ፈልግ

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን  

ካርዲናል ፓሮሊን ሁኔታዎች ቢመቻችሁ ኖሮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ቻይና ይሄዱ ነበር አሉ

በሮም ውስጥ የሚገኘው የጳጳሳዊ የሁርባኒያና ዩኒቨርሲቲ ለካርዲናል ሴልሶ ኮስስታንቲኒ እና ለቻይና የተሰጡትን ሥራዎች ለማቅረብ በቫቲካን ዋና ጸኃፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከቻይና ጋር ስለቀጠለው ውይይት እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለቻይና ሕዝብ ስላላቸው አድናቆት ተወያይተዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በአሁኑ ጊዜ ያለው ሁኔታ ገና ጊዜው ያልደረሰ ይመስላል፣ ነገር ግን "በቻይናውያን በኩል ግልጽነት ቢኖር ኖሮ ጳጳሱም ወዲያውኑ ወደ ቻይና ይሄዱ ነበር" ወደ ቻይና፣ ሁልጊዜም ለህዝቦቿ፣ ለታሪኳ እና ለሀገሯ፣ ለባህሏ ታላቅ አድናቆት እና ክብር ያሳዩባት ምድር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመሄድ ይፈልጉ ነበር ሲሉ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ተናግረዋል።

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አንድ ቀን ኃያሏን እና “ታላቋን” የኤዥያ አገርን ለመጎብኘት ያላቸውን ፈጽሞ የማይደበቅ ፍላጎት ደግመው ገልጸዋል።

የካርዲናል አስተያየቶች ሐሙስ ከሰአት በኋላ፣ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም በሮም ጳጳሳዊ ሁርባኒያና ዩኒቨርሲቲ "ካርዲናል ሴልሶ ኮስታንቲኒ እና ቻይና - በምስራቅ እና በምዕራብ መካከል ያለውን 'ድልድይ' ገንቢ -" በሚለው መጽሐፍ አቀራረብ ላይ አስተያየታቸው ሰጥተዋል።

የመጽሐፉን የአርትኦት ሥራ ያከናወኑት የጣሊያን የታሪክ ምሁር እና በቅድስት መንበር የስመተ ቅድስና ጉዳዮችን የሚመለከተው ተቋም ተወካይ ይሆኑ የእኔታ  ብሩኖ ፋቢዮ ፒጊን፣ የብፁዕ ካርዲናል ሴልሶ ኮስስታንቲኒ (1876-1958) ፣ የቻይና የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ልዑካን የሕይወት ታሪክ የተመለከተ በጣሊያንኛ ቋንቋ በማርሲየም ፕሬስ የታተመው መጽሐፍ ይፋ በሆነበት ወቅት ነበር ካርዲናል ፓቶሊን ይህንን ንግግር ያደረጉት።

ብፁዕ ካርዲናል ኮስታንቲኒ ያነሳሱት፣ ያስተዋወቁት እና ያደራጁት የኮንሲልየም ሲንሴን (የሴንሴን ጉባኤ) 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኡርባኒያና በተካሄደው ኮንፈረንስ ከአንድ ወር በኋላ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የቻይናን የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ልኡካንን ምስል በመቀስቀስ ነበር ለግንባታ መሠረት የጣሉት። ውይይት፣ ከእነዚህም ፍሬዎች አንዱ፣ ከብዙ አሥርተ ዓመታት በኋላ፣ በጳጳሳት ሹመት ላይ ከቅድስት መንበር ጋር የተደረገውን ስምምነት መፈረም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ያ ስምምነት እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈረመ ሲሆን በ2020 እና 2022 ሁለት ጊዜ ታድሷል።

የጳጳሳት ሹመት ስምምነት በዓመቱ መጨረሻ ይታደሳል

በካርዲናል ፓሮሊን በቀረበው ገለጻ ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት አጭር ውይይት ስምምነቱን አስታውሰዋል።

"ከቻይና ጋር ለተወሰነ ጊዜ እንደነበረው እየተነጋገርን ነው። በወቅቱ የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እና በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ የሚታደሰውን ስምምነት በጣም ጥሩውን አሰራር ለማግኘት እየሞከርን ነው" ብለዋል ለጋዜጠኞች ጥያቄዎች ካርዲናል ፓሮሊን ምላሽ ሲሰጡ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለቻይና ሕዝብ ያላቸው ክብር

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐሳብ በሣምንታዊው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማብቂያ ላይ ትናንት ሐሳባቸውን እንደገና ወደ ቻይና አዙረው ነበር፥ በቫቲካን ለተገኙ የቻይና ክርስቲያን ማሕበረሰብ አባላት ሰላምታ ሲያቀርቡ “የካርዲናል ሴልሶ ኮስታንቲኒ ጓደኞች” ፣ አጋጣሚውን ተጠቅመው “ለውድ የቻይና ህዝብ” ሰላምታዬ ይደረሳችሁ ሲሉ መናገራቸውን ካርዲናል ፓሮሊን አክለው ገልጸዋል።  

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "ለዚህ ክቡር ሕዝብ ሁሌም እንጸልያለን፣ ደፋር፣ እንደዚህ ዓይነት ውብ ባህል ስላለው ማለታቸው ተገልጿል።

