ፈልግ

Braccianti morti: berretti rossi in marcia, "schiavi mai" Braccianti morti: berretti rossi in marcia, "schiavi mai"  

የደህንነት ዋስትና ለስደተኞችም ሆነ ስደተኞችን ለሚያስተናግዱ ሕዝቦች አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።

ስደተኞችን ተቀብሎ በስርዓት ለማስተናገድ የሚያስችል ጠንካራ ደንብ ያስፈልጋል ያሉት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ በማከልም ስደተኞች ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር በሚሄዱበት ጊዜ ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ እና አገሮች ድንበሮቻቸውን ለስደተኞች ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በኢጣሊያ የቦሎኛ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ፣ የደህንነት ዋስትና ለስደተኞችም ሆነ ስደተኞችን ለሚያስተናግዱ ክፍሎች አስፈላጊ መሆኑን ተነገሩ። ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ ይህን የተናገሩት በቅርቡ በኢጣሊያ ውስጥ ፎጃኖ በተባለ አካባቢ በስደተኞች ላይ የደረሰውን የሕይወት መጥፋት ምክንያት በማድረግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ስደተኞችን ተቀብሎ በስርዓት ለማስተናገድ የሚያስችል ጠንካራ ደንብ ያስፈልጋል ያሉት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ በማከልም ስደተኞች ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር በሚሄዱበት ጊዜ ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ እና አገሮች ድንበሮቻቸውን ለስደተኞች ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ቀዳሚ መፍትሄ መሆን ያለበት ግን ስደተኞች ለሚነሱባቸው አገሮች እርዳታን ማድረግ ያስፈልጋል ካሉ በኋላ ስደተኞችን በተመለከተ የወጡትን ሕጎችንና ደንቦችን አክብረን ስንገኝ ስደተኞችም እንዲያከብሩ ማድረግ እንችላለን ብለዋል።

የደህንነት ዋስትና ለስደተኞችም ሆነ ስደተኞችን ተቀብለው ለሚያስተናግዱ አገሮችም አስፈላጊ ነው ያሉት የቦሎኛው ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ ባለፈው ዓመት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በሀገረ ስብከታቸው በተቀበሉበት ጊዜ ባሰሙት ንግግር በቦሎኛ በተዘጋጀላቸው የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች የኑሮ ሁኔታ እጅግ ከባድ እንደነበር ገልጸው በደቡብ ኢጣሊያ ፎጃኖ ላይ በስደተኞች ላይ የደረሰው የመኪና አደጋ እጅግ አስከፊ እንደነበር አስታውሰዋል።

ፍርሃት የጠላትነትን ስሜት ይወልዳል፤

በብራንቻንቲ ከተማ የሚኖሩትንና በቁጥር እጅግ በርካታ የሆኑ ስደተኞችን ያስታወሱት የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ጓልቲየሮ ባሰቲ እንደገለጹት የሰው ልጅ ይህን በሚያህል በርካታ ቁጥር በአንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ መኖር ተገቢ አይደለም ብለው ይህ ዞሮ ዞሮ በሰዎች መካከል መናናቅን ሊያስከትል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል። ጣሊያኖች በመሠረቱ ዘረኞች አይደሉም ነገር ግን የደህንነት ዋስትናቸው ያልተከበረላቸው ከሆነ ስደተኞችን ተቀብሎ ከማስተናገድ ይልቅ ፍርሃት እንደሚይዛቸው የገለጹት የፔሩጃው ሊቀ ጳጳ፣ በመሆኑም ሌላውን እንደ ጠላት እንዲመለከቱ ከሚያደርጋቸው ፍርሃት ማላቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

ፍርሃት ጥሩ አይደለም፤

ፍርሃት ጥሩ ምሳሌ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን የሰጡት የቦሎኛ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ፣ በሕብረተ ሰቡ መካከል ፍርሃት እንደነገሰ ገልጸው፣ ለሰው ልጅ በሙሉ የቅርብ አለኝታነቷን በተግባር እየገለጸች የምትገኝ ቤተ ክርስቲያን፣ ለሰው ልጅ የሚገባውን ሰብዓዊ ክብርና ጥንቃቄ የምታደርገው አንገብጋቢ ችግሮችንም በመጠቆም ጭምር ነው ብለዋል።

ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስና የመቆየት መብት፣

በኢጣሊያ ውስጥ ለስደተኞች ሊደረግ የሚገባውን አስቸኳይ እርዳታን በማስመልከት አስተያየታቸውን የሰጡት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ እንደገለጹት፣ ስደተኞችን ተቀብሎ በስርዓት ለማስተናገድ የሚያስችል ጠንካራ ደንብ እና ሕግ ያስፈልጋል ብለው፣ መንግሥትም ስደተኞችን በተመለከተ የሚነሱ ችግሮችን ለማቃለል የሚያደርገውን ጥረት መመልከት ያስፈልጋል ብለዋል። ሊቀ ጳጳስ ማቴዎስ ዙፒ በማከልም ስደተኞች የሚሄዱባቸው አገሮች ድንበሮቻቸውን ክፍት እንዲያደርጉ በሚለው ሃሳብና ስደተኞች በአገሮቻቸው የመኖር መብታቸው እንዲከበርላቸው በሚሉት ሃሳቦች ላይ ቤተ ክርስቲያን ከምትሰጠው ድጋፍ ጎን፣ ስደተኞች ለሚወጡባቸው አገሮች አስፈላጊውን እገዛ በማቅረብ የሥራ ዕድሎችን እንዲከፍቱ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ይህን በማድረግም ስደተኞች ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ሲጓዙ በሕይወታቸው ላይ ሊደርስ ከሚችለው አደጋ ማዳን ይቻላል ብለዋል።

የአፍሪቃ ወጣት ስደተኞች ሥራ መፍታትን አይፈልጉም፣

የአፍሪቃ ወጣት ስደተኞች ያለ ሥራ መቀመጥ አይፈልጉም ያሉት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ፣ ከዚህ በፊት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ኤጂዲዮ ማህበር አስተባባር ሆነው የሠሩባቸውን ጊዜያት አስታውሰው፣ በእነዚያ ዓመታት እንደተገነዘቡት የአፍሪቃ ወጣት ስደተኞች ሥራ በሚፈቱበት ሰዓት የወደ ፊት ሕይወታቸው ይጨልምባቸዋል፣ ምን ማድረግ እንደሚገባም ይጠፋባቸዋል ብለዋል። በመሆኑም የደህንነት ዋስትና ለስደተኞችም ሆነ ስደተኞችን ለሚያስተናግዱ አገሮች ሕዝቦች አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

የቁጣ ቃላትን ማሰማት ይቅር፣

ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ በተጨማሪ እንዳስገነዘቡት የኢጣሊያ ሕዝብ በስደተኞች ላይ የሚናገራቸው የቁጣ ቃል ተገቢ እንዳልሆነ ገስልጸው ቁጣ ቁጣን ከመውለድ ሌላ ምንም ትርፍ የለውም ብለዋል። እያንዳንዱ ሰው በተሰማራበት ዘርፍ ሙሉ ክብር  ሊሰጠው ይገባል ብለው ሕዝቡ በስደተኞች ላይ የሚያስቀይሙ ቃላትን ከመናገር እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ስደተኞችን ማስተናገድ ማንነታችንን የበለጠ ለማወቅ ያግዘናል፣

ስደተኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ አቅማችን ምን ያህል እንደሆነ እንድናውቅ ያግዘናል ያሉት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ዙፒ ስደተኞች አገሮቻቸውን ለቀው ከሚሰደዱበት ምክንያቶች አንዱ ከአቅም ማነስ የተነሳ ነው ብለዋል። የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ጓልቲየሮ ባሰቲ በመጨረሻም ስደተኞችን በተመለከተ የወጡትን ሕጎችንና ደንቦችን አክብረን ስንገኝ ስደተኞችም እንዲያከብሩ ማድረግ እንችላለን ብለዋል።        

11 August 2018, 15:36