ፈልግ

C9 በመባል የሚታወቀው የ9 ካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ ስብሰባ በቫቲካን መቀጠሉ ተገለጸ! C9 በመባል የሚታወቀው የ9 ካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ ስብሰባ በቫቲካን መቀጠሉ ተገለጸ! 

C9 በመባል የሚታወቀው የ9 ካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ ስብሰባ በቫቲካን መቀጠሉ ተገለጸ!

የካርዲናሎች ምክር ቤት በሚያዝያ ወር የሚያደርገውን ጓባሄ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተገኙበት ባለፈው ሰኞ ሚያዚያ 7/2016 ዓ. መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ይህ ጉባሄ ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው በየካቲት ወር ማብቂያ ላይ እንደ ነበረ ይታወሳል፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሴቶች ሚና መሪ ሃሳብ ላይ ካርዲናሎች እና ጳጳሳት ያበረከቱትን ሚና የሚገልጽ የሶስት ሴቶች ተሳትፎ ተመልክቷል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ማክሰኞ ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተገኙበት የካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባ መቀጠሉ የተገለጸ ይህ ክፍለ-ጊዜ ከላይ ለመጥቀስ እንደ ተሞከረው ባለፈው ሰኞ እለት ነበር የተጀመረው።

የየካቲት ስብሰባዎች

የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ የተካሄደው እ.አ.አ ከየካቲ 5 እስከ 7/2024 ዓ.ም የነበረ ሲሆን ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ሚና ላይ አስተዋፅዖ ያደረጉ ሶስት ሴቶችን ያሳተፈ ነበር። በሮም በሚገኘው ጳጳሳዊ የሳይንስ የትምህርት ተቋም አባላት የሣሌዥያን ማሕበር አባል የሆኑ እህት እና የክርስቶሎጂ (የነገረ-ክርስቶስ አስተምህሮ) እና ማሪዮሎጂ (የነገረ ማርያም አስተምህሮ) መምህር የሆኑት ሲስተር ሊንዳ ፖቸር፣ ጁሊቫ ዲ ቤራዲኖ፣ የቬሮና ሀገረ ስብከት ኦርዶ ቬርጂኑም ማሕበር አባል፣ መምህር፣ እና የመንፈሳዊ ትምህርት እና መንፈሳዊ ልምምዶች መምህርት፣ ጆ ቤይሊ ዌልስ፣ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ እና የአንግሊካን ሕብረት ምክትል ዋና ጸሐፊ ይገኙበታል። ባልፈው የካቲት ወር ላይ ካርዲናሎቹ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከመማክርት ጉባሄ አባላት ጋር ያደረጉት ስብሰባም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሲኖዶሳዊ ሂደት እና በስብከተ ወንጌል መሪ ሃሳብ ላይ ያተኮረ ሲሆን ብፁዕ ካርዲናል ሉዊስ አንቶኒዮ ታግሌ እና  ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚኬላ አስተዋጽዖ አድርገዋል።

"አዲስ" C9

እ.ኤ.አ. በመጋቢት 7/2023 ዓ.ም በሊቀ ጳጳሱ የመማክርት ጉባሄው መታደሱን ተከትሎ፣ የካርዲናሎች ምክር ቤት በቫቲካን ዋና ጸኃፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተዋቀረ ነው። የቫቲካን ግዛት ጳጳሳዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እና የቫቲካን ከተማ ጠቅላይ ግዛት ዋና ኃላፊ የሆኑት ፌርናንዶ ቬርጌዝ አልዛጋ ፍሪዶሊን አምቦንጎ ቤሱንጉ፣ የኪንሻሳ ሊቀ ጳጳስ፣ ኦስዋልድ ግራሲያስ የቦምቤይ ሊቀ ጳጳስ፣ ሴያን ፓትሪክ ኦማሌይ የቦስተን ሊቀ ጳጳስ፣ ሁዋን ሆሴ ኦሜላ የባርሴሎና ሊቀ ጳጳስ፣ ጄራልድ ላክሮክስ የኩቤክ ሊቀ ጳጳስ፣ ዣን ክላውድ ሆሌሪች የሉክሰምበርግ ሊቀ ጳጳስ፣ ሰርጆ ዳ ሮቻ፣ የሳኦ ሳልቫዶር ዳ ባሂያ ሊቀ ጳጳስ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ነበር። ጸሐፊው ዬኔታ ማርኮ ሜሊኖ፣ የክሬሲማ ጳጳስ ጳጳስ ናቸው።

የካርዲናሎች ምክር ቤት ማቋቋም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በመስከረም 28/2013 ዓ.ም በአለማቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ እርሳቸውን ለመርዳት እና የሮማን ኩሪያን ለማሻሻል ፕሮጀክት ለማጥናት ምክር ቤቱን በአስቸኳይ አቋቋሙ። ይህ ተግባር እ.አ.አ በመጋቢት 19/2022 ዓ.ም በታተመው በላቲን ቋንቋ “praedicate Evangelium” (ወንጌልን ስበኩ) በተሰኘው አዲሱ ሐዋርያዊ ሕግጋት ውስጥ ይፋ መሆኑ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት የመጀመሪያው የዘጠኙ ካርዲናሎች የመማክርት ጉባሄ የተካሄደው እ.አ.አ በጥቅምት 1/2013 እንደ ነበረም ይታወሳል።

 

17 April 2024, 21:29