ፈልግ

የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ   (AFP or licensors)

በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ዓለም አቀፍ ትብብር ማስፈለጉ ተገለጸ

ቅድስት መንበር በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለማስቆም አዳዲስ እርምጃዎች ያስፈልጋሉ የሚለውን የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔን ደግፋለች። ቅድስት መንበር ይህን ያስታወቀችው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 78ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሆነ ታውቋል። ቅድስት መንበር በተጨማሪም እርምጃዎቹ ወንጀለኞችን የማሰቃየት ወይም የሞት ቅጣት ወደሚበይኑ አገራት ተላልፈው እንዳይሰጡ ጠይቃለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በኒውዮርክ ሐሙስ መጋቢት 26/2016 ዓ. ም. በተካሄደው 78ኛ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የቅድስት መንበርን ድጋፍ በንግግር የገለጹት በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ ናቸው።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ካቻ በንግግራቸው፥ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚያግዙ ጠቅላላ እና አስገዳጅ ሕጋጎችን ቤተ ክርስቲያን እንደምትደግፍ አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህም የእያንዳንዱን ሰው ክብር ለማስጠበቅ፣ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማበረታታት እና ወንጀለኞች ላይ የሚፈጸሙ የማሰቃየት ተግባርን ለማስቆም የሚያግዝ ዘዴ ይሆናል በማለት አስረድተዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል እንደዚሁም፥ ማንኛውም ዓይነት ስምምነት በዓለም አቀፍ ደረጃ መጽደቁ አስፈላጊ እንደሆነ በማስገንዘብ፥ ወንጀሎች ሲገኙ አዲስ ሕግ ለማውጣት ሳይሆን ያሉትን ልማዳዊ ደንቦች በጥንቃቄ መከተሉ ወሳኝ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

እስረኞችን ከጉዳት መጠበቅ

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባሰሙት ንግግር፥ እስረኞችን የመጠበቅ አስፈላጊነት ላይም አትኩረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ምክትል ቋሚ ታዛቢ አቡነ ሮበርት መርፊ የቅድስት መንበርን መልዕክት ለጉባኤው አባላት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፥ ማንም ሰው በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ሊደርስ ወደሚችልበት ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ የሚለውን ረቂቅ ሕግ አንቀጽ ቁ. 5 በደስታ ተቀብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል እንደተናገሩት፥ ይህ አንቀፅ ማንም ሰው ለስቃይ ወይም ለሞት ቅጣት ሊጋለጥ ወደሚችልበት ፍርድ ተላልፎ እንዳይሰጥ ያግዳል ብለዋል። ለወንጀለኞች የሚደረግ ፍትሃዊ አያያዝ እና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ግዴታዎችን የሚያስከብረውን አንቀጽ 11 ን በደስታ ተቀብለዋል። ነገር ግን አንቀጹ ወንጀለኞች ወደ ነበሩበት ሥፍራ ተመልሰው ከማኅብረተሰባቸው ጋር የሚታረቁበትንም መንገድ ማዘጋጀት እንዲቻል ሊራዘም ይገባል ብለዋል። አቡነ ገብርኤል በማከልም፥ በተለይም ወንጀለኞቹ ከፈጸሙት ጥፋት መታረም እንዲችሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ዕርዳታን ማግኘት አለባቸው ብለዋል።

የሞት ቅጣት ፍርድ

አቡነ ሮበርት መርፊ በንባብ የቀረቡትን ሦስተኛውን ንግግር አስመልከተው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል አስተያየት ሲሰጡ፥ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ ተቀባይነት ካገኘ፥ “የመኖር መብትን የማስከበር፣ ማሰቃየትን የመከላከል እና ሌሎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶችን ከማክበር ግዴታዎች ጋር ግጭት እንዳይፈጠር መከላከያዎችን ማበጀት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመሆኑም የሞት ቅጣትን ያስቀሩ መንግሥታት ወንጀለኞችን በሞት ወደሚቀጡ መንግሥታት ተላልፈው እንዳይሰጡ የሚለውን ረቂቅ አንቀጽ 13/7 ን ቤተ ክርስቲያን እንደምትደግፍ ገልጸዋል። በተመሣሣይ ሁኔታም በሕጋቸው ውስጥ የሞት ቅጣትን የሚያስቀምጡ ነገር ግን በተግባር የማይተገበሩ መንግሥታት ወንጀለኞችን ለሞት አሳልፈው መስጠትን ማውገዝ አለባቸው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

 

 

06 April 2024, 16:50