ፈልግ

ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በቬትናም ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በቬትናም   (Vatican Media)

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር በቬትናም የ6 ቀን ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተገለጸ!

ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በቬትናም ዲፕሎማሲያዊ ጉብኝት እንደ ሚያደርጉ የተገለጸ ሲሆን በእዚያም ከቬትናም ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲሁም ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቫቲካን ከሌሎች ሀገሮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆታጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በሚያዝያ 02/2016 ዓ.ም ወደ ቬትናም የሚያደርጉትን ጉዞ የጀመሩ ሲሆን እስከ እሁድ ሚያዚያ 6/2016 ዓ.ም በእዚያ እንደሚቆዩ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡይ ታንህ ሶን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺን ጋር የሚደረጉ ስብሰባዎችን ያካትታል።

ከቬትናም የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያጠናክር ስብሰባ እና እንዲሁም በቬትናም በሚገኘው በቅዱስ ዮሴፍ ካቴድራል ተገኝተው መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያስርጉ ይጠበቃል። የሊቀ ጳጳስ ጋላገር ፕሮግራም ከዓብይ የዘረዓ ክህነት ተማሪዎች ጋር ለመገናኘት እና በፉ ካም ካቴድራል መስዋዕተ ቅዳሴን ለማሳረግ ወደእዚያው እንደሚያቀኑ ተገልጿል።

እ.አ.አ በታኅሣሥ ወር ቅድስት መንበር በቬትናም የሚኖሩ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቋሚ ተወካይ አድርጋ የፖላንድ ተወላጅ የሆኑትን ሊቀ ጳጳስ ማሬክ ዛሌቭስኪ ለመሾም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

እ.ኤ.አ. መጋቢት 31 ቀን 2023 በሮም በተካሄደው የቬትናም እና ቅድስት መንበር የጋራ የስራ ቡድን አሥረኛው ክፍለ ጊዜ ላይ በመመስረት ስምምነቱ እ.አ.አ በሐምሌ ወር 2023 ፕሬዝዳንት ቮ ቫን ቱንግ ቫቲካን በጎበኙበት ወቅት መፈረሙ ይታወሳል።

ሊቀ ጳጳስ ጋላገር በዓመቱ ውስጥ የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ከብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ጋ በመሆን ሀገሪቱን ሊጎበኙ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን ወደፊት በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሊጎበኟቸው እንደሚችሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸው ነበር።

የቬትናምን አስፈላጊነት እና ደረጃዋን እንደ "ኢኮኖሚያዊ ተአምር በብዙ መልኩ" አጉልቷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለቬትናም ቤተ ክርስቲያን የላኩት መልእክት

ቬትናም እና ቅድስት መንበር እ.አ.አ በ1975 ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ያቋረጡ ቢሆንምእ.አ.አ  ከ1990 በኋላ አወንታዊ ለውጦች መታየት ጀመሩ።

እ.ኤ.አ. በ 2011 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በቬትናም ቋሚ ነዋሪ ያልሆኑ የጳጳስ ተወካይ ሾሙ እና በ 2023 ሁለቱ ወገኖች ቋሚ ተወካይ ለመመደብ የሚያስችል ደንብ አረቀቁ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ. በመስከረም ወር 2023 በቬትናም ለምትገኘው ቤተክርስቲያን የካቶሊክ ምእመናን እንደ “ጥሩ ክርስቲያኖች እና ጥሩ ዜጎች” እንዲኖሩ የሚያሳስብ ደብዳቤ ላኩ።

በሃይማኖት፣ በዘርና በባሕል ሳይለዩ የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲመሰክሩ ጥሪ አቅርበው "መሰባሰብንና ልዩነቶችን ማክበር" አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበው ነበር። ይህ አካሄድ ካቶሊኮች እንደ ጥሩ ክርስቲያኖች እና ዜጎች ቤተ ክርስቲያናቸውን በማንቃት እና ወንጌልን በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው በማስፋፋት የክርስትና ሕይወት መታወቂያቸውን እንደሚያሳይ ሊቀ ጳጳሱ ተናግረው የነበረ ሲሆን “የሃይማኖት ነፃነትን ለመጠቀም ምቹ ሁኔታዎች” ባሉበት የካቶሊኮች ምሥክርነት ውይይትና የቬትናም ተስፋን ለማስተዋወቅ ይረዳል ብሏል።

10 April 2024, 16:26