ፈልግ

በ2017 በዓለማቀፍ ደረጃ ለጦር መሳሪያ ግዢ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 1739 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ በ2017 በዓለማቀፍ ደረጃ ለጦር መሳሪያ ግዢ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 1739 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ 

በ2017 በዓለማቀፍ ደረጃ ለጦር መሳሪያ ግዢ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 1739 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ

በስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከወታደራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ወጪ ዓለማቀፍ ሪኮርድ መሰበሩን እና በ2017 ዓ.ም. በዓለማቀፍ ደረጃ ለጦር መሳሪያ ግዢ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 1739 ቢሊዮን ዶላር መደረሱን ኢንስቲውቱ ካወጣው ሪፖርት ለመረዳት ተችሉዋል።

በ2017 በዓለማቀፍ ደረጃ ለጦር መሳሪያ ግዢ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 1739 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ

በስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከወታደራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ወጪ ዓለማቀፍ ሪኮርድ መሰበሩን እና በ2017 ዓ.ም. በዓለማቀፍ ደረጃ ለጦር መሳሪያ ግዢ የወጣው አጠቃላይ ወጪ 1739 ቢሊዮን ዶላር መደረሱን ኢንስቲውቱ ካወጣው ሪፖርት ለመረዳት ተችሉዋል።

በዓለማች ውስጥ የሚገኙ ሀገራት ቀጣይነት ባለው መልኩ የጦር መሳሪያ ለመታጠቅ በመሽቀዳደም በመግዛት ላይ እንደ ሆኑ ይታወቃል። የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት በዓለማቀፍ ደረጃ ሰላም እና ፍትህ እንዲረጋገጥ በማሰብ የሰላም ጠንቅ የሆኑ ነገሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የሚያጠና እንስቲቱት እንደ ሆን የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ደግሞ ዓለማችን ስላሟን እንድታጣ ከሚያደርጉዋት ነገሮች መካከል በቀዳሚነት እና በዋነኛነት የሚጠቀሰው የጦር መሳሪያ ንግድ እና ስርጭት መሆኑን በማንሳት ይህ የጦር መሳሪያ ምርት እና ስርጭት እንዲገታ የራሱን አስተዋጾ በማድረግ ላይ የሚገኝ ዓለማቀፍ እንስቲቱት ነው። የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት በቅርቡ ባወጣው መረጃ እንደ ገለጸው በታሪክ ውስጥ የጦር መሳሪያ ግዢ እና ሽያጪ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረበቻው አመታት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ2012 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት የጦር መሳሪያ ንግድ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጨምሮ እንደ ነበረ በሪፖርቱ የገለጸ ሲሆን አሁንም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር 2017 ዓ.ም የጦር መሳሪያ ግዢ እና ሽያጭ ከእዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሪከርድ በመስበር በ2017 ዓ.ም. ብቻ 1,739 ቢልዮን ዶላር መድረሱን በሪፖርቱ በመግለጽ ይህ ሁኔታ በጣም አስደናግጭ መሆኑን ጨምሮ ገልጾ ይህ ወጪ ከ2016 ለጦር መሳሪያ ግዢ ከወጣው ወጪ 1.1% እድገት ማሳየቱን በሪፖርቱ ተገልጹዋል።

በስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት ባወጣው ሪፖርት ላይ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም. የጦር መሳሪያ ግዢ እና ሽያጭ ያደርጉት ሀገሮች ውስጥ ቀደም ሲል ከተጠቀሰው 1,739 ቢልዮን ዶላር ውስጥ 60% ይህም በቁጥር አሀዝ ሲቀመጥ 1,043.4 ቢልዮን ዶላር ወጪ ያደርጉ ሀገሮች በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው። አንደኛዋ እና ቀዳሚዋ አመሪካ ስትሆን ከእዚያም በመቀጠል ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ሕንድ እና ራሻ 60% ድርሻ በመውሰድ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር 2017 ዓ.ም. የመሳሪያ ግዢ አካሄደዋል። ይህ ቀደም ሲል የገለጽነው የገንዘብ አሀዝ ውስጥ 610 ቢልዮን ዶላር ውጪ በማድረግ በቀዳሚነት የመሳሪያ ግዢ የፈጸመችሁ ሀገር አመሪካ ስትሆን ከአመሪካ በመቀጠል ቻይና ትገኛለች። ሳውዲ አረቢያ በ2017 ዓ.ም. ብቻ 69.4 ቢልዮን ዶላር የመስሪያ ግዢ መፈጸሟ የተገለጸ ሲሆን ሕንድ 63.9% ቢልዮን ዶላር በ2017 ዓ.ም ብቻ ለጦር መሳሪያ ግዢ ማውጣቷ ተገልጹዋል።

ራሻ በ2017  66.3 ቢልዮን ዶላር ወጪ በማድረግ የመሳሪያ ግዥ መፈጸሟ የሚታወቅ ሲሆን ይህም በ2016 ዓ.ም. ራሻ የጦር መሳሪያ ግዢ ካወጣቸው ወጪ ጋር ሲነጻጸር 20% ቅናሽ እንዳሳየ በስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት ካወጣው ሪፖርት ለመረዳት ተችሉዋል።

11 July 2018, 09:26