ፈልግ

bambini africa pace bambini africa pace 

በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ የጦር ሠራዊቱ ሰላምን ለማስፈን እየጣረ መሆኑ ተገለጸ።

የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ መንግሥት የጦር ሠራዊቱን በጦርነቱ በተጎዱት አካባቢዎች በማሰማራት፣ ከአማጺያን እጅ ነጻ በማውጣት፣ አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑ ታውቋል። ቢሆንም ጥረቱ ጊዜን የሚወስድ እንደሆነ ክቡር አባ ማቴዎስ አስረድተው ወደ ስፍራው የሚሰማራው የጦር ሀይል በቅድሚያ በቂ ስልጠናን መውሰድ ያስፈልጋል ብለው ምክንያቱን ሲገልጹ የመካከለኛው የአፍሪቃ ሪፓብሊክ ሰፊ አገር በመሆኑ የእያንዳንዱን አካባቢ አቀማመጥ ማወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በመካከለኛው አፍሪቃ አገር፣ የጦር ሠራዊቱ አባላት፣ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተሰማርቶ ሰላምን ለማስፈን ጥረት እያደረገ መሆናቸው ታውቋል። በመካከለኛዋ የፍሪቃ ሪፓብሊክ በርካታ አካባቢዎች በመንግሥት ተቃዋሚ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸውን፣ የዋና ከተማዋ የባንጊ ካቴድራል መሪ ካህንና የሃገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ ክቡር አባ ማቴዎስ ቦንዶቦ ገልጸዋል።

አባ ማቴዎስ ቦንዶቦ ከቫቲካን የዜና ማሰራጫ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በመካከለኛው አፍሪቃ አገር ሰላምን ለማስፈን የሚደረግ ጥረት ቢኖርም ሙሉ ሰላምን ለማምጣት ጊዜን ይጠይቃል ብለው፣ በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የተረጋጋ ማሕበራዊ ሕይወት በመጠኑም ቢሆን እየታየ መሆኑን ገልጸዋል። ይህን ካሉ በኋላ በአንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ማነስና የሕይወት ዋስትና ማጣት እየታየባቸው መሆኑን ገልጸዋል። እርሳቸው በሚኖሩባት በባንጊ የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ከመሆኑ የተነሳ በመጠልያ ጥቢያ የቆዩት ቤተሰቦች ወደ መኖሪያ ቤታቸው እየተመለሱ መሆናቸውንና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችም እየተነሱ መሆናቸውን ከቫቲካን የዜና ማሰራጫ ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸው እ. አ. አ. በ2014 ዓ. ም. ከ15,000 በላይ ከባንዶሮ ግዛት የተፈናቀሉት ቤተሰቦች እስካሁን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ መኖራቸውን ገልጸዋል።

የመጠለያ ጣቢያዎች በአማጽያን በተያዙ አካባቢዎች፣

ክቡር አባ ማቴዎስ ቦንዶቦ በማከልም አሊንዳዎ በተባለ አካባቢ አማጽያኑ በከፈቱባቸው ጥቃት የተነሳ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲሰደዱ የተገደዱ በርካታ ቤተሰቦች በአካባቢው በሚገኝ ካቴድራል ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ አስረድተዋል። ምክንያቱን ሲገልጹ ለሕይወታቸ ዋስትናን ሊያገኙ የሚችሉበት ብቸኛው ስፍራ ስለ ሆነ ነው ብለዋል። በአመጸኞች እጅ በተያዙ አካባቢዎች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሊሄዱ አይችሉም፣ የትምህርት ቤቱ አስተዳደርም ሥራውን በሚገባ ማከናወን አይችልም፣ ሆስፒታልና የጤና ጣቢያዎች አገልግሎቶች ሥራቸውን ያቆሙ በመሆናቸው የጤና አገልግሎትን ማግኘት አይቻልም ብለዋል። በመሆኑም ለአካባቢው ነዋሪዎች ፈጣን የእርዳታ እጅ ያስፈልጋቸዋል ብልዋል። ፊደስ የተባለ የዜና ማዕከል በበኩሉ ባሰራጨው ዜና ተፈናቃዮቹ የሚገኙበትን ሁኔታ ሲገልጽ፣ ዕድሜአቸው ከአራት ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት ትክክለኛ የአስተዳደግ መስመርን የተከተሉ አይደሉም ብሎ፣ እነዚህ ሕጻናት ወላጆቻቸውን አያውቁም፣ የተመቻቸ መኖሪያ ቤት ስለሌላቸው በፍርሃትና በጭንቀት ውስጥ ሆነው ያድጋሉ ብሏል።

