ፈልግ

ብጹዕ ካርዲናል  ፒዬትሮ ፓሮሊን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ በደቡብ ሱዳን ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የቅድስት መነበር ዋና ጸሐፊ በደቡብ ሱዳን ሐዋርያዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት  

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፡ “አፍሪካ የተስፋ ምድር ናት” ማለታቸው ተገለጸ!

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፅዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ለቫቲካን መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የአፍሪካ አህጉር ፈተናዎችን ለመጋፈጥ የሚያስችል አቅም እና ሃብት ቢኖራትም "ህዝቡ እና ደህንነታቸው ማስቀደም አለባቸው" ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"የደስታ ጊዜ" የእኛ "የግል" ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልገን በማረጋገጥ...

ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን 61ኛውን የአፍሪካ ቀን ምክንያት በማድረግ ሰኞ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በሮማ በሚገኘው ማሪያን ባሲሊካ በሳንታ ማሪያ ሜጄር ያደረጉትን የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነ-ስረዓት ካጠናቀቁ በኋላ ነበር መግለጫውን የሰጡት።

በቅድስት መንበር የአፍሪካ ቡድን አምባሳደሮች፣ ለጣሊያን ሪፐብሊክ እውቅና የተሰጣቸው የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ልዑካን እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት FAO/WFP/IFAD እውቅና የተሰጣቸው ቋሚ አፍሪካውያን ተወካዮች ተገኝተዋል። ከሮማን ኩሪያ የተውጣጡ አፍሪካውያን ቀሳውስት እና በጣሊያን የሚገኙ አፍሪካውያን ካህናት ተገኝተዋል።

ፈተናዎች እና ተስፋዎች

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በስብከታቸው ላይ ስለ አፍሪካ የተናገሩትን በነዲክቶስ 16ኛ እና ከእርሳቸው በፊት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ በድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ስብከት ስለአፍሪካ እ.አ.አ በ1995 ዓ.ም ላይ ጠቅሰው የአህጉሪቱን ፈተናዎች፣ ችግሮች እና “ንፅፅር” አጉልተው ገልጸው ነበር፣ ነገር ግን በተጨማሪም የአፍሪካ አህጉር ተስፋዎች ጭምር ገልጸው ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ለቫቲካን ረዲዮ - ቫቲካን ዜና በበዓሉ አከባበር ላይ እንዳሉት "ይህ በዓል ለአፍሪካ ቅርብ ስለሆንኩኝ ግላዊ ገጽታ አለው" ሲሉ አስታውሰው "ባለፉት ዓመታት በርካታ አገሮችን መጎብኘት ችያለሁ እና ግንኙነት አድርጌያለሁ። ከቤተክርስቲያን እና ከመንግሥታት እና ከባለሥልጣናት ጋር” በማለት የተናገሩት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን "ለእኔ" እዚህ መሆን የደስታ እና የጸሎት መካፈል የደስታ ጊዜ ነው" ብለዋል።

የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ አስፈላጊነት

“እኔ አምናለሁ” ሲሉ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተናገሩ ሲሆን አክለውም “አፍሪካ በራሷ አቅም ማሳካት አለባት፤ ጥንካሬ አላት፣ ሃብት አላት፣ የሁሉም ዓይነት ሀብት አላት፣ ነገር ግን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር የሚሰሩ ቅን ወዳጆች ያስፈልጋታል። ህዝቡ ለሰላም፣ ለእርቅና ለልማት እንዲሰራ ማበረታታት ያስፈልጋል” ብለዋል።

አህጉሪቱ “በጣም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ራሷን የምታገኘው በብዙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ስቃይ የሚያስከትሉ ግጭቶች” ውስጥ በመሆኗ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን በተለይም ምስራቃዊ የኮንጎ ግዛትን ማሰብ ተገቢ ነው ብለዋል።

ካርዲናሉ “የመውጣት ዕድል እንዳለ” ያላቸውን እምነት ሲገልጹ፣ “መርሁ ሁል ጊዜ አንድ ነው፡ ሕዝብና ደህንነታቸው ማስቀደም አለባቸው” ብለዋል።

"ቁሳዊ ጥቅም ቅድሚያ ከተሰጠ በእርግጥ ሰዎች መስዋእት ናቸው እና ለሰላም ምንም ዕድል የለም" ብለዋል። "ይሁን እንጂ ፍትህ ካለ፣ ሁሉም ሰው ቁሳዊ ሀብት ማግኘት የሚችል ከሆነ - እና ይህ የሁለቱም የሀገር ውስጥ ባለስልጣናት እና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተግባር ነው" ብለዋል ።

የቅድስት መንበር ርዳታ

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በበኩላቸው “አንድ ቤተሰብ በመሆናችን ቅድስት መንበር በአፍሪካ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ ትረዳለች፤ እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለአፍሪካ በሚያሳዩት ቀጥተኛ ፍላጎት” በማለት አረጋግጠዋል።

የዓለም አፍሪካ ቀን

የአፍሪካ አህጉር ህዝቦች የአለም አፍሪካ ቀንን እ.አ.አ በግንቦት 25 አክበረው አለፈዋል፤ ምክንያቱም በዚህ ቀን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ1963 ዓ.ም ስምምነቶች የተፈረሙ ሲሆን ይህም አጠቃላይ የአህጉሪቱን የነጻነት ፣የልማት ፣የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እድገት ትግል የሚያመለክቱ ናቸው ። የአፍሪካ የባህል ሀብት ማስተዋወቅ እና የተፈጥሮ ሐብት ብዝበዛን የሚቃወም ድርጅት ነው።

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እ.አ.አ ግንቦት 25 ቀን 1963 በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 33 ፈራሚ መንግስታት ያሉት በይነ መንግስታት የተመሰረተ ድርጅት ነው። የአፍሪካ ህብረት (AU) እ.ኤ.አ. ነሐሴ ወር 2002 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ደርባን ውስጥ በይፋ ስራ የጀመረ ሲሆን እ.አ.አ በመስከረም 1999 ዓ.ም የአፍሪካ ህብረት ስራውን ለማጠናከር አዲስ አህጉራዊ ድርጅት ለመፍጠር በወሰነው መሰረት የተቋቋመ ነው።

እ.አ.አ ግንቦት 25/1963 ዓ.ም ቀን የተቋቋመው ድርጅቱ ሁለት ቀስቃሽ ኃይል አለው። በመጀመሪያ፣ በትዝታ፣ የመጀመሪያ ጊዜያትን ያስታውሳል። ሁለተኛ፣ በጂኦፖለቲካዊ እና በተቋም ደረጃ፣ በመስራች አባቶች የታለመውን አፍሪካን ለመገንባት በግለሰብ እና በጋራ አቅም ላይ በየጊዜው ጥያቄዎችን ያስነሳል።

ቀኑ በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ስር የሰደደ ባህል ሆኖ በቅድስት መንበር እውቅና የተሰጣቸው የአፍሪካ ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች አህጉሪቱ በአለም ላይ ያላትን ሚና ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚያስችሉ ዝግጅቶችን የሚያዘጋጁበት እድል ነው።

29 May 2024, 13:42