አባት በቫቲካን ተቀብለው ባነጋገሯቸው ወቅት፣ አሲያ ቢቢን በጸሎታቸው እንደምያስታውሷት ገልጸው፣ አሲያ ቢቢ ጠንካራ ሰማዕት እንደሆነች መናገራቸው ይታወሳል።

የ47 ዓመት ዕድሜ ያላት አሲያ ቢቢ የካቶሊክ እምነት ተከታይና የ5 ልጆች እናት መሆኗ ታውቋል። የእስልምናን ሐይማኖት አንቋሽሻለች፣ የነብዩ መሐመድን ስም አጥፍታለች የሚል የወንጀል ክስ ተመስርቶባት፣ የሞት ቅጣት ፍርድ የተፈረዳባትን አሲያ ቢቢን፣ የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ. ም. ነጻ ማሰናበቱን ተከትሎ የአገሩ እስላማዊ የፓለቲካ ድርጅት በርካታ የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ለአሲያ ቢቢ የሕይወት ዋስትናን ለመስጠት ሲባል ከጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ወደ አንድ ያልታወቀ ስፍራ መዛወሯ ታውቋል። አሲያ ቢቢ በአገሩ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ነጻ ብትለቀቅም በፓክስታን እስላማዊ የፓለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች  የተቃውሞ ሰልፎችን እያካሄደ መሆኑ ታውቋል። አሲያ ቢቢ በበኩሏ ለሚጠሏት፣ በእስር ላሰቃዩዋትም በሙሉ ምሕረትን እንዳደረገችላቸውና በጸሎቷም እንደምታስታውሷቸው ገልጻለች።

30 November 2018, 15:42