ብሔራዊ የጦር ሃይልና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይል እገዛ፣

የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ መንግሥት የጦር ሠራዊቱን በጦርነቱ በተጎዱት አካባቢዎች በማሰማራት፣ ከአማጺያን እጅ ነጻ በማውጣት፣ አካባቢውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑ ታውቋል። ቢሆንም ጥረቱ ጊዜን የሚወስድ እንደሆነ ክቡር አባ ማቴዎስ አስረድተው ወደ ስፍራው የሚሰማራው የጦር ሀይል በቅድሚያ በቂ ስልጠናን መውሰድ ያስፈልጋል ብለው ምክንያቱን ሲገልጹ የመካከለኛው የአፍሪቃ ሪፓብሊክ ሰፊ አገር በመሆኑ የእያንዳንዱን አካባቢ አቀማመጥ ማወቅ ይኖርባቸዋል ብለዋል። በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ የካጋ ባንዶሮ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ታዴዎስ ኩሲ ከፊደስ የዜና ተቋም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፓብሊክ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሠራዊት፣ ከመኖሪያ ሥፍራቸው ለተፈናቀሉት በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩት ሰዎች የሚሰጠው ድጋፍ ግልጽነትና ቅንጅት ይጎድለዋል ብለዋል። ብጹዕ አቡነ ኩሲ እንደገለጹት የመንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ሠራዊት ለሕዝቡ የሚያስተላለፉት መረጃዎች ይቃረናሉ ብለው፣ ሁኔታውን ሲያስረዱ በአንድ በኩል ወደ ቀድሞ መኖሪያ ስፍራቸው መመለስ እንደሚችሉ ሲነገራቸው በሌላ ወገን ደግሞ ከቀድሞ መኖሪያ ስፍራቸው በሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዲስ የመኖሪያ ቤት ተገንብቶላቸው መኖር እንደሚችሉ ሲነገራቸው እውነቱ የቱጋ እንደሆነ ለይተው ማወቅ ይሳናቸዋል ብለዋል። ይህን የመሰለ የዕቅድ አፈጻጸም ችግር እንደሚታይ፣ የካጋ ባንዶሮ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ታዴዎስ ኩሲ ገልጸዋል።

ሐዋርያዊ አገልግሎት ለሰላም ከሚድረርግ ጥረት ጋር ይተባበራል፣

በሐዋርያዊ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር ፈጥሯል ያሉት ክቡር አባ ማቴዎስ ቦንዶቦ፣ ይህን በመሰለ አጋጣሚ እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርሃን መመራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ሐዋርያዊ አገልግሎትን የምናከናውነው ምቹ በሆነ ጊዜና ቦታ ብቻ ሳይሆን በመከራና በስደት መካከልም ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል። አሁን በአካባቢው የሚሰጥ ቀዳሚ ሐዋርያዊ አገልግሎት በአስከፊ ችግር ውስጥ የወደቀን ሕዝብ ማጽናናትና ማበረታታት እንደሆነ የገለጹት አባ ማቴዎስ፣ ሕዝቡ እምነቱን ማጣት የለበትም፣ ለእምነቱ ምስክርነትን እየሰጠ በተግባር መኖር አለበት ብለው ይህ ለሰላም ጥረት አስተዋጽዖ እንዳለው ሲገልጹ፣ የሐዋርያዊ አገልግሎት እቅድ በማውጣት በዋና ከተማ በባንጊ ውስጥ ከሌሎች የእምነት ተካታዮች ጋር በነበራቸው የጋራ ውይይት መልካም መግባባት እንደተፈጠረ አስረድተዋል። በዚህ የጋራ ውይይት አማካይነት በአገራችን ውስጥ እያንዳንዳችን ለጋራ ጥቅምና ሰላም ስንል በሕብረት መስራትና መጣር ያስፈልጋል ብለዋል። 

[ Audio Embed ይህንን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ]    

   

26 October 2018, 15:34