ፈልግ

2020.10.28 armi nucleari, missili, guerra, armamenti, disarmo atomico

ቅድስት መንበር፡ ‘የኑክሌር የጦር መሣሪያን መከላከል ቅዠት እየሆነ ነው’ ማለቷ ተገለጸ!

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቫቲካን ቋሚ ታዛቢ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦር መሣሪያ ትጥቅ ማስፈታት ኮሚሽንን ባነጋገረበት ወቅት የኑክሌር ጦር መሣሪያ የመገደብ አመክንዮ ሃሳባዊ መሆኑን በማረጋገጥ በኑክሌር የጦር መሳሪያዎች ክልከላ ላይ የተፈፀመውን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ አብርኾት) ለመቆጣጠር የሚያስችል አስገዳጅ አለም አቀፍ ስምምነት እንዲፀድቅ ይጠይቃል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በዓለም ዙሪያ እየጨመረ በሚሄደው ወታደራዊ ወጪ እና ግጭት ውስጥ፣ ቅድስት መንበር የሰላም የቅዠት ሐሳብ ብቻ የሚያቀርበውን የኒውክሌር መሣሪያዎችን መከላከያን ውድቅ ለማድረግ አስቸኳይ ልመናዋን በድጋሚ ገልጻለች። በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ጋብሪኤሌ ካቺያ “ግጭትን ከመከላከል ይልቅ የጦር መሳሪያዎች መገኘት አጠቃቀማቸውን ያበረታታል እና ምርታቸውን ይጨምራል”፣ አለመተማመንን ይፈጥራል እና የሀብትን አቅጣጫን ያስቀይራል ማለታቸው ተገልጿል።

የሞራል ግዴታ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቫቲካን ቋሚ ታዛቢ ሰኞ መጋቢት 21/2016 ዓ.ም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦር መሳሪያ አስፈቺ ኮሚሽን በሰጡት መግለጫ የጦር መሳሪያ መግዛት፣ ማከማቸት እና መጠቀም አቁመን ትጥቅ መፍታት “የሞራል ግዴታ” መሆኑን አረጋግጠዋል። ፍርሃት ወደ የመተማመን ሚዛን መቀየር አለበት”፣ ዘላቂ ሰላም የሚሰፍንበት ብቸኛው መሰረት ነው ብለዋል።

“የማስመሰል አመክንዮ – ሊቀ ጳጳስ ካቺያ እንዳስታወቁት - ብዙውን ጊዜ ፍትሃዊ ያልሆነውን ማለትም የኑክሌር ጦር መሳሪያ መታጠቅን ለማስረዳት ይጠቅማል፣ “ማንኛውም አጠቃቀሙ አሰቃቂ ሰብአዊ እና አካባቢያዊ መዘዞችን ያስከትላል፣ ይህም ተዋጊዎችን እና ያልሆኑትን አይለይም መጠነ ሰፊ እልቂት ልያስከትል ይችላል ብለዋል።

ስለዚህም ሁሉም ሀገራት የኑክሌር ጦር መሣሪያ ክልከላን (TPNW) እንዲቀላቀሉ የቅድስት መንበር ጥሪዋን በድጋሚ በማሳሰብ “የደህንነት አሉታዊ ጽንሰ-ሀሳብን በአዎንታዊ መልኩ ለመተካት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ያደርጋሉ ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

በማንኛውም የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንቅስቃሴ ላይ መሳተፍን የሚከለክሉ ሁሉን አቀፍ ስብስቦችን ያካተተው ስምምነቱ በ122 አገሮች ተፈርሞ እ.አ.አ በ2017 ተቀባይነት አግኝቷል።

ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አብርኾት) የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ በሰጡት መግለጫ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አጠቃቀምን በተመለከተ መደበኛ እና ተግባራዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቅድስት መንበር የሰው ሰራሽ አብርኾት ኤጀንሲን ለመፍጠር ያቀረበችውን ሃሳብ ደግመው ገልፀው በተመሳሳይ ጊዜ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ልማትን እና አጠቃቀምን የሚቆጣጠር አስገዳጅ ዓለም አቀፍ ስምምነት ለማድረግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተባብሮ እንዲሠራ አሳስበዋል።

እንዲህ ያለው የአስተዳደር ሥርዓት፣ “በታዳጊ ቴክኖሎጂዎች ላይ ከተወሰኑ ጥቅሞች ይልቅ የሰውን ልጅ በአጠቃላይ እንደሚያገለግል ለማረጋገጥ ይረዳል” ብሏል።

"በዓለም አቀፍ የኒውክሌር ቴክኖሎጂ አስተዳደር እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀምን በተመለከተ መደበኛ እና ተግባራዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በሚያስፈልግበት ጊዜ መካከል ብዙ ተመሳሳይነቶች ሊቀርቡ ይችላሉ" ሰላም በጦር መሳሪያ አይገነባም ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ገልጸዋል።

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ሲያጠቃልሉ፣ የቅድስት መንበር ያለማቋረጥ “የጦር መሣሪያ ድምጽ እንዲያበቃ” የምታደርገው ጥሪ ቀስ በቀስ ግን ፍጹም ትጥቅ የማስፈታቱን መንገድ በቆራጥነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅ ይህንን መንገድ እንዲከተል የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ የገለጹ ሲሆን “ሰላም የሚገነባው በጦር መሣሪያ ሳይሆን በትዕግስት በመደማመጥ፣ በመነጋገርና በመተባበር ነው። ልዩነቶችን ለመፍታት ለሰው ልጅ ብቁ መንገድ ሆኖ የሚቀረው የሰላም መንገድ ነው ማለታቸውም ተገልጿል።

04 April 2024, 15:30