ፈልግ

ከጣሊያን ቴሌቭዥን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬርባቲስታ ፒዛባላ ከጣሊያን ቴሌቭዥን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬርባቲስታ ፒዛባላ   (REUTERS)

ብጹዕ ፓትርያርክ ፒዬርባቲስታ በጋዛ ያለው ሁኔታ ሊታገሡት የማይችሉት መሆኑን ገለጹ

በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓተ አምልኮን የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬርባቲስታ ፒዛባላ ከጣሊያን ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በጋዛ ያለውን ሁኔታ ሊታገሡት የማይችሉት እንደ ሆነ ገልጸው፥ “በጋዛ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ስቃይ ለማስወገድ ሁሉም ሰው የቻለውን እንዲያደርግ” በማለት አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬርባቲስታ ፒዛባላ በቅርቡ TV2000 ከተሰኘ የጣሊያን ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጋዛ ያለውን ሁኔታ ሲገልጹ፥ በእርግጥ ሊታገሱት የማይችል ነው!" በማለት ተናግረዋል።

“ከዚህ በፊት ብዙ ዓይነት ችግሮች አጋጥመውናል፤ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ አቅማችን ሁልጊዜ ደካማ ቢሆንም ነገር ግን ረሃብ አልነበረም” ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ሕይወት ድርጅቶችን ጨምሮ ሁሉም ሰው በቅድስት አገር ውስጥ ያለውን ስቃይ ለማስቆም የተቻለውን ሁሉ ማድረግ አለበት” በማለት ብጹዕ ፓትርያርክ ፒዛባላ አሳስበዋል።

“የአሜሪካ መንግሥት ድክመት ትልቅ አጣብቂኝ ፈጥሯል” ያሉት ፓትርያርኩ፥ እስከ ዛሬ ድረስ ጉዳዮችን የሚያስተካክል ክፍል እንደ ነበር በማስታወስ፥ አሁን ግን ይህን ሚና የሚጫወት ማንም ባለመኖሩ እራሳቸው ማስተካከል እንዳለባቸው አጽንዖት ሰጥተው ይህም መቼ እና እንዴት ሊሆን እንደሚችል አናውቅም በማለት ተናግረዋል።

ብርሃነ ትንሳኤውን በጦርነት መካከል ማክበር

በላቲን የሥርዓተ አምልኮ ቀን አቆጣጠር የሕማማት ሳምንት ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት ቀደም ብለው ቃለ ምልልስ ያደረጉት ብጹዕ ፓትርያርክ ፒዛባላ፥ በፍልስጤም ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች በሕማማት ሳምንት ውስጥ የሚፈጸሙ የአምልኮ ሥነ-ሥርዓቶችን ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ለመሳተፍ የሚያስችል ፈቃድ እንደሚያገኙ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። 

“ፈቃዱ ይሰጠናል” ያሉት ፓትርያርኩ፥ “ሙስሊሞች የረመዳን በዓልን በኢየሩሳሌም እንዲያከብሩ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ሁሉ ክርስቲያኖች የብርሃነ ትንሳኤውን በዓል በኢየሩሳሌም ለማክበር ፍቃድ እንዲሰጣቸው አጥብቀን እንጠይቃለን” ብለዋል። ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም ለበዓለ ሆሳዕና እሁድ እና ለፋሲካ በዓል በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የፍቃድ ወረቀቶ ይኖሩናል” ብለዋል።

“አስቸጋሪ የፋሲካ በዓል ይሆናል” በማለት አስተያየታቸውን የሰጡት በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓተ አምልኮን የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬርባቲስታ ፒዛባላ፥ “በጌቴሴማኒ ኢየሱስን ያጋጠመውን የብቸኝነት ጊዜን አሁን ሁላችን የምንጋራው እንደሆነ አስባለሁ” ብለዋል።

 

23 March 2024, 16:14