ካርዲናል ፓሮሊን አስተያየት ሲሰጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "በእርግጥ ታላቅ አድናቆት አላቸው እና ለቻይና ሕዝብ እና ለቻይና ብሔር ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማሉ። ምናልባት እርሳቸው የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል ስለሆኑ ነው። ስለዚህ ሁሉም ቅርስ አለው። ያለፈው ... በእርግጠኝነት እነዚህ ሁሉ እርስ በርስ ለመረዳዳት ፣ ለመቀራረብ እና ለመረዳዳት የሚጠቅሙ እርምጃዎች ናቸው ብለዋል ።

እውን ሊሆን የሚችል የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጉብኝት በቻይና

በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሐዋርያዊ ጉዞን የሚያመለክት ጳጳሳዊ ጉብኝት ሊሆን እንደሚችል ሲጠየቁ ካርዲናል በጥንቃቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

"በእርግጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ቻይና ለመሄድ ፈቃደኛ ናቸው፣ በእርግጥ ወደ ቻይና መሄድ ይፈልጋሉ" ብለዋል፣ "ለእኔ ግን አይመስለኝም፣ እስካሁን ድረስ ይህ የጳጳሱ ምኞት እውን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሊተገበሩ የሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ” ብለዋል።

"ቻይና ለልባችን ቅርብ ነች"

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በመቀጠል በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባደረጉት ንግግር ለቻይና ያላቸውን ፍቅር ደግመው ገልጸዋል።

ቻይናን፣ ህዝቦቿን፣ ባህሏን፣ ወጎቿን፣ አሁን እያደረገች ያለውን ጥረት እናደንቃለን።... "በእውነቱ ቻይና ለልባችን ቅርብ ናት፣ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ለተባባሪ የሥራ ባለሟሎች ልብ ቅርብ ነች" ብለዋል።

የኮስታንቲኒ ዘዴ

በዝግጅቱ ላይ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ብፁዕ ካርዲናል ኮስታንቲኒን አስታውሰዋል።

በተለይም ሐዋርያዊ ልዑካን እ.አ.አ በ1946 ዓ.ም ወደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ 12ኛ ሄዶ የቻይናውን ጳጳስ ስም በጳጳሳት ምርጫ ውስጥ እንዲካተት እና 32 አዲስ ካርዲናሎች ውስጥ እንዲካተት ሲጠይቁ እና ስማቸውም የተገለጸበት እና ካርዲናልን በማወደስ ያሉ ታሪኮችን አቅርቧል። “የወንጌል ብርሃንን በቻይና ለማዳረስ” እና ከሁሉም በላይ የተቀረጸች ቤተክርስቲያንን ለማስተዋወቅ ጥረት፣ ስራዎች እና መስዋዕትነትን ከፍለው ነበር ብለዋል።

እ.አ.አ በ1924 ዓ.ም በሻንጋይ የተካሄደውን ሐዋርያዊ ጉባኤ አጥብቀው የጠየቁት ካርዲናል ኮስታንቲኒ ለሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ትንቢታዊ መነሳሳት እና እ.አ.አ በ1963 ዓ.ም 23 ጳጳሳትን ያቀፈች የቻይና ቤተክርስቲያን መሰረት የጣሉት ካርዲናል ኮስታንቲኒ ነበሩ። በቻይና ከሚገኙ ብዙ የሚስዮናውያን ተቋማት ተቃውሞ በወቅቱ ቢገጥማቸውም።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን "ለአሁኑ ጳጳሳት የሐዋርያዊ ሹመት መስመርን ተከትለዋል" ብለዋል።

የቻይናውያን ጳጳሳት ከጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር

በቅድስት መንበር እና በትልቁ እስያ ግዛት መካከል ያለው "የኮስታንቲኒ ዘዴ" ዛሬ "የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስም የተከተሉት አቅጣጫ ነው" ሲሉ የካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ተናግረዋል ። ይህ በተመሳሳይ መልኩ በቤኔዲክት 16ኛ እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም የፃፉትን 'ለቻይና ካቶሊኮች መልእክት' እና እ.አ.አ በ 2018 ቤጂንግ ላይ ለጳጳሳት ሹመት ከተፈረመው "ጊዜያዊ" ስምምነት ጋር የተጣጣመ ነው።

"በስምምነቱ ምክንያት በኮንፊሽየስ እምነት ተከታዮች ምድር ያሉ ሁሉም ጳጳሳት ከቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ጋር ሙሉ በሙሉ ግንኙነት አላቸው" ያሉት ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ስለዚህም “በቻይና ካቶሊኮች የተጀመረው ውይይትና ሂደት በመጋቢዎቻቸው እየተመራ የላቀ ስምምነትን ለመፍጠር፣ ለፍቅሩ ብዙ ማረጋገጫ ከሰጡ ጳጳስ ጋር ሙሉ ቁርኝት ለመፍጠር የተጀመረው ውይይት እና ሂደት እንደሚቀጥል ተስፋ አሁንም ይኖራል” ሲሉ ተናግረዋል።

 

21 June 2024, 16:39